1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ የመሰረተችው ክስ

ረቡዕ፣ ጥር 1 2016

ኔዘርላንድስ ዘ ሄግ የሚገኘው የአለም ፍርድ ቤት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ አይሲጄ ነገና ከነገ ወዲያ ደቡብ አፍርካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ ይመለክታል። እስራኤል ግን በጋዛ የምታክሂደው ዘመቻ በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሃማስን በዜጎቿ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጽም ለመካላከልና ለማጥፋት ነው በማለት ነው የምትከራከረው።

ደቡብ አፍሪቃ፣ እስራኤል በፍልስጤሞች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅማለች በማለት ከሳለች
ዘ-ሔግ ኔዘርላንድስ የሚያስችለዉ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪቃ በእስራኤል ላይ የተመሰረተቺዉን ክስ ያዳምጣልምስል Peter Dejong/AP Photo/picture alliance

የደቡብ አፍሪቃ ክስ እና እስራኤል ነገ በዘሄግ

This browser does not support the audio element.

 

ኔዘርላንድስ ዘ ሄግ የሚገኘው የአለም ፍርድ ቤት  በእንግሊዝኛ ምህጻሩ አይሲጄ ነገና ከነገ ወዲያ ደቡብ አፍርካ በእስስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ ይመለክታል።  ደቡብ አፍርካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችው ክስ፤ በራሷ በእስራኤል፤በአሜሪካ፤ ብርታኒያና  የአውሮፓ ህብረት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሀማስ፤ መስከረም 26 ቀን  በሰላማዊ የስራኤል ዜጎች ላይ የፈጽመውን ግድያና ጠለፋ ተከትሎ፤ እስራኤል በጋዛ በክፈተችው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ እርምጃ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ  በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ይህንን ወንጀል ባስቸኳይ እንዲያስቆም የሚጠይቅ ነው።ደቡብ አፍሪቃ ከእሥራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ማቋረጧ ያስከተለው ድጋፍና ተቃውሞ ካንድ ሳምንት በፊት  በ84 ገጽ ተሰንዶ የቀረበው የደቡብ አፍርካው ክስ፤ ባለፉት ሶስት ወራት እስራኤል  በጋዛ  ነዋሪዎች ላይ የፈጸመችቸውን የግድያ፣ የአየር ድብደባ፣ የማፈናቀልና መጠለያ የማሳጣት፤ የመሰረታዊ ፍጆታዎች ክልከላን ያካተቱቱ ኢሰባዊ ድርጊቶችንና ወንጀሎችን፤  እንዲሁም በእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣኖች የተሰጡ  ጥላቻን የሚቀሰቅሱና የዘር ማጥፋት ወንጀልን እንዲፈጸም የሚያነሳሱ  መግለጫዎችናና ንግግሮችን  የያዘ ነው ነው ተብሏል።

የእስራኤል መቃወሚያ

እስራኤል ግን በጋዛ የምታክሂደው ዘመቻ በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሃማስን በዜጎቿ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጽም ለመካላከልና ለማጥፋት ነው በማለት ነው የምትከራከረው። የኢስራኤል ቃል አቀባይ ሚስተር  ኤይሎን ሌቭይ በዚህ ጉዳይ በሰጡት ስተያየት ደቡብ አፍርካን ክፉኛ ነቅፈዋል።   “ደቡብ አፍርካ የሃማስን ድርጊት በመሸፋፈን የወንጀሉ ተባባባሪ ሁናለች ።ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኖች መዳኛ ፍርድ ቤት በሩሲያ ላይ ክስ ለመመስረት ምርመራ ጀመረ

በክሱ ላይ የተሰሙ ድጋፍና ተቃውሞዎች

ደቡቡ አፍሪካ በእስራኤል ላይ የመሰረተችውን ክስ  በርካታ በመካከለኛው ምስርቅ፣ ኢስያና ላቲን አሜርካ የሚገኙ አገሮች የደገፉት ሲሆን ፤ ያውሮፓ አገሮች ግን ባብዝኛው ዝምታን መምረጣቸው ነው የሚነገረው። አሜሪካ፤ በቃል አቀባይ ጆን ኪርቢይ በኩል ክሱን መሰረ ቢስና መረጃ ሊቀርብበት የማይችል ስትል አጣጥለዋለች።

የዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት-ዘ ሔግ ኔዘርላንድስ ምስል Peter Dejong/AP Photo/picture alliance

 

ደቡብ አፍርካ ለምን ግምባር ቀደም የእስራኤል ከሳሽ ሆነች

ደቡብ አፍሪካ በግምባር ቀደምነት በእስራኤል ላይ ይህን ክስ የመሰረተችበትን ምክኒያት፤ አንዳንዶች ገዝው የደቡብ አፍርካ ኤኤንሲ ፓርቲ በትግሉ ወቅት ከፍስልጤሞች ጋር ከነበረው ግንኝነት ጋር ቢያገናኙትም፤ በፕሪቶሪያ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፊሰር የሆኑት ዶክተር ሲቴምቢሌ ምቢቴ ግን የተፈጸመው ግድያና የደረሰው ግፍ ከፍተኛ  በመሆኑንና ይህን ለማስቆም የሚደርገው ጥረትም አንስተኛ በመሆኑ ምክኒያት እንደሆነ ነው የሚናገሩት፤ “ ከኦክተበር  7 ጀምሮ በጋዛ የደረሰው በግልጽ የሚታይ ነው። የሞቱት ሰዎች ቁጥር ብዛት ብቻ ሳይሆን እስካሁን ከሞቱ ከ22 ሺ በላይ ሰዎች ግማሺ ያህሉ ህጻንት መሆናቸው አስደንጋጭ ነው፡፤ በዚያ ላይ እስካሁን በመንግስታቱ ድርጅት በኩልም ይሁን በሌላ  አንድም ድርጊቱን ለማስቆም የቻለ የለም  በማለት የደቡብ አፍርካው እንቅስቃሴ  በፍርድቤቱ በኩል ይህን ወንጀል ለማስቆም የተደረገ ጥረት መሆኑን ገልጸዋል።።የእሥራኤልና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት

የሚጠበቅ ውስኔ

ፍርድ ቤቱ በነገና ከነገ ወዲያ ውሎው የየሁለቱንም ወገኖች የመከራእክሪያ  ሀሳቦች አዳምጦ በሚቀጥሉት አንድና ሁለት ወራት ውሳኔ እንደሚሰጥ ነው የሚጠበቀው።፡ ውሳኔው ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መናገር ባይቻልም እየተፈጸመ ያለው ወንጀል እንዲቆም  የሚጠይቅ ማዘዣ ሊወጣ እንደሚችል ግን ይጠበቃል። አሜሪካዊው የሰባዊ መብት ጠበቃ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ቦይሌ  እንደሚሉት የቀረቡት መረጃዎችና ማስረጃዎች ደቡብ ፍርካን እንድታሸነፍ የሚይደርግ ነው። “የቀረቡትን መረጃዎች  እንደመረመርኳቸው ከሆነ፤ ደቡብ አፍርካ የምታሸንፍ ይመስለኛል። ይህ ከሆነ ደግሞ እስራኤል ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብ የሚጠይቅ ትዛዝ ሊተላለፍ ይችላል ብለዋል።

የውስኔው ተግባራዊነት አጠራጣሪነት

ሆኖም ግን የፍርዱንም ሆነ የሚወጣውን ትዛዝ ተፈጻሚነት ብዙዎች ይጠራጠራሉ። ፍርድ ቤቱ ከዚህ  በፊት በሌሎች  ላይም ሆነ በራሷ በእስራኢል ላይ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ አለመሆናቸውን የሚጠቅሱ ወገኖች ከዚህም የየለየ ነገር መጠበቅ እንደማያቻል ነው የሚናገሩት።

ገበያው ንጉሴ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW