1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃ ከእሥራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ማቋረጧ ያስከተለው ድጋፍና ተቃውሞ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 15 2016

ራማፎሳ ደቡብ አፍሪቃ ጉዳዩ ወደ ICC እንዲተላለፍ ማድረጓን ኳታርን በጎኙበት ወቅት ነበር ለጋዜጠኞች የተናገሩት። የውሳኔ ሀሳቡን ያዘጋጀው «የኤኮኖሚ ነጻነት ተዋጊዎች» የተባለው የግራ ክንፉ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው። የፓርቲው ሊቀመንበር ጁልየስ ማሌማ እስራኤል ለዓለም አቀፍ ሕግ ተገዥ እስክትሆን ድረስ ያለን ግንኙነት መቋረጥ አለበት ብለዋል።

Cyril Ramaphosa
ምስል Khaled Desouki/AFP

ደቡብ አፍሪቃ ከእሥራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ማቋረጥ መወሰኗ ያስከተለው ድጋፍና ተቃውሞ

This browser does not support the audio element.

የደቡብ አፍሪቃ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሪቶሪያ የሚገኘው የእሥራኤል ኤምባሲ ለመዝጋትና ከእሥራኤል ጋር የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሙሉ ለማቋረጥ መወሰኑ ድጋፍም ተቃውሞም አስከትሏል።። ምክር ቤቱ በ248 የድጋፍና በ91 ተቃውሞ ያሳለፈው ይህ ውሳኔ እሥራኤል ከሀማስ ጋር በምታካሂደው ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እስክትደርስ ድረስ መሆኑንም አስታውቋል። የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት በውሳኔ ሀሳቡ ለመስማማት የበቃበት ምክንያት በኃይል በተያዘችው በፍልስጤም ግዛት የሚፈጸሙት ወንጀሎች መሆናቸውን አስታውቋል። የኤ.ኤን.ሲ ሊቀ መንበርና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እሥራኤል ፍልስጤም ውስጥ የምትፈጽመው የጦር ወንጀል ነው ብለዋል። 
«ደቡብ አፍሪቃ እንደ ሌሎች የዓለማችን በርካታ ሀገሮች የእሥራኤል መንግሥት እርምጃ ወደ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በምህጻሩ ICC መተላለፍ የሚገባው አድርጋ ትመለከተዋለች። ያስተላለፍንበት ምክንያትም በዚያ የጦር ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብለን ስለምናምን ነው። አሁን ወደ ሰዎች ማጎሪያ ካምፕነት በተቀየረውና የዘር-ማጥፋት በሚካሄድበት በጋዛ በሚሆነው በጣም ደንግጠናል።»የእስራኤል ሃማስ ግጭት የአፍሪቃውያንን አስተያየት ከፋፍሏል
 
ራማፎሳ ደቡብ አፍሪቃ ጉዳዩ ወደ ICC እንዲተላለፍ ማድረጓን ኳታርን በጎኙበት ወቅት ነበር ለጋዜጠኞች የተናገሩት። የውሳኔ ሀሳቡን ያዘጋጀው «የኤኮኖሚ ነጻነት ተዋጊዎች» የተባለው የግራ ክንፉ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው። የፓርቲው ሊቀመንበር ጁልየስ ማሌማ እስራኤል ለዓለም አቀፍ ሕግ ተገዥ እስክትሆን ድረስ ያለን ግንኙነት መቋረጥ አለበት ብለዋል።
«በሕገ መንግሥታችን እሴቶች ስም የፍልስጤማውያን ሰብዓዊ መብቶች እስኪከበሩ ፣ እስኪታወቁ እና ጥበቃ እስኪደረግላቸው ድረስ እነዚህን ግንኙነቶች ማቆም አለብን። እሥራኤል ለዓለም አቀፍ ሕጎች ተገዥ መሆን አለባት። ይህ ሳይሆን ከነርሱ ጋር የምንቀጥለው ማናቸውም ግንኙነት ሕገ መንግሥታችንን እንደማጥቃት መቆጠር አለበት።»
በጉዳዩ ላይ የሀገሪቱ ምክርቤት ውሳኔ ከማሳለፉ በፊት በእንግሊዘኛ ምህጻር FF+ የተባለው  የነጭ ብሔረተኞቹ ፓርቲ «የነጻነት ግንባር »ደቡብ አፍሪቃ በዚህ የውሳኔ ሀሳብ ሰበብ ችግር ውስጥ እንዳትወድቅ አስጠንቅቆ ነበር። ከፓርቲው አባል አንዱ ኮርነ ሙልደር እንዲህ ነበር ስጋታቸውን የገለጹት።
«የእሥራኤልን አምባሳደር ብታባርር እና ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ብታቋርጥ ደቡብ አፍሪቃ ምንም ዓይነት ሚና መጫወት የምትችልበት አቋም አይኖራትም። ሽምግልና ይሁን ግጭቱን ለማስቆም በሚደረግ ጥረት ውስጥ  የበኩሏን አዎንታዊ እና ገንቢ ሚና የመጫወት ሙከራ የማድረግ እድል አይኖራትም። »የብሪክስ ጉባኤ በጁሐንስበርግ-ደቡብ አፍሪቃ

የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች በጎርጎሮሳዊው ነሐሴ 2203 ዓ.ም.ጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ በተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ።ከግራ ወደ ቀኝ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳሲልቫ ፣የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ ፣ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰግየቭ ላቭሮቭ ምስል GIANLUIGI GUERCIA/AFP


ራማፎሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በእሥራኤል ወታደራዊ ዘመቻ ወቅት የእሥራኤል አመራር እጅግ በርካታ ህዝብ በሚገኝበት በጋዛ በሀማስ ላይ የሚወስደውን እርምጃ ክፉኛ ተችተዋል። ራማፎሳ በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋርበኢንተርኔት ባካሄዱት ጉባኤ ላይ ራማፎሳ እሥራኤል በፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሕገ ወጥ ኃይል በመጠቀም የምትፈጽመውን የጅምላ ጥቃት የጦር ወንጀል ሲሉ ገልጸዋል። በጋዛ ነዋሪዎች ላይ ሆነ ተብሎ ይፈጸማል ያሉት የመድኃኒት የነዳጅ የምግብ እና የውኃ አቅርቦት ክልከላንም ከዘር ማጥፋት እርምጃ ጋር የሚስተካከል ነው ብለዋል። እሥራኤልን የሚደግፉ ድርጅቶች የደቡብ አፍሪቃን መንግሥት ውሳኔ በእጅጉ ተቃውመዋል።
ከመካከላቸው አንዱ በደቡብ አፍሪቃ የፅዮናዊ ፌደሬሽን የፖሊሲ ጉዳዮች ሃላፊ ቤንጂ ሹልማን ናቸው እርሳቸው እንደሚሉት የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት በእሥራኤል ሰብዓዊ መብቶቿን የማስጠበቅ መብት ላይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆም ሞግቷል።

የኤ.ኤን.ሲ ሊቀ መንበርና የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እሥራኤል ፍልስጤም ውስጥ የምትፈጽመው የጦር ወንጀል ነው ብለዋል። ምስል SIPHIWE SIBEKO/REUTERS


« የደቡብ አፍሪቃ ፅዮናዊ ፌደሬሽን እሥራኤል በጽንፈኛው የሀማስ ድርጅት ላይ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የምታካሂደውን የመከላከል ጦርነት መቀጠሏን እንደግፋለን። ሀማስ ሴቶችን ህጻናትን እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተፈጸመባቸው ግፍ የተረፉ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ዜጎች የሚገኙባቸውን 240 ሰዎች አግቷል።»የደቡብ አፍሪካ የዲፕሎማሲ አጣብቂኝ እና የሱዳን ስደተኞች ቀውስ በቻድ
ሆኖም የፖለቲካ ተንታኙ ክዋንዳሌ ኮንድሎ ደቡብ አፍሪቃ የእሥራኤልን ጉዳይ ወደ ICC እንዲተላለፍ በማድረጓ ተስማምተዋል። «ደቡብ አፍሪቃ የዚህ ድርጅት አባል ሆና እስከቀጠለች ድረስ ጉዳዩን የማታስተላልፍበት ምክንያት አይኖርም። ይህ ICC እውነተኛ ተቋም፣ ዓለም አቀፍ የፍትህ ተቋም መሆኑን ማሳየት የሚችልበት ወቅት ነው።»


አንዳንድ ታዛቢዎች ደቡብ አፍሪቃን መንታ አቋም የያዘች ሲሉ ይተቿታል። ሀገሪቱ ባለፈው ነሐሴ የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤን በጆሀንስበርግ ባስተናገደችበት ወቅት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሚካፈሉ ከሆነ የእስር ማዘዣ እንድትቆርጥ በICC ተጠይቃ ነበር።ሆኖም ያኔ መንግሥትና ገዥው የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክርቤት ፓርቲ እርስ በርስ የሚፃረሩ መግለጫዎችን ሲያወጡ ሌሎች ደግሞ ሀገሪቱ ከICC አባልነት እንድትወጣ ጥሪ አቅርበው ነበር። በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓመተ ምህረትም ICC የእስር ማዘዣ የቆረጠባቸው የያኔው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦመር አል በሽር በጆሀንስበርጉ  የአፍሪቃ ኅብረት ጉባኤ ላይ ሲገኙም ተመሳሳይ ውዝግብ ተነስቶ ነበር  ።
ኬት ሄርሲን
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW