1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው በፍሎሪዳ ንግግር አደረጉ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2017

በፍሎሪዳ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር "የአሜሪካ ሕዝብ 47ኛው ፕሬዝደንት አድርጎ ስለመረጠኝ ላመሰግን እወዳለሁ" ያሉት ዶናልድ ትራምፕ "ለሁሉም ዜጋ" ለመታገል ቃል ገብተዋል። ዶናልድ ትራምፕ በሕዝብ ድምጽ (popular vote) ማሸነፋቸውን ቢናገሩም እስካሁን ይፋ በሆነው ውጤት በእርግጠኝነት ሊታወቅ አይችልም።

ዶናልድ ትራምፕ
ዶናልድ ትራምፕ በሕዝብ ድምጽ (popular vote) ማሸነፋቸውን ቢናገሩም እስካሁን ይፋ በሆነው ውጤት በእርግጠኝነት ሊታወቅ አይችልም። ምስል Brendan McDermid/REUTERS

በቤተሰቦቻቸው ተከበው የምረጡኝ ዘመቻቸው የምርጫውን ሒደት በሚከታተልበት ፍሎሪዳ ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ሰላምታ ሰጥተዋል። 

ትራምፕ ንግግር ማድረግ ሲምሩ ደጋፊዎቻቸው ከፍ ባለ ድምጽ  "ዩኤስኤ" ይሉ ነበር። 

ትራምፕ "እውነቱን ለመናገር ይኸ የምንጊዜውም ታላቅ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነው። በዚህ ሀገር ምንአልባትም በምድር ታሪክ እንዲህ አይነት ነገር ታይቶ አይታወቅም" ሲሉ ተደምጠዋል።

ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን "ለመፈወስ" እና በሪፐብሊካኖች የሚነሳውን የድንበር ችግር ለመፍታት ቃል ገብተዋል። 

"የአሜሪካ ሕዝብ 47ኛው ፕሬዝደንት አድርጎ ስለመረጠኝ ላመሰግን እወዳለሁ" ያሉት ትራምፕ "ለሁሉም ዜጋ" ለመታገል ቃል ገብተዋል።

"ልጆቻችን የሚገባቸውን ጠንካራ፣ ደሕንነቷ የተጠበቀ እና የበለጸገች አሜሪካ" እስክትኖር ዶናልድ ትራምፕ "እረፍት አይኖረኝም" ብለዋል። 

ዶናልድ ትራምፕ በሕዝብ ድምጽ (popular vote) ማሸነፋቸውን ቢናገሩም እስካሁን ይፋ በሆነው ውጤት በእርግጠኝነት ሊታወቅ አይችልም። 

ትራምፕ ቤተሰቦቻቸውን አመሥግነው፣ ዕጩ ምክትል ፕሬዝደንት ጄዲ ቫንስን አሞግሰው እንደ ሲኤንኤን (CNN) ያሉ መገናኛ ብዙኃንን "የጠላት ጎራ" ሲሉ ወርፈዋል።


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW