1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ዩክሬን የአውሮጳ ዋና አጀንዳ ሁና የመቀጠሏ ስጋት እና የሕብረቱ የተከፋፈለ አቋም

ገበያው ንጉሤ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2018

ስብሰባው የአመቱ የመጨረሻ ጉባኤ እንደመሆኑ ሁሉ በውጭ ግንኙነት፤ በስደተኖች ጉዳይ፣ የንግድና ኢኮኖሚ አጀንዳዎችና ወደ ህብረቱ ለመግባት በሚጠባባበቁ ሀገራት ማመልከቻዎችና ሌሎች ሲገፉ በቆዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን እንዲሚያሳልፍ ሲጠበቅ ነበር። ዋናውና ወሳኙ ጉዳይ ግን ለዩክሬን የፋይናንስ ችግር ባፋጣኝ መፍትሄ የማፈላለጉ አጀንዳ ነበር።

የዩክሬኑ ፓሬዚደንት ቮልዶሚር ዜሌንስኪ በአውሮጳ ህብረት ንግግር ሲያደርጉ
ለሳምንታት ሲያከራክር ቆይቶ ከውስኔ የተደረበት ይህ የህብረቱ ውሳኔ፤ የዩክሬንን መከላከያ የሚያጠናክር ነበርምስል፦ John Thys/AFP/Getty Images

ዩክሬን የአውሮጳ ዋነኛ አጀንዳ እንደሆነች የጎርጎሪዎሱን 2025 ተገባደደ

This browser does not support the audio element.

የአውሮፓ ህብረት የአመቱ የመጨረሻ ጉባኤ ዋና አጀንዳ

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት የተካሄደው የ27ቱ የአውሮጳ ህብረት አባል አገራት የመሪዎች ጉባኤ በተለየ ሁኔታ አሥጨናቂ የነበር ቢሆንም፤ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑ ነው የተገለጸው።  ስብሰባው የአመቱ የመጨረሻ ጉባኤ እንደመሆኑ ሁሉ  በውጭ ግንኙነት፤  በስደተኖች ጉዳይ፣ የንግድና ኢኮኖሚ አጀንዳዎችና ወደ ህብረቱ ለመግባት በሚጠባባበቁ ሀገራት ማመልከቻዎችና ሌሎች ሲገፉ በቆዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን እንዲሚያሳልፍ ሲጠበቅ የነበር ቢሆንም ዋናውና ወሳኙ አጀንዳ ግን ለዩክሬን የፋይናንስ ችግር ባፋጣኝ መፍትሄ የማፈላለጉ አጀንዳ ነበር።

የዩክሬን የፋይናንስ ችግርና የህብረቱ ድጋፍ ወሳኝነት

ዩክሬን ከሩሲያ የተከፈተባትን ጦርነት ለመመከት የአውሮጳ ህብረት በብዙ ቢዮን ዩሮ የሚቆጠር የገንዘብና ወታደራዊ እርዳታ ያደረገ ሲሆን፤ ባለፈው አመት ብቻ 27 ቢዮን ዩሮ እርዳታ መለገሱ ተገልጿል። ባሁኑ ወቅት ግን ዩክሬን በክፍተኛ የፋይናንስ ችግር ውስጥ በመሆኗና የአሜሪካ ድጋፍም እየቀነሰ በመሆኑ  አውሮጳ ደርሶ ክልታደጋት በስተቀር የፕሬዝደንት ዘለንንስኪ መንግስት ጦርነቱን መመክት ቀርቶ ህልውናው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል እየተገለጸ ነው።። አውርፓ ደግሞ ገና ከጅምሩ ሲደግፋትና ሲያስጣጥቃት የነበረችውን ዩክሬንን አሁንም በመደገፍና በማስጣጠቅ፤ እስታራቲጃዊ ጠላቴና የደህንነት ስጋቴ ነው ብሎ የፈረጀውን ሩሲያን መታገሉን ግዴታው አድርጎ እንደሚወስድ ነው የሚታመነው። በመሆኑም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በብራስልስ የተካሄደው የመሪዎች  ጉባኤ ዋና ግቡ ዩክሬንን ክውድቀትና ሽንፈት ለመታደግ የሚያስችል ፋይናንስ በማቅረብ ለሩሲያም የአውሮጳና ዩክሬን ወዳጅነትና አጋርነት ዘላቂ መሆኑን ማስገንዘብ መቻል ነበር ማለት ይቻላል።

መሪዎቹ የደረሱበት ስምምነትና ያሳለፉት ውሳኔ

27ቱ አባል ገሮች ከሞላ  ጎደል ሁሉም፤ ዩክሬንን አሁን መርዳትና ከጎኗ መቆም እንደሚያስፈልግ ቢያምኑም፤ ገንዘቡ ከየትና እንዴት ተገንቶ እንደሚሰጥ ግን ልዩነቶች ነበሯቸው። ኮሚሽኑ ያቀረባቸው አማራጮች ጀርመንና ሌሎችም የደገፉት፤  በአውሮፓ ባንኮች ታግዶ ከሚገኘው የሩሲያ 210 ቢዮን ኢሮ ታሳቢ 90 ቢዮን ኢሮ መርዳት ወይም የህብረቱ አገሮች ባጋራ ተብድረው ማቅረብ የሚሉት ነበሩ።  በየትኛው አማራጭ ሊስማሙ ወይም ደግሞ ጭራሹን ሊፋረሱ ይሆን ተብሎ በሚጠበቅበት ሰዓት ከተራዘም ውይይትና ክርክር በኈላ ሀሙስ ከሊሊቱ ዘጠኝ ሰአት  የካውንስሉና ኮሚሽኑ ፕሬዝዳንቶችና የወቅቱ የህብረቱ ፕሬዘደንሲ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስተር ከስብሰባው ወተው ነበር ውሳኔውን ያበሰሩትና እፎይታቸውን የገለጹት። የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ሚስተር አንቶኒዮ ኮስታ፡ “ ለዩኪሬን የገባነውን ቃል ፈጽመናል። ለሚቀጥሉት ሁለት  አመታት የሚሆን  የ90 ቢዮን ኢሮ እንዲሰጥ ወስንነናል” በማለት ገንዘቡ በህብረቱ አገራት ጋራ ብድር ኢሮ ቦንድ  የሚገኝ እንደሆነና  ዩክሬን ይህን ገንዘብ የምትከፍለው ሩሲያ የጦርነት ጉዳት ካሳ ስትከፍላት መሆኑን አስታውቅዋል።

27ቱ አባል ገሮች ከሞላ  ጎደል ሁሉም፤ ዩክሬንን አሁን መርዳትና ከጎኗ መቆም እንደሚያስፈልግ ያምናሉምስል፦ Lisi Niesner/REUTERS

የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዝሮ ቮንዴር ለየንም እንደዚሁ፤ “ አባል አገሮች በጋራ ተብድረው ለሁለት አመት የሚዘልቅ  የ90 ቢዮን ኢሮ ብድር ለመስጠት ተስማምዋል” በማለት ይህም በአውሮፓ ህብረት ዋስትና ከገበያ ሚገኝ ብድር  መሆኑን ግለጸዋል።

ዩክሬንን ከሩሲያ ተቀማጭ ገንዘብ ለመርዳት በነበረው ዕቅድ የገጠመው ተቃውሞ ጭብጥ

የአውሮጳ ኮሚሽን በቅድሚያ ያቀረበውና በብዙዎቹ አባል አገሮች በተለይም በጀርመን ይገፋ የነበረው ከሩሲያ በአውሮፓ ባንኮችታግዶ ካለ ገንዘብ  ወጭ ሆኖ ለዩክሬን ይሰጥ የሚለው ሀሳብ ውድቅ የተደርገው በዋናነት አባዛኛው እንዳይንቀሳቀስ የታገደው የሩሲያ ገንዘብ የሚገኝባት ቤልጅየም ባቀረበችው ተቃውሞና ህጋዊ ክርክር ነው። በአውሮፓ ባንኮች እንዳይንቀሳቀስ ታግዶ የሚገኘው የሩሲያ 210 ቢሊዮን ኢሮ ውስጥ 180 ቢሊዮኑ በቤልጅየም ኢሮክሊር የገንዘብ ማስቀምጫ ባንክ  የተቀመጠ ነው።  የቤልጀይም ተቃውሞ ምንም እንኳ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት በማወጇ  ንብረቱ እንድይንቀሳቀስ ቢደረግም ይህን ገንዘብ አሳልፎ ለሌላ ያውም እየተውጋቻት ላለችው አገር ዩክሬን መስጠት ግን የህግ ጥያቄ ሊያስነሳና ባለዕዳም ሊያደርግ ይችላል የሚል ነው። ቤልጅየም ይህን ገንዘብ አሳልፋ ልትሰጥ የምትችለው ህብረቱ ሊደርስባት ለሚችለው የህግ ተጠያቂነትና ባለዕዳነት ሙሉ ዋስትና ሲሰጣት ብቻ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስተር በርት ዴዌቨር የጦርነት ካሳ አከፋፈል ውስብስብና ግዜ የሚፈጅ ወይም ደግሞ ሊክፈልም የማይችል ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ጭምር መሞገታቸው ተገልጿል።፡

ጉባኤው ያጸደቀው የአውሮጳ የጋራ ብድር መርጃ ዕቅድና የጀርመን ቅሬታ  

ባንጻሩ አባል ሃገራት በጋራ ከገበያ ተበድረው ለዩክሬን ቢያበድሩ ተመራጭ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስተር ዴዌቨር እንደ አማራጭ አቅርበው ነበር።  አንድን አባል ሀገር ተጠያቂና ባለዕዳ ሊያደርግ ከሚችል አሰራር ይልቅ አባል አገራቱ በጋራ ተብድረው ለዩክሬን ሊረዱ ይችላሉ በማለት አገራቸው ለዩክሬን እርዳታ መሰጠቱን እንደማትቃወም ሚስተር ዌቨር አስታውቀዋል። የአውሮጳ ኮሚሽኒም በኮሚሽኑ በጀት ዋስትና የጋራ ብድር ወይም ኢሮ ቦንድ አማካይነትለዩኪሬን ብድር ማቅረብን በሁለተኛ አማራጭ ይዞት የነበር ሲሆን፤በመጨርሻ መሪዎቹ መሪዎቹ ያጸደቁት የ90 ቢዮን ኢሮ የሚገኘውም ከዚህ የጋራ ብድር እንደሆነ ተገልጿል። ይህ በድር ከወለድ ነጻና ከሩሲያ የጦርነት ካሳ ክፍያ በኋላ የሚመለስ እንደሆነም በውሳኔው ተመልክቷል።

ጀርመንና የስሜን አውሮፓ አገሮች ይህኛውን የጋራ ብድር ዕቅድ ተቀባይነት እንዳያገኝ በሰፊው ተንቀሳቅሰው እንደንበር ነው የሚታወቀው። በተለይ የጀርመኑ ቻንስለር  ፊሬሪክ ሚርዝ የየጋራ ብድሩ በዜጎች ላይ ተጨማሪ ጫና አስለሚፈጥር ብቻ ሳይሆን ለዩክሬን ችግር በቅድሚያ የሩሲያን ገንዘብ መጠቀም ተገቢና ለሩሲያም ትምህርት ሰጭ ነው በሚል እመንት ከጉባኤው በፊት ብራስልስ ድረስ በመዝለቅ  ጠቅላይ ሚኒስተር ባርት ዌቨርን ለማሳመን ጥረት ማድረጋቸው ተሰምቷል። ሆኖም ግን የቤልጅየሙ ጠቅላይ ሚኒስተር ባልተለመደ ሁኔታ ከባባዶቹን የህብረቱን አባል አገሮች  በመጋፋትና በጽናት በመከራከር  ዕቅዱን በማስለውጣቸው በተለይ በአገራቸው አብኛው ህዝብና ተቃዋሚዎቻቸው ጭምር ድጋፍ አግንተዋል ተወድሰዋልም።

ውሳኔው ያለተቃውሞ ያለፈበት ዘዴ

በነበረው ሰፊ ልዩነትና ሰፊ ክርክር ምክኒያት ጉባኤው ከስምምነት ሳይደርስ እንዳይነሳ ስጋት ተፈጥሮ እንድነበር የሚገልጹት ምንጮች፤ ይህ እንዳይሆንና ከጋራ ውሳኔ ላይ እንዲደረሰ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆርጂያ ሜሎኒ አስተውጾ ከፍተኛ እንድነበር ተንግሯል። ጠቅላይ ሚኒስተር ሜሎኒ የሩሲያን ተቀማጭ ገንዘብለዩክሬን በማዋል በኩል ከቤልጅየም የተነሳውን ስጋት እንደሚጋሩ አሳውቀው የነበር ሲሆን፤ ጉባው ከውሳኔ መድረስ ሲያቅተው  የጋራ ብድሩን ዕቅድ በማንቀሳቀስና ውሳኔውን ሊያግዱ የሚቺሉትን አገሮችንም ከብድሩ ነጻ እንዲሆኑና ውሳኔውን ግን እንዳይቃወሙ በማግባባት የጋራ ብድሩ እቅድ ከ27ቱ አባል አገራት በ24ቱ አገሮች ተደግፎ እንደጸደቀ  በማደረግ በኩል ገንቢ ሚና ተጫውተዋል ነው የሚባለው ።

የጋራ ብድር የውሳኔ ሀሳብ የሁሉንም አባል አገራት ስምምነት የሚጠይቅ ቢሆንም ሀንጋሪን ስሎቫኪያንና ቼክ ሪፑብሊክን ብድሩ እንዳይመለክታቸው በማድረግ ውሳኔውን ግን እንዳይግዱ ማድረግ እንድተቻለ ታውቋል።

የጉባኤው ውሳኔ አንደምታና ግብረ መልሶች

ለሳምንታት ሲያከራክር ቆይቶ ከውስኔ የተደረበት ይህ የህብረቱ ውሳኔ፤ የዩክሬንን መከላከያ የሚያጠናክርና፤ መንግስታዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት የሚያግዝ ሲሆን፤ ለሩሲያ ደግሞ አውሮፓ አሁንም ከዩኪረን ጎን የቆመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

በርክታ ያውሮፓን ፖለቲካ የሚከታተሉ ታዛቢዎች አሁን ባለው ሁኔታ ለዩክሬን መርጃ የሚሆን ገንዘብ ማፈላለግና ማግኘት ትልቅ ተግዳሮት በመሆኑ ጉባኤው ይህን ማድረግ መቻሉ ስኬት እንደሆነ ነው የሚናገሩት።፡ በአውሮፓና አለማቀፍ ፖለቲካ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዳኔኤላ ስቺክዋርዘር ጉባኤው የተሳክ ነበር ከሚሉት አንዷ ናቸው። “ ባጠቃላይ ጥሩ የጋራ ውሳኔ ነው። ካንድ የጋራ ግብ ለመድረስ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ  የብሄራዊ ፍላጎቶች ግጭት ሲኖር የሚደርስበት የጋራ ስምምነትና ውሳኔ ነው በማለት ዋና ግባቸው የሆነውን ዩክሬንን የመርዳት ግብ ያሳካ ጉባኤ መሆኑን ገልጸዋል።

ርክታ ያውሮፓን ፖለቲካ የሚከታተሉ ታዛቢዎች አሁን ባለው ሁኔታ ለዩክሬን መርጃ የሚሆን ገንዘብ ማፈላለግና ማግኘት ትልቅ ተግዳሮት ሆኗልምስል፦ Stephanie Lecocq/REUTERS

የቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስተር ባርት ዴዌቨርም ተቃውሟቸው በአገራቸው ታግዶ የተቀመጠው ገንዘብ ለዩኪረን ሊተላለፍበት የነበረውን ዕቅድ እንጂ ለዩኪሬን እርዳታ መስጠቱን እንዳልሆነ በመግለጽ፤ በጋራ ብድር ዩክሬን እርዳታ እንዳታገኝ ቢደረግ ለዩክሬንም ላውርፓ ህብረትም ትልቅ ውድቀት ይሆን እንደነበር ተናግረዋል፤ “ብራስልስ በዚህ ጉዳይ ተክፋፍሎ ቢሆን ኖሮ አውሮፓ ከጂኦ ፖለቲካ ጠቀሜታው  ወቶ ነበር።ለዓለምም አውሮፓ የተአማኒነቱ ግዜ አብቅቷል የሚል መልክት የሚያስተላልፍ ነበር” በማለት ውሳኔው ውሮፓንም ዩኪረንንምነ ያዳነ መሆኑን ገልጸዋል።

ሩሲያ ግን ህብረቱ በሩሲያ ተቀማጭ ገነዘብ ላይ ማዘዝ አለመቻሉን እንደአቅመ ቢስነትና የአጸፋእርምጃውን በመፍራትእንደተወሰደ አድርጋ ነው የወሰደችው። የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒተር ሚስተር ኦርባን ውሳኔው የሩሲያን ገንዘብ ሳይነካ መወሰኑ ትክክል እንደሆነና የቤልጀይም ጠቅላይ ሚኒስተር ጥሩ ስራ እንደሰሩ ሲናገሩ ተሰምተዋል

 ጠቅላይ ሚኒስተር ዴዌቨር ግን ውሳኔው ይልቁንም ለሩሲያ የእሚያስተላልፈው መዕክት ቀላል አይደለም ነው የሚሉ፤ “ ለሞስኮ የሚያስተላለፈው መልክት አለው፤ ምክኒያቱም ውሳኔው አውሮፓ ዩክሬንን ለቀጣዮቹ ሁለት አመታትም የሚረዳ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ሚስተር ፑቲን ጦርነቱን ለማቆም እንዲያስቡ ሊያደርጋቸውም ይችላል” በማለት  ውሳኔው ጦርነቱን በማቀዝቀዝ በኩል አስተዋጾ ሊኖረው እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ዩክሬን የአውሮፓ ዋና አጀንዳ ሁና የመቀጠሏ ስጋት

በተጭማሪም ህብረቱ በሩሲያ ተቀማጭ ገንዘብ ላይ አለመወሰኑ ለአሜሪካ  የሰላም ጥረት ሊረዳና ምናልባትም የድርድር ማሳለጫ ግባት ሊሆን እንደሚችልም የሚናገሩ አሉ። ይህ ሁሉ ሆኖም ግን፤
የዩክሬን ጉዳይ ላለፉት ሶስት አመታትና በተለይም በዚህ አመትየአውሮፓ ተግዳሮትና አመቱን ሙሉም በየስብሰባዎቹና የመሪዎች ጉባኤ አይንተኛና አከራራክሪ  አጀንዳ እንደንበር ሁሉ፤  በቀጣዩ አመትም እንደዚሁ መነጋገሪያና መወዛገቢያ፤ ምናልባትም የልዩነትና የክፍፍል  ምክኒያት ሆኖ እንደሚቀጥል ነው የብዙ ባለሙያዎች እመንት። አሜሪካ ከዩኪሬንና ሩሲያ  ጦርነት ለመውጣት እያሳየች ያለው ዝንባሌ፤ ያቀረበችው የሰላም ዕቅድ የዩክሬንና የህብረቱን ፍላጎቶች በሚያሟላ  ሁኔታ የመሳካቱ ሁኔታ ማጠራጠሩ፤ እንዲሁም ፕሬዝዳንት ትራም አሚሪካ ካውሮፓ ጋር ያላትን ስትራቴጂክዊ አጋርነት እያጠየቁ መሆኑ፤ ላውሮፓ ቀጣዩ አመትም የፈተናና ተግዳሮት አመት ሊሆን እንደሚችል አመላካቾች ናቸው እንደ ብዙዎቹ የፖለቲካ ተንታኞች አስተያየትና እምነት ።፡

ገበያው ንጉሴ

 

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW