1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዳግም አሳሳቢ ሁኔታን ለደቀነው ኮቪድ የክትባት ዘመቻ

ዓርብ፣ ሰኔ 3 2014

በኢትዮጵያ 70 በመቶ ህዝብ የኮሮና ተዋሲ ስርጭትን የሚገታው ክትባት ለማዳረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ እንዳመለከተው፤ ትናንት በተጀመረው ሶስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ተዋሲ ክትባት ዘመቻ በ10 ቀናት ውስጥ 25 ሚሊየን ዜጎችን በክትባት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

Äthiopien | Addis Abeba | Dereje Duguma | Pressekonferenz des Gesundheitsministeriums
ምስል Seyoum Getu/DW

3ኛዉ ዙር የክትባት ዘመቻ እስካሁን ምንም ክትባቱን ባላገኙ ላይ ትኩረት ሰጥቶአል

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ 70 በመቶ ህዝብ የኮሮና ተዋሲ ስርጭትን የሚገታው ክትባት ለማዳረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፤ ትናንት በተጀመረው ሶስተኛ ዙር የኮቪድ-19 ተዋሲ ክትባት ዘመቻ በ10 ቀናት ውስጥ 25 ሚሊየን ዜጎችን በክትባት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ዓለማ ላ ሌላኛው የወረርሽኝ ስጋት የደቀነው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ አለመግባቱንና እንዳይገባም የጥንቃቄ ምርመራዎች በሰፊው በየኬላው እየተደረጉ መሆኑን አመልክቷልም፡፡

ነጂብን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አግኝቼ ባነጋገርኩበት ወቅት ነው አስተያየቱን የሰጠኝ፡፡ ከነጂብ አስተያየት በተቃራኒ የኮቪድ ክትባትን ለመውሰድ በርካታ ስጋትና አስተያየቶችን በመደርደር እምብታቸውን የሚገልጹም ቁጥራቸው የዋዛ አይደለም፡፡ በተለይም ወረርሽኙ ከባለፉት ጥቂት ሳምንታት በፊት የመቀነስ አዝማሚ ማሳየቱ የጥንቃቄ ጉድለትንም ጭምር ያስከተለ ነበር፡ ይሁንና በኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን ስጋት ወደ መሆን የመጣው ወረርሽኙ ባሁን ጊዜ 12 ሰዎችን በፅኑ ህክምና መስጫ ክፍል ውስጥ ማስተኛቱ ነው የሚነገረው፡፡ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተውም በተለይም ባለፉት አራት ሳምንታት ቀስ በቀስ የኮቪድ-19 ተዋሲ ለሆስፒታል የሚያደርሳቸው ሰዎች ቁጥር ከፍ እያለ ነው ብሏል፡፡ በዓለማቀፍ ደረጃ 12 ቢሊየን ዶዝ የኮቪድ መከላከያ ክትባት ሲሰራጭ ሙሉውን ዶዝ የወሰዱ በ3 ቢሊየን ገመታሉ፡፡ ባደጉ አገራት ከ70 በመቶ የላቀ የማህበረሰብ ቁጥር ክትባቱን ስለመውሰዳቸውም ነው የሚነገረው፡፡ በኢትዮጵያ የተዋሲው ስርጭት አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ከፍ ማለቱን ተከትሎ እስካሁን ለ24 ሚሊየን ዜጎች ብቻ ተዳርሶ የነበረው ክትባት በትናንትናው እለት ሶስተኛ ዘመቻው መከፈቱን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡ 

ምስል Seyoum Getu/DW

ትናንት በተጀመረውና ለአስር ቀናት ይቆያል በተባለው 3ኛ ዙር የክትባት ዘመቻ እስካሁን ምንም ክትባቱን ያላገኙ ዜጎች ዋነኛ ትኩረት ሲሆኑ አንድ ዙር የተከተቡ ሙሉ ዶዝ እንዲወስዱ እንዲሁም ሙሉ ዶዝ ወስደው 6 ወራት የሞላቸው የማጠናከሪያ ዶዝ እንዲወስዱም ይሰራል ተብሏል፡፡ በዚህ 10 ቀናት 25 ሚሊየን ዜጎችን ለመከተብ እቅድ መያዙም ተነግሯል፡፡ በመላው አገሪቱ በየትኛም ጤና ጣቢያ ክትባቱ እንደሚሰጥ ያመለከቱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዓለማውም ሶስት ነው ብለዋል፡፡  የኮሮና ተዋሲ በጎርጎራውያኑ 2019 በቻና ሁዋን ግዛት ከተከሰተ ወዲህ በዓለም ከ530 ሚሊየን ህዝብ በላይ በወረርሽኙ ተጠቅተው 5.3 ሚሊየን የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በኢትዮጵያ ደግሞ እስካሁን 477 ሺህ ሰዎች በተዋሲው ተጠቅተው፤ ከ7 ሺህ 500 በላይ የመሆኑት በተወሲው ጦስ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ 
ኂሩት መለሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW