1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ግንቦት 14 2009

በሳውዲ አረቢያ ካለሕጋዊ ፈቃድ  የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ የተሰጣቸዉ የ90 ቀናት ገደብ ሊያልቅ አንድ ወር ገደማ ቀርቶታል። የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ እየሞከረ መሆኑ ተሰምቷል።

Saudi Arabien Arbeiter kehren nach Äthiopien zurück
ምስል DW/S. Shiberu

M M T/ Unstoppable Illegal Migration to Saudi Arabia - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የሳዉዲም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ ጥረታቸውን መቀጠላቸውን ቢናገሩም፣ አንዳንድ ኢትዮጵያውን ወደ ሳዉዲ የሚያደርጉቱን ሕገወጥ ጉዞ እንዳላቋረጡ ዶይቼ ቬሌ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች  ገልጸዋል።

አቶ ፉኣድ ዩሱፍ አህመድ ከአምስት ዓመት በላይ በጅዳ ከተማ ይኖራሉ። በኢትዮጵያ ያለዉ «ኢኮኖሚና ነጻነት ጉዳይ» ባህር አቋርጠው ወደ ሳዉዲ መሄድ መገደዳቸውን የሚናገሩት  አቶ ፉኣድ ግን እስካሁን ሕጋዊ የመኖርያ ፍቃድ የላቸውም። እንደሳቸው አሁንም ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እንዲወጡ የሳውዲ መንግሥት በጠየቀበት ባሁኑ ጊዜም ግን ሌሎች ተሰደው የሚመጡ እንዳሉ አቶ ዩሱፍ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

አቶ ፉኣድ ወደ ሳውዲ በስደት የሚገቡት ኢትዮጵያውያን ብዛት ምን ያህል መሆኑን ለመናገር እንደማይችሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ እየሞከረ መሆኑ ተሰምቷል። ሰሞኑንም የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሳውዲ የሚገኙት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ለመመለስ ያመነቱበት ድርጊት እንዳሳሰባቸዉ ገልጸው፣ የተሰጣቸዉ ቀነ ገደብ ሳያበቃ በፊት እንዲመለሱ ጠይቀዋል።

መንግሥት ዜጎቹ ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ እያበረታታ እና አስፈላጊ ዝግጅቶችን እያደረገ ባለበት በዚሁ ጊዜ ሌሎች ዜጎች በሕገወጥ መንገድ መሰደድ መቀጠላቸው ይሰማል።

ወደ 400,000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ካለሕጋዊ ፈቃድ በሳዉዲ አረቢያ እንደሚኖሩ ይገመታል። ከዚህም መካከል 23,000 የጉዞ ሰነዶች እንደወሰዱ መንግሥት ያወጣቸው ዘገባዎች ያሳያሉ። ይኸው ቁጡር ተለዋዋጭ እንደሆነ የገለጹት አቶ መሃመድ ወደፊት መረጃዎችን ሰብስበው ይፋ እንደምያደርጉ አስታውቀዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW