1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ደብረወርቅ ከተማ በተደረገ ዉጊያ 10 ሰዉ ተገደለ፣ ከተማይቱ ዛሬ ተረጋግታለች

ኢሳያስ ገላው
ማክሰኞ፣ ኅዳር 8 2019

በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል በአካባቢው ይህን መሰል ግጭት ከተካሄደ ከ11 ወራት በላይ ተቆጥሯል ያሉት አስተያየት ሰጭም ትናንት ግን በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጦርነት እንደነበር ይናገራሉ፡፡

ከምሥራቅ ጎጃም አካባቢዎች አንዱ
ከምሥራቅ ጎጃም አካባቢዎች አንዱምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

ደብረ,ወርቅ ከተማ በተደረገ ዉጊያ 10 ሰዉ ተገደለ፣ ከተማይቱ ዛሬ ተረጋግታለች

This browser does not support the audio element.

 

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በናርጅና እናውጋ ወረዳ ደብረወርቅ ከተማ ትናንት ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል ጦርነት መካሄዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡በዉጊያ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።የደብረወርቅ ከተማ ከትናንቱ ድባብ ወጥታ  ዛሬ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መሄዳቸውንና መደበኛ ኑሮ መቀጠሉን የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

"በጣም ከባድ፣ በጣም ከባድ ነበር አሁን በቃ ለመድነዉና ትናንት ሁሉ ነገር ዝግትግት አለ ጥቁር ቀን ሆነ ዛሬ ሁሉም ወደየስራው የሚያልፍበት  አለፈበት ወደ መደበኛው እንጂ እነሱ ወጡ በቃ አለቀ ብዙ ሰዉ ተጎድቶል መጥፎ ነበር በጣም፡፡
በጣም ከባድ ከባድ አይገልፀዉም  የሚገርመው ከተማው ሙሉ ጩኸት ነበር ፉከራ ነው የምትሰማ ምንድነው የሚሆነው ጭንቀት ሁሉ ነበር ፖሊስ ጣቢያው ላይ ቦምብ ይጣላል በቃ የምትሰማው ድምጽ መፎከር  አይነት ነው በጣም ይረብሽ ነበር፡፡"

የነዋሪዎች ስነ-ልቦናዊ ስጋት እና የዕለት ተዕለት ኑሮ ተጽዕኖ

ጦርነቱ ከባድ እንደነበር የገለጹት ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ማህበረሰቡ ምንም እንኳን ዛሬ ወደ ስራ ቢመለስም መረጋጋት እንዳልቻለ ነው የሚናገሩት፡፡

"በጣም ከባድ ነበር አዎ 11 ሰዓት ነው የተጀመረው ወጊያዉ   ከባድ ነበር ሲነጋ ከ 1 ሰዓት በኃላ  ነው ወጥተው ሄዱ ለሁለት ሰዓት ያክል በጣም ከባድ ነበር፡፡ ነገርስ እንዲህ እኛስ ሞች አይደለን በሚለው አሁን እጅግ በጣም ቆዝሞ ተሸማቆ ነው እስከ ዛሬም ትናንትናም ማለት ነው ዛሬም ወደ ስራ ቦታ ሄድን እንጂ ተሸማቆ ለስራ ጠዋት ራስ ወጥቶ ለሚሄ  ለአጨዳ ምናምን ሲሄድ ቀን አለ መስሎህ እኮ ነው ምናምን እስከማለ ይሄ ቃል አሁን ከፍተኛ ስነልቦና ነው የሚጎዳን በንዲህ አይነት ሁኔታ በር በጮህ ቁጥር እኮ አሁንም ተተኩሰ ይላል ሰው፡፡"

ትናንት በአካባቢው የተከሰቱ  ግጭቶች እና ወቅታዊ ሁኔታ

በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል በአካባቢው ይህን መሰል ግጭት ከተካሄደ ከ11 ወራት በላይ ተቆጥሯል ያሉት አስተያየት ሰጭም ትናንት ግን በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጦርነት እንደነበር ይናገራሉ፡፡

"ከአንድ ዓመት ሊሞላ ነው የሚገርምህ ታህሳስ 7 ነበረ ከዚህ በፊት በጣም መጥፎ የነበረ እንጂ  ዓመት ሊሞላው ምንም አልቀረውም ነበረ፡፡
ትናንት የዚህንኑ ዉጥረት ለመጨምር በዙሪያው በሸበል በረንታ እናማይ የሚባል አለ ብቻና የዶሀ ምናምን አጋጣሚ ካወቅካቸው እነሱ እነሱ ላይ ወደዚህ እንዳይመጣ ለማድረግ አይነት ቀለልም ቢል ነበረ አጎራባች ወረዳው ቀላል ነበር እንጂ ነበረ ቢቸናም ነበር ሸበል በረንታ የምትባለች የዶሀ አካባቢ ነበረ ያው አስቸጋሪው በጣም የከፋዉ ይሄ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን ምንም የሰማሁት የለም፡፡"

ፎቶ ከክምችት።የፋኖ ታጣቂምስል፦ Solan Kolli/AFP/Getty Images

በደብረወርቅ ከተማ ትናንት በነበረው ጦርነት ከ10በላይ ሰዎችን ቀብረናል ያሉት የአካባቢው ነዋሪም ትናንት አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፈናል ብለዋል፡፡

"ሞት መቼም  ምን ያህል ጭንቀት እንደሚፈጥር ታውቃለህ በጣም ቆዝመን በ ስራ ሁሉ ያው ትምህርት የለም ነበረ ተዘግቶ ነዋ ያለ ያው በዚህ ሁኔታ እጅግ በጣም ከባድ ነበረ የዛ ሁሉ ቤተሰብ ሲሮጡ ሲያለቅሱ ምናምን ስታይ ሌላ ስሜት ነው የሚፈጥርብህ ሌላም ቦታ ይሄዱ ሌላም ወረዳ አሉ  ቤተሰቦቻቸው ሌላ ቦታ የተነሳ አስከሬን  አለ እንጂ ደብረወርቅ ተቀብሮል  እስከ 13 አካባቢ ይመስለኛል እና ሌላም ቦታ ይሄዳሉ ፡፡"

      ከቤት ያልወጣ ሀዘን

ባለፈው ሶስት ዓመታት በአካባቢው የነበረው ጦርነት ማህበረሰቡን በእጅጉ ጎድቶታል ያሉት አስተያየት ሰጭም ግጭቱ ለእጅግ ከፍተኛ ቀውስ እንዳዳረጋቸው ይናገራሉ፡፡

"ምን ያልተጎዳ አለ በእናትህ አሁን የሰነልቦናውን የመጀመሪያውን ያዝልኝ አንደኛ የምታጣው ሲሞቱ የሚገርምህ ከዚህ በፊት ከፋኖም   ሲሞት እዚሁ ነዉ  ለቅሶ የምትቀመጥ መርዶው እዚሁ ነዉ  ከነዚህ ሲሞት ቀባሪውም  እዚህ ነው እና የመጀመሪያዋ የስነልቦና ጉዳት አለ በዚያ ላይ አሁን ተኩስ ሲሰማ ወደዚያም ወደዚህም የሚገባዉ ጨምሮል የእናቶች ቤተሰቡ ጭንቀት ከዚያ ላይ ስራ አጥነት  መጨምር ቀውሱ ብዙ ነው ፡፡"

ትናንት ከረፈደ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ መረጋጋት የተመለሰችው ደብረወርቅ ከተማ ዛሬ በሰርክ እንቅስቃሴዋ ላይ ትገኛለች፡፡

ኢሳያስ ገላዉ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

Edited by: Negash Mohammed ነጋሽ መሐመድ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW