1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ሳይንስኢትዮጵያ

ድንችን ለረዥም ጊዜ የማቆየት ዘዴ

ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2016

ገበሬዎቹ በዚህ ቴክኖሎጂ ሲጠቀሙ ለዘር የሚሆነው ድንች የሚያወጣው ግንድ ጠንካራና እስኪዘራ ድረስ የማይጎዳ በመሆኑ ከፍተኛ ምርት ማግኘት እንደተቻለ ባለሙያው አስረድተዋል። ከቴክኖሎጂው በተጨማሪ ዩኒቨርስቲው በምርምር ያወጣቸው የድንች ምርጥ ዘር ስለሚጠቀሙ በሄክታር ከ 370 እስከ 400 ኩንታል እያገኙ ነው።

በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ድጋፍ ከሚመረት ድንች በከፊል
በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ድጋፍ ከሚመረት ድንች በከፊልምስል፦ Privat

ድንችን ለረዥም ጊዜ ማቆየት

This browser does not support the audio element.

ድንች አብቃይ ተብለው ከሚታወቁ አካባቢዎች ምስራቅ ሃረርጌ ይገኝበታል። የአካባቢው ገበሬዎች ድንች ለቀጣዩ የዘር ወቅት ለማዘጋጀትም ሆን ከምርት በኋላ ወደ ገበያ የሚያቀርቡበት ባሕላዊ የሆነ የማቆያ ዘዴ ይጠቀሙ ነበር። ይህ ግን ድንቹ ሳይበሰብስ የሚቆይበት ዕድሜ ቀናት ቢበዛ ሳምንታት ነበረ ይላሉ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ የምርምር ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አቶ ፈይሳ ሁንዴሳ። በተለይ ለዘር ዝግጅት ገበሬዎች ድንቹን መሬት ላይ በመቆላል አፈር ያለብሱታል አልያም በማዳበሪያ ከረጢት አከማችተው እቤት ውስጥ ያስቀምጡታል። ይህ በቂ የጸሐይ ብርሃን ስለማያገኝ ድንቹ የሚያበቅለው ግንድ ደካማ ከማድረጉም በላይ ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደማይችል ነው አቶ ፈይሳ የሚያስረዱት።

በዚህ ባሕላዊ የድንች ዘር የማብቀልና የማቆየት ዘዴ ተጠቅመው የሚያመርቱ ገበሬዎች በሄክታር ከ20 እስከ 30 ኩንታል ምርት ያገኙ እንደነበረ ገበሬዎቹ ነግረውናል። ይህን ችግር ለመፍታት የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች በቀላልና በአካባቢ ከሚገኙ የመስሪያ ዕቃዎች ሊሰራ የሚችል እና ድንችን እስከ 6 ወራት ድረስ ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ በምርምር በማዳበር ገበሬው ምርቱን እንዲያሳድግ እያደረጉ ይገኛሉ። ለመሆኑ ለዘር የሚፈለግ ድንች የማቆያ ቴክኖሎጂው አሰራር እንዴት ነው አልናቸው አቶ ፈይሳን
" የድንች ዘር የማቆያ መጋዘን የሚሰራው እዚሁ በአካባቢያችን ከሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ነው። ለምሳሌ ወለሉ እንደማንኛውም ወለል ይሰራል። ለንጽህና ሲባል ከዛ የተሻለም ማድረግ ይጣላል። መጋዘኑ ሲሰራ የጣራ ክዳን የሚኖረው ሲሆን አራቱም ግድግዳዎች  ከወገብ በላይ ክፍት ይደረጋል። ካስፈለገ በሽቦ መሸፈን ይቻላል። ይህም የተመጣጠነ የጸሐይ ብርሃንና ነፋስ እንዲያገኝ ያስችለዋል። ንቹ የቀመጥበት ከዕንጨት የተሰራ መደርደሪያ አልጋ ይሰራል። "

የተመጣጠነ የፀሐይ ብርሃንና ነፋስ እንዲያገኝ ተደርጎ የተቀመጠ ለዘር የሚውል ድንችምስል፦ Privat


ድንች ከማሳ ከተሰበሰበ በኋላ ረዥም ጊዜ መቆየት ከማይችሉ ተክሎች ይመደባል። በመሆኑም ገበሬዎች ምርታቸውን ለረዥም ጊዜ በማቆየት ወደገበያ እንዳያወጡት ቶሎ ስለሚበሰብስ የላባቸውን ዋጋ ማግኘት አይችሉም ነበር። የዩኒቨርስቲው ተመራማሪዎች ለዚህም መላ አበጅተውለታል።

"ድንችን ለረዥም ጊዜ በማቆየት ለገበያናለምግብነት ለማዋል ደግሞ የመጋዘኑ አሰራር ተመሳሳይ ሆኖ መጋዘኑ መሉበሙሉ ጨለማ እንዲሆን ተደርጎ ይሰራል። ይህም ድንቹ ፀሐይ ብርሐን አግኝቶ በውስጡ ያለውን ምግብ በመጠቀም ወደ ብቅልነት ሳይለወጥ ብዙ ጊዜ እንዲይ ያደርገዋል። በዚህ ዘዴ ድንቹን እስከ 6 ወራት ማቆየት ይቻላል።"

ገበሬዎቹ በዚህ ቴክኖሎጂ ሲጠቀሙ ለዘር የሚሆነው ድንች የሚያወጣው ግንድ ጠንካራና እስኪዘራ ድረስ የማይጎዳ በመሆኑ ከፍተኛ ምርት ማግኘት እንደተቻለ ባለሙያው አስረድተዋል።  ከቴክኖሎጂው በተጨማሪ ዩኒቨርስቲው በምርምር ያወጣቸው የድንች ምርጥ ዘር ስለሚጠቀሙ  በሄክታር ከ 370 እስከ 400 ኩንታል እያገኙ እንደሆነ አቶ ፈይሳ አክለዋል። 

ድንችን ለረዥም ጊዜ የማቆየት ዘዴምስል፦ Privat


አርሶ አደር ዲኖ ሉያ ከዚህ ቀደም በባሕላዊ መንገድ ድንች በሚያመርቱበት ጊዜ በዛ ቢባል በሄክታር 30 ኩንታል ያገኙ እንደነበር አጫውተውናል። አሁን ይህን ቴክኖሎጂና ምርጥ ዘር መጠቀማቸው ዘሩ ሳይበሰብስ ስለሚቆይ የተሻለ ምርት እንደሚያገኙ ነው ያከሉት።

ይህ በሐረማያ ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎች የተገኘው የምርምር ውጤት የሆነ ቴክኖሎጂ በመላ ሃገሪቱ ወደሚገኙ ድንች አምራች ገበሬዎች ለማስፋፋት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ የምርምር ኤክስቴንሽን አስተባባሪው አቶ ኢብሳ ገልጸውልናል።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW