1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ግጭች ተግዳሮት የሆኑበት የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ

ሰኞ፣ ነሐሴ 29 2015

በኢትዮጵያ ድህረ ኮቪድ-19 ወረርሽን በኢትዮጵያ ተስፋፍቶ የቆየው ግጭት ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ፈተና ሆኖ መቆየቱ እየተነገረ ነው። እንደ ባለሙያዎች አስተያየት በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ ባለው አቅም ልክ መሥራት ቢቻል የቱሪዝምና መስተንግዶውን ዘርፍ ከግብርና ቀጥሎ ትልቁ የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ ይቻላል።

ፎቶ፤ የአባይ ድልድይ
በኢትዮጵያ ድህረ ኮቪድ-19 ወረርሽን በኢትዮጵያ ተስፋፍቶ የቆየው ግጭት ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ፈተና ሆኖ መቆየቱ እየተነገረ ነው። ፎቶ፤ የአባይ ድልድይምስል Seyoum Getu/DW

ግጭች ተግዳሮት የሆኑበት የቱሪዝም ዘርፍ

This browser does not support the audio element.

 

በኢትዮጵያ ድህረ ኮቪድ-19 ወረርሽን በኢትዮጵያ ተስፋፍቶ የቆየው ግጭት ለሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ  ፈተና ሆኖ መቆየቱ እየተነገረ ነው። እንደ ባለሙያዎች አስተያየት በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ ባለው አቅም ልክ መሥራት ቢቻል የቱሪዝምና መስተንግዶውን ዘርፍ ከግብርና ቀጥሎ ትልቁ የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ ይቻላል።

ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን በአዲስ አበባ ከተማ የሆቴል ባለቤትና የሆቴል ባለንብረቶች ማሕበር ሰብሳቢ ናቸው። በሙያው ከተሰማሩ ረጅም ጊዜ መቆጠሩን የሚገልጹት ወ/ሮ አስቴር ከቱሪዝም ጋር ጠንካራ ቁርኝት ያለው የሆቴሉ ዘርፍ ከዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ ማግሥት በአገሩቱ ተደጋግሞ በሚስተዋለው ግጭት ክፉኛ መፈተኑን ያስረዳሉ።

እንደ ባለሙያዎች አስተያየት በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ ባለው አቅም ልክ መሥራት ቢቻል የቱሪዝምና መስተንግዶውን ዘርፍ ከግብርና ቀጥሎ ትልቁ የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ ይቻላል። ፎቶ፤ የቢሾፍቱ ሐይቅ ባባጋያምስል Seyoum Getu/DW

«ሰው እንደ ልቡ ካልተንቀሳቀሰ ወደ አገሪቱ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይገታል፡፡ ያለውን ችግር አጋኖ የማውጣት ነገርም ይስተዋላል፡፡ ይህ ነው ለኢንደስትሪው ከፍተኛ ተግዳሮት የደቀነው» ይላሉ። በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በአማካሪነት ተሰማርተው ከ25 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ በተለያዩ ሃገራት ከ50 በላይ ሆቴሎችን በማደራጀት ወደ ሥራም በማስገባት በርካታ ሥራዎችን የሠሩ ባለሙያ አቶ ፍስሐ አስረስ በፊናቸው ከኮቪድ ማግስት ዓለም ላይ ሃገራት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ እያገገሙ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አሁንም ያላባራው ግጭት እንቅፋት ሆኖ ቀጥሏል ባይ ናቸው። «ሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ድንጉጥና ጥንቃቄን የሚፈልግ ዘርፍ ነው። ከኮቪድ ማግስት በአገራችን በተከሰተው ግጭት ሃገራት ገደብ መጣላቸው ሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን ክፉኛ ፈትኗል። ከዚህ የተነሳ ሆቴሎች አሁንም ድረስ ወጪያቸውን እንኳ ለመሸፈን ከፍተኛ ፈተና ውስጥ ናቸው።» ነው የሚሉት።በኦሮሚያ የቱሪዝም ዘርፍ እና ተግዳሮቱ

ባለሙያው እንደሚሉት ኢትዮጵያ ያላት የቱሪዝም ጸጋ ግን ምናልባትም ከግብርናው በመቀጠል ትልቁ የኢኮኖሚ አመንጪ ዘርፍም ነው። በሆቴል ኢንቨስትመንት የተሰማሩት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞንም አሁንም ቢሆን አገሪቱ በቱሪዝም ዘርፍ ካላት አቅም አንጻር የሰላም ችግሩ ከተወገደ ተስፋው ብሩህ ነው ይላሉ።  «ትልቁ ነገር ያለንን መስህብ ማስተዋወቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብን» ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

በሆቴል ኢንቨስትመንት የተሰማሩት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞንም አሁንም ቢሆን አገሪቱ በቱሪዝም ዘርፍ ካላት አቅም አንጻር የሰላም ችግሩ ከተወገደ ተስፋው ብሩህ ነው ይላሉ።  «ትልቁ ነገር ያለንን መስህብ ማስተዋወቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብን» ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ፎቶ፤ የአዲስ አበባ ከፊል ገጽታምስል Seyoum Getu/DW

ኢትዮጵያ በጊዜ ያልተገደበ የቱሪስቶች መዳረሻ አገር እንድትሆን በመንግሥት ደረጃ መዳረሻ አማራጮችን በማስፋት ከዘርፉ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ለማግኘት በትኩረት ተሠርቷል ያሉን ደግሞ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲለሺ ግርማ ናቸው።የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታ ኮቪድና ግጭት ዘርፉን ፈትነውት መቆየታቸውን ያልሸሸጉት አቶ ግርማ በኢትዮጵያ ወርኃ መስከረም ከየትኛውም ወቅት በተሻለ በቱሪስቶች የሚመረጥ እንደመሆኑ አሁን ካለው የጸጥታ ተግዳሮት ጎን ለጎን አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው የአገሪቱ አከባቢዎች ለጎብቢዎች ዝግጁ ሆነው እንዲጎበኙ በአንክሮ መሠራቱን ገልጸውልናል፡፡ ከዓለም አቀፍ ቱሪስቶች በተጨማሪ በተስፋፉ መዳረሻዎች የአገር ውስጥ ጎብኒዎችም ለጉብኝት በመጋበዝ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ጥረት እንደሚደረገም ሚኒስትር ዴኤታው አክለው አብራርተውልናል።

ሥዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW