ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ መሥራች ጉባኤውን በቅርቡ መቐሌ ላይ እንደሚያደርግ አስታወቀ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 23 2017
የትግራይ ሕዝብ "የተለየ መንገድ" ስለሚያስፈልገው እና አሁን በክልሉ ያለው ችግር "በነበረበት መንገድ የሚፈታ" ባለመሆኑ መቋቋሙን በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የተባለው ፓርቲ ገለፀ።
ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘቱን የጠቀሰው ፓርቲው "ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ ችግር ሊፈታ የሚችልበት አቅም ስለሌለው" አዲስ ያለውን አስተሳሰብ ይዞ ሙምጣቱንም ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል።
የቀድሞዉ የትግራይ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት የሚመሩት የህወሓት አንጃ አዲስ ፓርቲ መሰረተ
ፓርቲው "የለውጥ ሀሳብ" ያላቸው የተባሉ የቀድሞ የሕወሓት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመሮችን ጨምሮ በ100 ሰዎች መመስረቱም ተገልጿል። ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) የተባለው ክልላዊ የፖለቲካ ድርጅት ትግራይ ክልል ውስጥ አሁን ተጋርጧል ያለውን "የሰላም፣ የፍትሕ፣ የመልካም አስተዳደር" እጦት ለመፍታት፣ የአዲሱን ትውልድ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ አማራጭ ሆኖ መቅረቡን የፓርቲው የሚዲያ እና የኮሚዩኒኬሽን አስተባባሪ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ዛሬ አዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል ውስጥ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
የቀድሞ የሕወሓት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመሮች ጭምር በመስራችነት የተሳተፉበት ይህ ድርጅት በሕወሓት ውስጥ ሆነው የለውጥ ኃይልን የደገፉትን፣ ወጣቶች እና ምኁራንን በማሳተፍ ከክልል እስከ ቀበሌ አደረጃጀት እና የአባላት ምልመላ በቅርቡ እንደሚያደርግ፣ ከ1 እስከ 1 ወር ተኩል መቀሌ ላይ መስራች ጉባኤውን እንደሚያደርግም ገልጿል። ከመሥራቾቹ መካከል የተወሰኑት ትግራይ ውስጥ የደኅንነት ሥጋት ያለባቸው መሆኑንም አቶ ረዳዒ አስታውቀዋል።
በአፋር ክልል ወደ ትግራይ የሚሄዱ የጭነት መኪናዎች ኬላዎች ላይ ተዘግተዋል።
ስምረት "የሰዎችን ነፃነት እና መብት የሚያረጋግጥ" እንደሚሆን የተናገሩት አቶ ረዳዒ በስም ያልጠቀሷቸውን አራት የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የችግሮች ሁሉ ምንጭ አድርገው ከሰዋል። በእነዚህ ሰዎች ከኤርትራ መንግሥት ጋር የሚደረግ ያለት ግንኙነት "ጦርነት ሊቀሰቅስ" እንደሚችልም ጠቅሰዋል።
ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ