ድርቅ፣ ረሀብ እና የርዳታ ማፈላለጊው ስብሰባ በሮም
ሰኞ፣ ሐምሌ 18 2003ማስታወቂያ
አሁኑኑ አጣዳፊ ርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር በነዚህ ሀገሮች ፡ በተለይ ድርቁ አብዝቶ በጎዳት በሶማልያ ሁኔታዎች እየከፉ እንደሚሄዱ ዲዩፍ አስጠንቅቀዋል። ለጋሽ ሀገሮች ርዳታ ለማቅረብ ቃል ቢገቡም፡ እስካሁን ለተጎጂዎች የደረሰው ገንዘብ በጣም ንዑስ መሆኑ ነው የተገለጸው። ፋኦ ያስተናገደው ይኸው በሮማ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የዛሬውን ስብሰባ የሮማው ወኪላችን ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ ተከታትሎታል። ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት አነጋግሬዋለሁ።
አርያም ተክሌ
ሒሩት መለሰ