1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ መስቷን አቋረጠች

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 2018

የትራምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ፣ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች ህጋዊ መኖርያ ፈቃድን በግዚያዊነት ማገዱን አስታወቀ። " ሁኔታዎችን ከገመገሙ በኋላ እና አግባብነት ካላቸው የአሜሪካ መንግስት ተቋሞች ምክክር ካደረጉ በኋላ፤ የደኅንነት ዘርፍ ቢሮ ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ለጊዜያዊ ጥበቃ ሁኔታ ስያሜ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንደማትቀጥል።

USA Haushaltskrise Shutdown Freiheitsstatue
ምስል፦ picture alliance / empics

አሜሪካ በተገን ጠያቂ ኢትዮጵያዉያን ላይ የወሰደችው ርምጃ አንድምታው ምን ይኾን?

This browser does not support the audio element.

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ መስቷን አቋረጠች

 

የትራምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ፣ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች ህጋዊ መኖርያ ፈቃድን በግዚያዊነት ማገዱን አስታወቀ።  "የአገሮችን ሁኔታ ከገመገሙ በኋላ እና

አግባብነት ካላቸው የአሜሪካ መንግስት ተቋሞች ምክክር ካደረጉ በኋላ፤ የደኅንነት ዘርፍ ቢሮ   ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ለጊዜያዊ ጥበቃ ሁኔታ ስያሜ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንደማትቀጥል፤  ፣ "የሃገር ውስጥ ደህንነት ጸሐፊው ክሪስቲ ኖኤም በፌዴራል ውስጥ በተለጠፈ ማስታወቂያ ላይ መናገራቸዉን ሮይተርስ ዘግቧል።

የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የሕግ ከለላ (TPS) ጥቅም አይገባቸውም ሲል ይህን እፎይታ ያነሳው ዛሬ አርብ ነው ። ጊዜያዊ ከለላው በሰሜኑ በተለይም በትግራይ ጦርነት ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የተሰጠ ነበር ። በዚህ እድል ሲጠቀሙ የነበሩ በግምት ወደ 26 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ላይ ምን ሊከተል ይችል ይሆን? ታምራት ዲንሳ የአትላንታ ዘጋቢኢችን ታሪኩ ኃይሉን በስልክ አነጋግሮታል ።

ታምራት ዲንሳ

ታሪኩ ኃይሉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW