1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ደቡብ ሱዳን፣ የአሕ ጉባኤና የኢትዮጵያ መስተንግዶ

ረቡዕ፣ የካቲት 15 2015

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽ/ቤት የዛሬው መግለጫ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተደርጎ በነበረው 36 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዙሪያ ያተኮረ ነበር። 53 የአፍሪካ ሀገራት የተሳተፉበት ነው የተባለው ይሄው ጉባኤ ላይ ሌሎች ብዙ ቁጥር ያላቸው የሚመለከታቸው ተሳታፊዎችም የተስተናገዱበት እንደነበር ተገልጿል።

Äthiopien Addis Abeba | 36. Sitzung des Afrikanischen Union Gipfel
ምስል፦ Solomon Muche/DW

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ጥቃት በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.


                     

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ኢትዮጵያን ግዛት ዘልቀዉ በመግባት የከፈቱን ጥቃት ለማስቆም የሁለቱ ሐገራት ባለስልጣናት ለመነጋገር እየጣሩ መሆናቸዉን የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ደቡብ ምዕራብ ድንበር በኩል 200 ኪሎ ሜትር ድረስ በመግባት ሰዎችን መግደል፣ሐብት ንብረት መዝረፍና የወርቅ ማዕድን ማዉጫ ጉርጓዶችን መቆጣጠራቸዉ ተዘግቧል። የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ በሰጠዉ ሳምንታዊ መግለጫ ከደቡብ ሱዳኑ ዉግብ በተጨማሪ ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ አዲስ አበባ ዉስጥ ስለተደረገዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ሒደትም ማብራሪያ ሰጥቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽ/ቤት የዛሬው መግለጫ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ተደርጎ በነበረው 36 ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዙሪያ ያተኮረ ነበር። 
53 የአፍሪካ ሀገራት የተሳተፉበት ነው የተባለው ይሄው ጉባኤ ላይ ሌሎች ብዙ ቁጥር ያላቸው የሚመለከታቸው ተሳታፊዎችም የተስተናገዱበት እንደነበር ተገልጿል።
ጉባኤው የተናበበ ሥራ የተከናወነበት ፣ ኢትዮጵያውያን ኃላፊነታቸውን በበጎ የተወጡበት እና በሰላም ተጀምሮ በሰላም የተጠናቀቀ ነበር ሲሉ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል። "ስኬታማ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል። 
ከጉባኤው በተጓዳኝ በተደረጉ የሁለትዮሽ ውይይቶች ኢትዮጵያ ብዙ ድጋፎችን ማግኘት መቻሏን የገለፁት ቃል ዐቀባዩ " ተገኘ ያሉትን ስኬት ሲገልፁ በዓመት ሊሰራ የሚችለውን ሥራ  በአንድ ሳምንት ያከናወንበት ነው" ብለዋል።
ለሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ ከደቡብ ሱዳን ደንበር አቋርጠው እስከ 200 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው በገቡ ታጣቂዎች እየፈፀሙት ነው ስለተባለው ከግድያ፣ ዝርፊያና ማፈናቀል ያለፈ የወርቅ ማውጫ ሥፍራዎችን የመቆጣጠርና ሕገ - ወጥ የጦር መሣሪያ የማዘዋወር ጉዳይ "የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት እና የፀጥታ መዋቅሮች ተነጋግረው ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ" የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከሌሎች የጎረቤት ሀገሮች በተለይም ከሱዳን እና ኤርትራ ጋር ያላት የድንበር ጥበቃ ቁጥጥር ምን ይመስላል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ግን ምላሽ አልሰጡበትም።
ሰለሞን ሙጬ 

የኢትዮጵያ ዉጉሚ ቃል አቀባይ መለስ ዓለምምስል፦ Solomon Muchie/DW

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW