1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርቅን የመቋቋሚያ ዘዴ በአፋር

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 25 2008

መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የኤልኒንዮ የአየር ፀባይ ለውጥን ተከትሎ ከፍተኛ ድርቅና እና ጎርፍ ያጠቃቸዉ አካባቢዎች ችግሩን በዘላቂነት ለመቋቋም በሚችሉበት ዘዴ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ። ከነዚህ ድርጅቶች መካከል የጀርመኑ የቴክኒክ ተራእዶ ድርጅት «GIZ» «ቬልት ሁንገር ሂልፈ» እና የ«ጀርመን አግሮ አክሽን» ይገኙበታል።

Hilfsprojekten für die Opfer von Dürre und Flut in Afar
ምስል DW/G. Tedla

ድርቅን የመቋቋሚያ ዘዴ በአፋር

This browser does not support the audio element.

በዚሁ መሰረት በተነቃቁት ፕሮጀክቶች በአፋር ከሰመራ አዉራጃ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ሰርዶ አካባቢ ከሦስት መቶ በላይ የዝናብ ዉኃ ማቆርያ ጉድጓዶች ተሰርተዋል። በሰመራ አፋር ክልል የተፈጥሮ ኃብት ልማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ መሃመድ አህመድ እንደገለፁት፤ አርብቶ አደሩ ከብቱ በድርቅ ምክንያት እያለቀ ባለበት በአሁኑ ሠዓት ወላድ የሆኑ ፍየሎችና በጎችን ከማኃበረሰቡ እየገዛን ድርቁ ካለፈ በኋላ መልሰን ችግር ላይ ላለዉ አርብቶ አደር በስጦታ መልክ እንሰጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

ምስል DW/G. Tedla

ይህን ስንል አንደኛ አርብቶ አደሩ የቀንድ ከብቱ ከሚሞት ሸጦ ገንዘቡን ይጠቀምበታል፤ ሁለተኛ ማቆያ ስፍራ ላይ አስቀምጠን ድርቁ ሲያልፍ እንስሳቶቻቸዉን ላጡ እንደገና በስጦታ የምንሰጥበት ሂደት ነዉ ፤ «ዲስቶኪንግ» ና «ሪስቶኪንግ» ተብሎ ይጠራል ሲሉ አብራርተዋል።


ለሁለት ዓመታት ዝናብ ያልጣለበት የምስራቃዊ ኢትዮጵያ አፍር ግዛት ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱ ይታወቃል። በአብዛኛዉ አርብቶ አደር በሚገኝበት በዚህ ክልል ያለዉ የቀንድ ከብት በዉኃ እጦት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ ላይ መዉደቁም የሚታይ ሆንዋል። የአፋር ሕዝብ በባህሉ መሠረት ለቀንድ ከብት በሚሰጠዉ ከፍተኛ ግምት በዉኃ እጦት ድርቅ ላይ የወደቀዉን ከብት አርዶ የመብላት ፍላጎት እንደሌለዉ ይታወቃል። በአፍሪቃዉ ቀንድ በኢትዮጵያ በጅቡቲና በኤርትራ ወደ አራት ሚሊዮን አፋር እንደሚኖር ዘገባዎች ያሳያሉ።

ምስል DW/G. Tedla

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ሰሞኑን አፋር አካባቢን ተዘዋዉሮ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ ድርቅና እና ጎርፍ ያጠቃቸዉ አካባቢዎች ችግሩን በዘላቂነት ለመቋቋም እያደረጉ ያሉትን ተመልካክቶ ሰፋ ያለ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW