1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት ተጨማሪ ማዕቀብና የዩክሬን ጦርነት

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ ጥቅምት 14 2018

ዛሬ የአዉሮጳ ሐገራት መሪዎች ከዩክሬን ፕሬዝደንት ቮልዶሚር ዜለንስኪ ጋር ለንደን ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።የአዉሮጳና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የወሰዱት የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የዩክሬኑ ጦርነት ሥለሚቆምበት ብልሐት በቅርቡ ፑዳፔሽት-ሐጋሪ ዉስጥ ይነጋገራሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት መሆኑ ነዉ

ከግራ ወደ ቀኝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን።ሁለቱ መሪዎች በቅርቡ ቡዳፔሽት-ሐንጋሪ ዉስጥ ፊትለፊት ተገናኝተዉ ለመነጋገር ቀጠሮ ነበራቸዉ።ይሁንና የዉይይቱ ጊዜ ሲጠበቅ ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥለዋል
ከግራ ወደ ቀኝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን።ሁለቱ መሪዎች በቅርቡ ቡዳፔሽት-ሐንጋሪ ዉስጥ ፊትለፊት ተገናኝተዉ ለመነጋገር ቀጠሮ ነበራቸዉ።ይሁንና የዉይይቱ ጊዜ ሲጠበቅ ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥለዋልምስል፦ ZED

ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት ተጨማሪ ማዕቀብና የዩክሬን ጦርነት

This browser does not support the audio element.

ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት በያዝነዉ ሳምንት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ጥለዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ሮዝኔፍና ሉክኦይል የተባሉ የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ኩባንዮች አሜሪካ ዉስጥ ያላቸዉ ሐብትና ንብረት እንዳይንቀሳቀስ አግዳለች።የአሜሪካ ኩባንዮችም ከሁለቱ ኩባንዮች ጋር እንዳይሰሩ ከልክላለች።የአዉሮጳ ሕብረት በበኩሉ የሕብረቱ አባል መንግሥታት ከሩሲያ ፈሳሽ ጋዝ እንዳይገዙ አግዷል።አዉሮጳ ባንኮች ዉስጥ የሚገኝ የሩሲያ ገንዘብን ለዩክሬን ለመስጠትም አባል ሐገራት እየተነጋገሩ ነዉ።

ዛሬ የአዉሮጳ ሐገራት መሪዎች ከዩክሬን ፕሬዝደንት ቮልዶሚር ዜለንስኪ ጋር ለንደን ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።የአዉሮጳና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ እርምጃ የወሰዱት የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ መሪዎች የዩክሬኑ ጦርነት ሥለሚቆምበት ብልሐት በቅርቡ ፑዳፔሽት-ሐጋሪ ዉስጥ ይነጋገራሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት መሆኑ ነዉ።ሥለ ማዕቀቡና ዉይይቱ የዋሽግተን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW