ድሬደዋ: የጭነት መኪና አሽበርካሪዎች ቅሬታ
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 10 2013
ማስታወቂያ
ለDW ቅሬታ ያቀረቡ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ይዘውት የመጡት ጭነት ሳይረገፍ ለረዥም ቀናት በመቆየታቸው ለእንግልት እና ላልተገባ ወጪ መዳረጋቸውን ተናግረዋል ፡፡
የንብረቱ አስመጪ የሆነው ድርጅት መንግስት በፈቀደው የቀረጥ ነፃ ፍቃድ ዕቃውን ማምጣቱንና አሁን የተፈጠረው መስተጓጎል በጉሙሩክ በኩል በአሰራር የተፈጠረ እንደሆነ አስረድቷል፡፡ በመጉለላቱም ንብረቱ እየተጎዳ ይገኛል ብሏል፡፡
የደሬዳዋ ጉሙሩክ መቅረጫ ጣቢያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ስራ አስኪጅ አቶ ደመላሽ በጉዳዩ ላይ ለ DW በሰጡት ምላሽ ችግሩ የተፈጠረው ቅርንጫፉ በሚሰጠው አገልግሎት አሰጣጥ አይደለም ፤ ቀረጥ ነፃን በሚመለከት በፌደራል ደረጃ የወጣውን መመርያ መሰረት አድርጎ ስራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ አስመጭዎቹ እንዲከፍሉ የተጠየቁትን ታክስ እንዲከፍሉ ወይም የገንዘቡን መጠን ተቀማጭ ገንዘብ (ዲፖሲት) አስይዘው እቃውን እንዲያራግፉ እና ቅሬታ እንዲያቀርቡ አማራጭ ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡ ይኸው ተፈፃሚ ካልሆነ ዕቃውን ማራገፍ አስቸጋሪ መሆኑንም ተናግሯል፡፡
መሳይ ተክሉ
ልደት አበበ