1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብና መልዕክቱ፣ ቃለ መጠይቅ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 17 2013

በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግስታት ባለስልጣናት፣ በጦር አዛዦች፣ «መደበኛ ያልሆነ» ባሉት የአማራ ክልል ኃይል አዛዦችና በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይል አዛዦችና አባላት እንዲሁም በየቅርብ ቤተሰቦቻቸዉ ላይ የመግቢያ ፍቃድ ወይም የቪዛ እገዳ ጥሏል

Dr. Awol Allo
ምስል Privat

ከዶክተር አወል ቃሲም አሎ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

This browser does not support the audio element.


የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን እንደፃፉት  ትግራይ ዉስጥ ያለዉ ቀዉስና የኢትዮጵያን ልዑላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነትና የግዛት አንድነትን የሚያሰጉ ሌሎች አደጋዎችን ዩናይትድ ስቴትስን በጅጉ ያሳስቧታል።በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀመዉን ግድያ፣ አስገድዶ  ማፈናቀል፣ የወሲብ ጥቃትን፣ ለሰላማዊ ሕዝብ አገልግሎት በሚዉሉ በዉሐ፣ በሕክምና ማዕከላትና በሆስፒታሎች ላይ የሚደርስ ጥፋትና ዘረፋን ዩናይትድ ስቴትስ ታወግዛለች።ኤርትራ ጦሯና ከኢትዮጵያ ለማስወጣት የገባችዉን ቃል እንድታከብርም ሚንስትሩ ጠይቀዋል።
ይሁንና «የትግራይ ክልልን ያወደመዉን ጦርነት «በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተፋላሚ ኃይላት የወሰዱት ሁነኛ እርምጃ» የለም-እንደሚንስትሩ።

ምስል privat

«ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እርምጃ የሚወስድበት ወቅቱ አሁን ነዉ-ብለዋል ብሊንከን።ብሊንከን «ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ» ያሉት ወገን የሚያደርገዉን አናወቅም፣ መንግስታቸዉ ግን በኢትዮጵያና በኤርትራ መንግስታት ባለስልጣናት፣ በጦር አዛዦች፣ «መደበኛ ያልሆነ» ባሉት የአማራ ክልል ኃይል አዛዦችና በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይል አዛዦችና አባላት እንዲሁም በየቅርብ ቤተሰቦቻቸዉ ላይ የመግቢያ ፍቃድ ወይም የቪዛ እገዳ ጥሏል።ዩናይትድ ስቴትስ ምግብና መድሐኒትን ከመሰሳሰሉ የሰብአዊ ርዳታዎችና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ይጠቅማሉ ከምትላቸዉ ድጋፎች ዉጪ ለኢትዮጵያ የምትሰጠዉን የምጣኔ ሐብት፣ የፀጥታና የወታደራዊ ድጋፍም አቁማለች።ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪቃ ሐገራት ከምትሰጠዉ ርዳታ ከፍተኛዉን የምታገኘዉ ኢትዮጵያ ነበረች።በዓመት ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል።

ሥለ ማዕቀቡ ምክንያት፣ የሚያደርሰዉ ጫና እና መፍትሔዉን በተመለከተ በኪል-ብሪታንያ ዩኒቨርስቲ የሕግ ረዳት ፕሮፌሰርና የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር አወል ቃሲም አሎ እና በብራስልስ የዶቸ ቬለ ዘገቢ ገበያዉ ንጉሴን አነጋግረናል ሙሉ ቃለ መጠይቁን ለማድመጥ በቅደም ተከተል የቀረቡንትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ።

ነጋሽ መሐመድ 


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW