የ63 ኩባንያዎች የማዕድን ማምረትና ምርምር ፈቃድ ተሰረዘ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2013ማስታወቂያ
በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በማዕደን ማምረትና ምርምር ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ከተሰጣቸው ተቋማት ውስጥ የ63ቱ ፈቃድ መሰረዙን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዐስታወቀ። የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ታከለ ዑማ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፦ ፈቃድ የተሰረዘባቸው ተቋማት በተገቢው ወቅት የተሰጣቸውን ፈቃድ ባለማሳደሳቸው፤ ከአቅም በታች በማምረትና የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ያልፈጸሙ ናቸው። ሚኒስትሩ በመግለጫው እንዳሉት በሜድሮክ ኢትዮጵያ በሻኪሶ-ለገደምቢ ሲተገበር የነበረው የማዕድን ማውጣት ተግባር ችግሮቹ ተቀርፎ ወደ ሥራ ይመለሳል። በሌላ በኩል ባለፉት ሁለት ወራት በትግራይ ክልል ሲመረት የቆየው በወር 346 ኪ.ግ. የሚገመት፤ ባጠቃላይም ከ700 ኪ.ግ. በላይ ወርቅ ወደ ማዕከላዊው ብሔራዊ ባንክ ሳይገባ ቀርቷል ተብሏል፡፡ ባለፉት አምስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ 302.9 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱም ታውቋል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ