1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድሬዳዋ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ሶማሌ ክልል ሰፈሩ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 11 2014

በጎሳ ግጭትና በተያያዥ ጠብ ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ ላለፉት አራት ዓመታት ያክል ድሬዳዋ ከተማ ዉስጥ ተጠልለዉ የነበሩ ተፈናቃዮች ሶማሌ ክልል መስፈራቸዉ ተነገረ።የድሬዳዋ አደጋ ስጋት መስሪያ ቤት እንዳለዉ አሁን ሶማሌ ክልል የሰፈሩት ከ600 በላይ አባዎራዎች ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ናቸዉ።

Äthiopien Dire Dawa | IDPs
ምስል Mesay Mekonne/DW

This browser does not support the audio element.

ለአራት አመታት ያህል በድሬደዋ ተጠልለው የቆዩ ከስድስት መቶ በላይ አባወራዎች አብዛኞቹ በዘላቂ እንዲቋቋሙ መደረጉን የድሬደዋ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበርያ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በድሬደዋ ለአራት አመታት ያህል የቆዩት ዜጎች በሶማሌ ክልል የተሌዩ አካባቢዎች ቦታ ተዘጋጅቶ እንዲሰፍሩ መደረጉ ተገልጻል፡፡ መሬት ተሰጥቷቸው ከመጠለያ መውጣታቸው ጥሩ መሆኑን የሚያነሱት ተፈናቃዮች ዘላቂ ኑራቸውን የሚመሩበት ሁኔታ አለመመቻቸቱንና እሱን እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

የድሬደዋ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበርያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሱሌይማን አሊ ለዶይቼ ቬሌ እንደነገሩት ከሶማሌ ክልል አደጋ ስጋት ፅ/ቤት ጋር በመሆን ላለፉት አራት አመታት በድሬደዋ በመጠለያ የቆዩ ዜጎችን አብዛኞቹን በሶማሌ ክልል ባሉ የተለያዩ ቦታዎች የማስፈር ስራ ተሰርቷል፡፡

ምስል Mesay Mekonne/DW

በዘላቂነት የማስፈር ስራው በህብረተሰቡ ምርጫ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት  ኃላፊው በግብርና ላይ የተመሰረተ ኑሮ ይኖሩ የነበሩት ዜጎች ለዚሁ አመቺ በሆነ ቦታ መስፈራቸውን ጠቁመዋል፡፡ አሁን በድሬደዋ የቀሩ ዘጠና ስምንት አባወራዎች በዚሁ ሳምንት ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ይሄዳሉ ብለዋል፡።

በዛለቂ መልሶ ማቋቋሙ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን አካባቢ ከሰፈሩ ተፈናቃዮች አንዱ የሆኑት አቶ ቦቆሬ ሀሰን ለዶይቼ ቬሌ በስልክ ተከታዩን አስተያየት ሰተዋል፡፡

ዘላቂ ኑሮን በጀመሩበት አካባቢ የውሀ አቀርቦት ችግር መኖሩን የገለፁት አቶ ቦቆሬ የትምህርት የጤናና ሌሎች መሰረተ ልማቶችም ባግባቡ አለመኖራቸውን በመጥቀስ እንዲሟላ ጠይቀዋል፡፡

በድሬደዋ ለመዝናኛ ማዕከል እና ለወጣቶች ስፖርት ማዘውተርያነት ቢሰሩም ተፈናቃዮቹን ለማስቀመጥ በመዋላቸው አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩት ማዕከላት አሁን የተፈናቃዮቹን መውጣት ተከትሎ ወደ ስራ እንዲገቡ ያደረጋል ተብሏል፡፡  


መሳይ ተክሉ


ልደት አበበ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW