1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳን ወደ ሁለተኛ ዙር ጦርነት ትገባ ይሆን?

ቅዳሜ፣ ኅዳር 27 2012

በደቡብ ሱዳን ኖርዘርን ሌክስ ግዛት ግጭት ተቀስቅሶ 79 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ሰላም አስከባሪዎች ጣልቃ ገብተዋል። በአካባቢው በጣለው ከባድ ዝናብ እና የአገሪቱ መንገዶች ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ሳቢያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ባለፈው ማክሰኞ ሩምቤክ ከተባለችው የግዛቲቱ ዋና ከተማ ወደ ማፐር የተጓዙት በሔሊኮፕተር ነበር

የኅዳር 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ትኩረት በአፍሪቃ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ሱዳን ኖርዘርን ሌክስ ግዛት ግጭት ተቀስቅሶ 79 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ጣልቃ ገብተዋል።

በአካባቢው በጣለው ከባድ ዝናብ እና የአገሪቱ መንገዶች ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ሳቢያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ባለፈው ማክሰኞ ሩምቤክ ከተባለችው የግዛቲቱ ዋና ከተማ ወደ ማፐር የተጓዙት በሔሊኮፕተር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት 75 የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ጋክ እና ማኔዌር በተባሉ ማኅበረሰቦች መካከል ለተቀሰቀሰው ግጭት መፍትሔ እስኪፈለግ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት በዚያው ይቆያሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ የደቡብ ሱዳን ልዩ ልዑክ ዴቪድ ሺረር ውጊያው እንዲቆም አሳስበዋል። በሁለቱ የደቡብ ሱዳን መሪዎች መካከል ያለው ልዩነት መፍትሔ ካልተበጀለት መላ አገሪቱ ወደ ሁለተኛ ዙር ዩ,ርስ በርስ ጦርነት እንዳትገባ አስግቷል። የዛሬው ትኩረት በአፍሪካ መሰናዶ በደቡብ ሱዳን እና በሶማሌ ላንድ ፖለቲካ ላይ ያተኩራል።

ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW