የጀርመን የኳስ «ንጉሠ-ነገሥት» የ78 ዓመቱ ፍራንስ ቤከን ባወር አረፈ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2016
ማስታወቂያ
በጀርመን እግር ኳስ ታሪክ ስመ ጥር ዝና ካተረፉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የ78 ዓመቱ ፍራንስ ቤከን ባወር ትናንት ማረፉ ተገለጸ ። የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር ዕውቁ የኳስ ሰው ማረፉን ዛሬ ዐስታውቋል ። ቤንከንባወር በጀርመን የእግር ኳስ ታሪክ በተጨዋችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ዘመን የዓለም ዋንጫ ካነሱ ሦስት ጀርመናውያን መካከል አንዱ ነው ። ፍራንስ ቤከን ባወር ያረፈው ከጤና ችግር ጋ በተያያዘ መሆኑም ተዘግቧል ። የታኅሣሥ 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በጀርመን የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድም «ንጉሠ-ነገሥት» በሚል ቅጽል ስም ይታወቃል ። ለጀርመን ስፖርት ታላቅ አስተዋጽዖ ያበረከተው ይህ የስፖርት ሰው በዕድሜዎቹ መገባደጃ ላይ ግን ጀርመን እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 የዓለም ዋንጫን እንድታዘጋጅ ለማስቻል በተፈጸመ ቅሌት ውስጥም ስሙ ይነሳል ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ