ድሬዝደን የዛሬ 75 ዓመት እና ዛሬ
ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2012ማስታወቂያ
የዛሬ 75 ዓመት በተባበሩት ኃይሎች የቦምብ ውርጅብኝ የተንኮታኮተችው የጀርመኗ ድሬዝደን ከተማ ዛሬ አንሠራርታ ስትታይ ያንን ሁሉ ሰቆቃ ያለፈች አትመስልም። ሆኖም ዛሬም ግን የጦርነቱ ጠባሳ በቀላሉ እንዳይዘነጋ ጥልቅ ማስታወሻ የተቀመጠባት በመሆኗ ያለፈ ታሪኳን የምታሳይበት ቤተመዘክር በከተማዋ ማዕከል ተሸክማለች። ያኔ የጦር እስረኛ የነበረው አሜሪካዊ ታሪክ ፀሐፊ ኩርት ቮንጉት «ስሎውተር ሃውስ ፋይቭ» በተሰኘው መጽሐፉ ከቦምብ ድብደባው በኋላ የድሬዝደን ከተማ «የጨረቃን ገጸ ምድር መሰለ» ሲል የጻፈው አገላለጽ በብዙዎች ይጠቀስለታል። በእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ዘንድም ከፍተኛ ቃጠሎን ለመግለፅ «እንደ ድሬዝደን» የሚለውን አባባል መጠቀም የተለመደ መሆኑን የሚያስረዱ ሌሎች ጽሔፎችም አሉ። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በተቃረበበት በዚያን ወቅት በምሥራቅ ጀርመኗ ግዛት ድሬዝደን ከተማ ላይ የወረደው ቦምብ 25 ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ፈጅቶ፤ 25 ሺህ ገደማ ቤቶችንም አውድሞ ከተማውን ወደፍርስራሽ ክምርነት መለወጡ ለታሪክ ተመዝግቧል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ