1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃትና ግፊት እየተደረገባቸዉ ነዉ

ሐሙስ፣ ኅዳር 19 2017

ከዚሕ ቀደም የተበታተነና የወርሮ በሎች የነበረዉ ጥቃት፣ዘረፋና ጫና አሁን የተደረጃ መልክና ባሕሪ እየያዘ፣ በዉጪ ሰዎች ጥላቻና ከሐገር በማስወጣት ላይ ያነጣጠረ ነዉ።አርቲስ በላይ አዳነ የተባበሩት የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ እንዳለዉ ጥቃቱ በመላዉ ደቡብ አፍሪቃ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ላይ በተደጋጋሚ ይሠነዘራል።

የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ማሕበር በደቡብ አፍሪቃ አርማ
የተባበሩት የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ማሕበር በኢትዮጵያዉያን ላይ የሚደረገዉን ጫና ለመቋቋም ከተለያዩ ወገኖች ጋር በመሆን ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታዉቋል

ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጥቃትና ግፊት እየተደረገባቸዉ ነዉ

This browser does not support the audio element.

ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን  ሐገሪቱን ለቅቀዉ እንዲወጡ ተደጋጋሚና የተቀነባበረ ጥቃት፣ግፍትና ጫና እየተደረገባቸዉ መሆኑን አስታወቁ።ለአደጋ የተጋለጡት ኢትዮጵያዉያንና የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ መሪዎች እንደሚሉት ኢትዮጵያዉያኑ ባለፉት ጥቂት ወራት ሱቆቻቸዉ እየተመዘበሩ፣እየተቃጠሉ ወይም እየተዘጉ ነዉ።በቡድን የተደራጁ የሚመስሉት ኃይላት በኢትዮጵያዉያኑ ላይ የሚያደርሱት አካላዊ ጥቃት፣ዛቻና ማስፈራሪያም እበረታ ነዉ።

በስልክ ያነጋገርናቸዉ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉትከዚሕ ቀደም የተበታተነና የወርሮ በሎች የነበረዉ ጥቃት፣ዘረፋና ጫና አሁን የተደረጃ መልክና ባሕሪ እየያዘ፣ በዉጪ ሰዎች ጥላቻና ከሐገር በማስወጣት ላይ ያነጣጠረ ነዉ።አርቲስ በላይ አዳነ የተባበሩት የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ ነዉ።በላይ እንደሚለዉ ጥቃቱ በመላዉ ደቡብ አፍሪቃ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ላይ በተደጋጋሚ ይዘሠነዘራል።አጥቂዎቹ ደግሞ በአብዛኛዉ ዱዱላ የተባለዉ ቡድን አባላት ናቸዉ።

                                     

ፓስተር ሳሚ እንደሚሉት ደግሞ ባለፉት ጥቂት ቀናት ዉስጥ ብቻ በርካታ የኢትዮጵያዉያን ሱቆች ተዘርፈዋል።ከ700 የሚበልጡ ተዘግተዋል።የሰዎች አካል ጎድሏልም።«መጤዉን ጠል የሆኑ ፓርቲዎች ባንዳድ ቦታ 700 ሱቆች ዘግተዋል።ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ የሚሰራበትን።ሱቅ መዝጋት ብቻ አይደለ አካል ማጉደል፣ ሰዎችን መግደል ሁሉ አለበት።»

ፓስተር ሳሚ እንደሚሉት ደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ሱቆችና ሌሎች የንግድ ተቋማት በ21 ቀናት ዉስጥ ሕጋዊ ፈቃድ እንዲያወጡ የሐገሪቱ ፕሬዝደንት ሲርያል ራማፎዛ የዛሬ ሁለት ሳምንት ግድም አሳስበዋል።ይሁንና በደቡብ አፍሪቃ ቢሮክራሲ ፍቃድ ለማዉጣት ሶስት ሳምንት አይደለም አመትም አይበቃ።በዚሕም ምክንያት  መግለጫዉ ኢትዮጵያዉያኑን ከሥራ ለማፈናቀል፣ ከሐገር ለማባረርና ጥቃቱን ለማባባስ ያለመ ነዉ።-እንደ ፓስተር ሳሚ

ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2019 በዉጪ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት፣ ዘረፋና ድብደባ ደርሶ ነበርምስል Getty Images/AFP/M. Spatari

                            

አርቲስ በላይ አዳነም ከጥቃቱ ጀርባ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት ሹማምንታት እንዳሉበት ይናገራል።በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተዘዋዋሪ መንገድም ቢሆን ጥቃት፣ ዘረፋና ግፊቱን ለማስቆም ከኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ጋር ሆኖእየጣረ መሆኑን አርቲስት በላይ አስታዉቋል።ፓስተር ሳሚ በበኩላቸዉ የዙሉ ንጉስን ጨምሮ የተለያዩ ወገኖችና ተቋማት ጥቃቱን እንዲያስቆሙ ለማግባባት ኢትዮጵያዉያን ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስታዉቀዋል።በቅርቡ ታላቅ የአደባባይ ሰልፍ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።ፓስተሩ እንዳሉት ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ወደ አንድ ሚሊዮን ይገመታል።

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW