1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ድሬዳዋ መሰረተ ልማቶችን እንድታስፋፋ ተጠየቀች

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 21 2015

የኢንደስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል ዝቅተኛ ያሉትን የኢንዱስትሪ ዘርፍ የስራ እድል ፈጠራ ከፍ ለማድረግ መስራት ይገባል ብለዋል።መንግስት ከተማዋ ነፃ የንግድ ቀጠና እንድትሆን ማድረጉን ያነሱት አቶ መላኩ በዚህ እድል የሚመጡ ባለ ኢንዱስትሪዎችን ለማስተናገድ አስተዳድሩ የሆቴል ግንባታ እንዲሁም መሰረተ ልማትን ማሳደግ ይጠበቅበታል ብለዋል።

Äthiopien Dire Dawa
ምስል፦ Messay Teklu/DW

ድሬዳዋ ባለሀብቶችን ለመሳብ መሰረተ ልማቶችን እንድታስፋፋ ተጠየቀች

This browser does not support the audio element.

በድሬደዋ የኢንዱስትሪው ዘርፉ ለነዋሪዎቿ የፈጠረው የስራ እድል ዝቅተኛ በመሆኑ ይበልጥ መስራት ይገባል ተብሏል። ከአጠቃላይ ነዋሪው ህዝብ ብዛት አንፃር ሲታይ ሁለት በመቶ አይሞላም የተባለውን የዘርፉን የስራ እድል ለማሳደግ አዳዲስ ባለሀብቶችን መሳብ እና ለእነሱ የሚመች አገልግሎት መዘርጋት እንዲሁም ነባሮቹ እንዲጠናከሩ ማድረግ ትኩረት እንደሚያሻው የኢንደስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል አስገንዝበዋል። በሌላ በኩል ከተማዋ በቅርቡ ነፃ የንግድ ቀጠና እንድትሆን መደረጉ ዘርፉ እንዲሻሻል ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጡት ሚንስትሩ ይህንን ለማስተናገድ የከተማ አስተዳደሩ በመኖርያ ቤት ዝግጅት ፣ በሆቴል ፣ በመንገድ መሰረተ ልማት እና ሌሎች መስኮች አስቀድሞ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።

"ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ሀሳብ  በድሬደዋ በተዘጋጀ መድረክ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ባደረጉት ንግግር "እድገት አሳይቷል " ባሉት የኢንደስትሪ ዘርፍ ባሉ አራት መቶ አምሳ ያህል አምራች ኢንዱስትሪዎች አስራ ሁለት ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ጠቁመዋል።ድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ሆነች
በመድረኩ የተገኙት የኢንደስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል በሪፖርቱ መሠረት ዝቅተኛ ያሉትን የዘርፉ የስራ እድል ፈጠራ ከፍ ለማድረግ መስራት ይገባል ብለዋል። በቀጣይችግሮችን ቀርፎ ለውጥ ለማምጣት መሰራት አለባቸው ያሏቸውን ተግባራት ጠቁመዋል። የፌደራል መንግስት ከተማዋን ነፃ የንግድ ቀጠና እንድትሆን ማድረጉን ያነሱት አቶ መላኩ በዚህ እድል የሚመጡ ባለ ኢንዱስትሪዎችን ለማስተናገድ አስተዳድሩ አስቀድሞ በመኖርያ ቤት ፣ በሆቴል ማስፋፋት እና የመንገድ መሰረተ ልማትን በማሳደግ በኩል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል ።ሃያ አራት ሰዓት ሰላሙ የተጠበቀ አካባቢ መፍጠርና የደርቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያተኮረ የቅድመ ዝግጅት ተግባር የከተማ አስተዳደሩ ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።
በውይይቱ የመስተዳድሩን ካቢኔ አባላት ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተሳትፈዋል።ከቅርብ ወራት ቀደም ብሎ በሀገሪቱ የመጀመርያ የሆነው የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።

መሳይ ተክሉ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ

በድሬዳዋ ኢንዱስትሪን ማስፋፋት በሚቻልበት መንገድ ላይ ያተኮረ መድረክ ምስል፦ Messay Teklu/DW
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW