ድላሚኒ ዙማ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽነር
ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2005![](https://static.dw.com/image/16099599_800.webp)
ማስታወቂያ
ከቀድሞው አቻቸው ተሰናባቹ ዣን ፒንግ ስልጣኑን የተረከቡት ድላሚኒ ዙማ በአፍሪቃ ኅብረት ትልቅ ኃላፊነት እንደሚጠብቃቸዉ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።
ከእሳቸዉ አስቀድሞ በኃላፊነት ላይ የነበሩትን ለጥረታቸዉ በማመስገንም በማሊ፤ ሱዳንና ሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋ በመተባበር ለማስወገድ እንደሚሠሩ አመልክተዋል፤
«ስለዚህ ጥረታችንን አሰባስበን በማሊና ሳህል አካባቢ ያሉ ግጭቶችን ለማስወገድ እንጥራለን። እስካሁን ችግሩን ለማስወገድ እየሞከሩ ካሉት ከተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት እና ከአካባቢዉ ድርጅት ECOWAS ጋ በቅርበት ለመስራት እንሞክራለን። ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን እንዲረዳም ለአፍሪቃ ከፍተኛ የሽምግልና መድረክም አስፈላጊዉን ድጋፍ መስጠታችንን እንቀጥላለን።»
በአፍሪቃ ኅብረት ታሪክ ሴት ከፍተኛ የመሪነት ስልጣን ስትይዝ ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ የመጀመሪያዋ ናቸዉ። ዙማ ሀገራቸዉ ደቡብ አፍሪቃን በዉጭ ጉዳይና በአገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።
የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ በአፍሪቃ ህብረት የተካሄደውን የስልጣን ርክክብ ስነ-ስርዓት ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ