1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያየለው የሶሪያ ዓመፅ

ሰኞ፣ ሐምሌ 16 2004

የአረብ ሊጋ በሶርያ ውጊያው ያበቃ ዘንድ አሳድ በፍጥነት አል ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ ዛሬ ሲጠይቅ የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በሶሪያ መንግስት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለማጠናከር ወስኗል። ይህንን ርምጃ ሶርያ ዝም ብላ እንደማትመለከት በበኩሏ እየገለፀች ነው።

Syrian regime supporters flash the V-victory sign as they hold up a portrait of Syrian President Bashar Assad during a rally at Umayyad Square in Damascus, Syria. Wednesday Oct. 26, 2011. Some thousands of Syrians packed the square Wednesday in a show of support for embattled President Bashar Assad, a few hours ahead of a visit by senior Arab officials probing ways to start a dialogue between the regime and the opposition. (ddp images/AP Photo/ Bassem Tellawi)
ምስል AP

የቃታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሀመድ ቢን ያሲም አል ታኒ ዛሬ እንዳስታወቁት፤ የአረብ ሊጋ  አል አሳድ ስልጣናቸውን ባስቸኳያ እንዲለቁ ጠይቋል።  እንደ አልጃዚራ ዘገባ አል በአሳድ ላይ ጉዳት ሳይደርስ አገራቸውን ለቀው የሚወጡበትን መንገድ ሊጋው እንደሚያመቻች አል ታኒ ገልፀዋል።  ሚኒስትሩ አክለውም የሶሪያን ስደተኞች ለመርዳት ሊጋው 100 ሚሊዮን ዶላር ዝግጁ ማድረጉን፣ እንዲሁም ልዩ የሶርያ ልዑክ ኮፊ አናን  ንግግራቸውን ስልጣኑን ወደፊት ከሚረከበው የሽግግር መንግስት ላይ እንዲያተኩሩ አሳስበዋል።

እንደ ተቃዋሚ ወገኖች ገለፃ፤ የመንግስት ወታደሮች ደማስቆስ ውስጥ የመኖሪያ አካባቢዎችን ጭምር ሲያጠቁ ሰንብተዋል።

  በሰሜን ሶሪያ በምትገኘው ሁለተኛ ትልቅ ከተማ አሌፖ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል ትናንት ከባድ ውጊያ ሲካሄድ ቆይቷል። ፍልሚያው ባየል ቁጥር  አገር እየለቀቀ ወደ ጎረቤት አገሮች ቱርክ እና ኢራን የሚሰደደው ዜጋ በጣሙን ጨምሯል።  የድንበር መሸጋገሪያ ባብ ኤል ሳላም  በአማፂያኑ እጅ መሆኑ ተነግሯል። አንድ የኢንተርኔት ቪዲዮ በድንበር አካባቢ ስላለው ግጭት ሲያሳይ፤

ጦርነት በሶሪያምስል Reuters

«  የመሸጋገሪያ ድንበር ባብ ኤል ሳላምን ከከበብን በኋላ ከአሳድ ሰዎች ነፃ አድርገናል። ከከባድ ሽንፈት በኋላ ሸሽተዋል። ይኼው እኔ  ባብ ኤል ሳላም መተላለፊያ  ከሶሪያ ነፃ አውጭ ወታደር ወንድሞቼ ጋ ቆሜያለሁ። ይህ ህንፃ ከቱርክ ጋ ይለየናል። እግዚያንሄር ፍቃዱ ከሆነ አሌፖን ነፃ አውጥተን አቃጣሪዎቹን ለመሸኘት ወደ ፕሬዘዳንቱ ቤተ መንግስት እናመራለን፤ ።»

የመንግስት ወታደሮች ይህንኑ የድንበር መሸጋገሪያ ቆይተው ከአየር እንደደበደቡ ተገልጿል። ከኢራን ጋ በሚያዋስነው ድንበርም እንደዚሁ ጦርነት እንደሚካሄድ ነው የሚነገረው፤« ሶርያ ውስጥከቀጠለው ውጊያ በኋላ እጅግ ብዙ  ሰዎች እየተመለሱ ነው። ባለፈው ሀሙስ ብቻ 3000 ሰዎች ከጦርነት ሸሽተው መጥተዋል። ይህም በድንበር አካባቢ የሚካሄደውን ስራ ከባድ አድርጎታል። ይሁንና በትራንስፖርት  ሚኔስቴር ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከድንበሩ ወደ ባግዳድ ልንወስዳቸው ችለናል።»

ይላሉ የድንበሩ ከተማ ከንቲባ አብደልሚኒም ካላፍ ። የሶሪያ የተቃዋሚ ብሔራዊ ምክር ቤት እንደገለፀው ከቱርክ መንግስት ጋ የድንበር ቁጥጥሩን በተመለከተ ውይይት ተጀምሯል። የብሔራዊ ምክር ቤት ቃል አቀባይ አብዱል ባሴት ሳኤዳ፤

  « የድንበር መተላለፊውን ሙሉ ቁጥጥር ገና በትክክል ማጣራት ይኖርብናል፤ በዚያ ስላለው ሁኔታ ለመናገር ።  ስለዚሁ ጉዳይ ከቱርክ መንግስት እና ከሶሪያ ነፃ አውጭ ጦር ጋ እንመክራለን። ምክንያቱም ቱርክ ኋላፊነት አለባትና። በመሠረቱ በድንበሩ የሚታየውን ሁኔታ ለማስተካከል የሚያስችሉ ውሳኔዎች መወሰድ አለባቸው ።»

በኢራን የመጠሊያ ጣቢያምስል Reuters

የሶሪያ የመንግስት ቴሌቪዥን ከቀናት በኋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ አሳድን በቴሌቪዥን አሳይቷል። ዛሬ የአውሮፓ ህብረት ብራስልስ ውስጥ ባደረገው ውይይት በሶርያ መንግሥት ላይ ማዕቀቡን ለማጠናከር ወስኗል።  ይህ በዚህ እንዳለ፣ የሶሪያ መንግስት ከውጭ አገሮች ጥቃት ከተሰነዘረበት በኬሚካል መሳሪያዎች እንደሚጠቀም ገልጿል። 

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW