ደም አፋሳሹ የኬንያ ምርጫ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 23 2000ማስታወቂያ
መንግስት በአገሪቱ መገናኛ ዘዴዎች የቀጥታ ስርጭት እገዳ አስፍኖአል። የአዉሮጻ ህብረትን ወክሎ በኬንያ የተከናወነዉን የምርጫ የተከታተለዉ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫዉ መስተጓጎሉን እና የተነገረዉ ዉጤት አጠራጣሪ መሆኑን ገልጾአል። በሌላ በኩል ኦዲንጋ የሚመሩት የብርቱካኑን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ነገ በናይሮቢ የሃዘን መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥሪ አቅርቦአል። መንግስት ተቃዋሚዉ ፓርቲ የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኑን ይከሳል። በናይሮቢ ነገ ይደረጋል የተባለዉ የሃዘን መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ሌላ ደም እንዳያቃባ እያሰጋ ነዉ ዝርዝሩን ያድምጡ