ድርቅ ያስተጓጎለው የመማር ማስተማር ሂደት በሶማሌ ክልል
ዓርብ፣ መጋቢት 9 2014ማስታወቂያ
በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ። ድርቁ በክልሉ ከአንድ ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቋረጥ አስገድዷል። በሶማሌ ክልል ድርቅ ጉዳት ባስከተለባቸው አካባቢዎች ለሚኖረው ማኅበረሰብ የምግብ ፣ የውሀ እና ሌሎች ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል። በዚህ መሀልም በክልሉ የተለያዩ ዞኖችን ለችግር ለዳረገው ድርቅ በቅርቡ የሚጠበቀው የበልግ ዝናብ መፍትሄ ያመጣል በሚል ተስፋ ተደርጓል።
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ