1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ9 ዩሮ የትራንስፖርት ትኬት በጀርመን

ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2014

ጀርመን ወደየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ የሚጓዙ መንገደኞች በወር 9 ዩሮ ብቻ እንዲከፍሉ፣ ይህም ለ3 ወራት እንደሚዘልቅ ይፋ አድርጋለች። አላማውም ነዋሪዎች የግል መኪናቸውን ከመጠቀም ተቆጥበው በሕዝብ ትራንስፖርት በመጠቀም የነዳጅ ፍጆታን እንዲቀንሱ ነው ተብሏል።

ICE 4 Zug der Deutsche Bahn
ምስል Soeren Stache/dpa/picture alliance

የ9 ዩሮ የትራንስፖርት ትኬት በጀርመን

This browser does not support the audio element.

የጀረመን ምድር ባቡር ድርጅት Deutsche Bahan በቅርቡ በቡር ያደረገዉ የትራንስፖርት ዋጋ ቅናሽ ቋሚ የባቡር መንገደኞችን ሲያረካ፣ አዳዲስ መንገደኞችንም የባቡቡር ትራንስፖርት ተጠቃሚ አድርጓል። Deutsche Bahan አዲስ ባወጣዉ ታሪፍ መንገደኞች ለሶስት ወራት በየወሩ በ9ኝ ዩሮ ብቻ በመክፈል በአካባቢያዊ፣ በከተማ ዉስጥ ባቡሮችና ባዉቶቡሶች  መጓጓዝ ይችላሉ።
ሩስያ በዩክሬይን ላይ የከፈተችው ጦርነትና እሱን ተከትሎ በተጣሉ ማዕቀቦች ምክንያት በተለይም በነዳጅ ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ሐገሮችን ክፉኛ እየፈተነ ነው። ይህን ጉዳት ለማርገብ የተለያዩ የአውሮፓ ሐገራት የሕዝብ ትራንስፖርት ዋጋ ከመቀነስ እስከነአካቴው በነጻ እስከመስጠት የሚደርሱ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። ጀርመን በበኩሏ ወደየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ የሚጓዙ መንገደኞች በወር 9 ዩሮ ብቻ እንዲከፍሉ፣ ይህም ለ3 ወራት እንደሚዘልቅ ይፋ አድርጋለች። አላማውም ነዋሪዎች የግል መኪናቸውን ከመጠቀም ተቆጥበው በሕዝብ ትራንስፖርት በመጠቀም የነዳጅ ፍጆታን እንዲቀንሱ ነው ተብሏል።
አቶ አሸናፊ በርሊን ከተማ ኗሪ ናቸው የ9 ዩሮ ትኬትም ተጠቃሚ ነው። በዚህ ቅናሽ ቲኬት ወደተለያዩ የጀርመን ከተሞችከቤተሰቡ ጋ እየተጠቀመበት እንደነና በዚህም ደስተኛ እንደሆነ ገልጾልናል።

ሚስተር ሚላን ዢኩች ከሰርቢያ በጥተው በቦን ከተማ በሕክምና ሙያ ላይ ተሰማርተው ይኖራሉ። እሳቸው በአባዛኛው የ9 ዩሮ ትኬት ሐሳቡ ግሩም ቢሆንም በ3 ወራት የዋጋ ቅናሽ ሕዝቡ የሕዝብ ትራንስፖርት የመጠቀም ልምድ ያዳብራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸውልናል።

<< እኔ በጣም ደስ ብሎኛል። ምክንያቱም የ9 ዩሮ ትኬትሉሁሉም ነዋሪዎች ምቹ ነው። ለምሳሌ ከዚህ ከቦን ወደ ፍራንክፈርት ወይም ራቅ ያሉ ከተሞች ለአንድ ጉዞ እስከ 100 ዩሮ እከፍል ነበር። ደርሶ መልስ 200 ዩሮ መሆኑ ነው።  አሁን የህ ሁሉ ቀርቶ በ9ዩሮ ለአንድ ወር ወደየትኛውም የጀርመን ክፍል መጓዝ ይቻላል። የጀርመን መንግስት ይህ ያደረገው ከዩክሬይን ጦርነት ጋ በተያያዘ የነዳጅ ዋጋ በመወደዱ ነዋሪዎች የሕዝብ ትራንስፖርት የመጠቀም ልምድ እንዲያዳብሩ ታሳቢ በማድረግ ነው። በኔ በኩል ሓሳቡ ጥሩ ነው በሦስት ወር የቲኬት ቅናሽ ግን ልምዱ ይመጣል ብዬ አላምንም። ጊ,መንግስት ሐሳቡ ግን ግሩም ነው።>>
በአዲሱ የዋጋ  ምክንያት ከቦን እስከፍራንክፈርት ባሉ የባቡር ጣቢያዎች በሰዎች ተጨናንቀው ባቡሮችም ከወትሮው በተለየ ታጭቀው ሲያጓጉዙ ተመልክተናል።
ወጣት አለማዮህ የሙዩኒክ ከተማ ነዋሪ ነው። በ9 ዩሮ ትኬት ደስተኛ መሆኑን ቢገልጽም ከሶስት ወር ቦኋላም የዋጋ ቅናሹ ካልቀጠለ አሁን እየታየ ያለው የሕዝብ ትራንስፖርት የመጠአም ሁኔታ ወደነበረበት ሊመለስ ይችላል ባይ ነው።

በጀርመን በ2022 በተደረገ ጥናት በግል መኪና የሚጠቀመው ሰው ቁጥር 64 በመቶ ሲሆን የሕጥብ ትራንስፖርት ተጠቃሚው ግን 24 በመቶ ብቻ ነው። አሁን የተደረገው ቅናሽ የሕዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን ቁጥር እስከ 30 በመቶ  ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምስል Hauke-Christian Dittrich/dpa/picture alliance

ዮሀንስ ገብረእግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW