1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶናልድ ትራምፕ ስለ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ምን አሉ? ቃለ መጠይቅ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 9 2017

በዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተፎካካሪያቸው ከማላ ሐሪስን በሰፊ የድምፅ ልዩነት ካሸነፉ በኋላ ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን ሰጥተዋል ። በፕሬዚደንትነት ቃለ መሐላ ከመፈጸማቸው አንድ ወር ግድም ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ በዋናነት ምን አሉ? ቃለ-መጠይቅ

Beste Reuters-Fotos 2024 | Ex-Präsident Trump
ምስል Brendan McDermid/REUTERS

ዶናልድ ትራምፕ ስለ አሜሪካ የውጭ ግንኙነት ምን አሉ?

This browser does not support the audio element.

በዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተፎካካሪያቸው ከማላ ሐሪስን በሰፋ የድምፅ ልዩነት ካሸነፉ በኋላ ሪፐብሊካኑ  ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን ሰጥተዋል ። 

መግለጫውን የተከታተለው የአትላንታው ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉን በዋናነት ስለተነሳው ጉዳይ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። ዶናልድ ትራምፕ ጥር ሰኞ፤ ጥር 12 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በፕሬዚደንትነት ቃለ መሐላ ከመፈጸማቸው አንድ ወር ግድም ቀደም ብለው ከትናንት በስትያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በዋናነት ስለ ውጭ ፖሊሲያቸው ምን አሉ? 

አውሮጳውያን ዩክሬንን እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ጦር መሣሪያዎች በተደጋጋሚ በማስታጠቅ እና በተለያዩ ርዳታዎች በመደገፍ የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲንን ወደ ድርድር ለማስመጣት ጥረት ቢያደርጉም ያ ሳይሳካ ቀርቷል ። ቭላድሚር ፑቲንም ጦራቸው ዩክሬን ውስጥ ጥቃቱን ቀጥሏል ።

የአውሮጳ መሪዎች በዚህ ሁኔታ ውስጥ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ከአውሮጳ ወደ ዩክሬን ምድር የመላክ ፍላጎት እንዳላቸው ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል ። ዶናልድ ትራምፕ  የዩክሬንን ደኅንነት ለማስጠበቅ አንድም ወታደሬ የዩክሬንን መሬት አይረግጥም ሲሉ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጥተዋል ። በንግግራቸው ምናልባት ስለዚህ ያሉት ነገር አለ? ዩክሬን ወደፊት በዶናልድ ትራምፕ የመሪነት ዘመን ከዩናይትድ ስቴትስ የምታገኘው ርዳታ ምን ይመስላል?

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታሪኩ ኃይሉ

ሸዋዬ ለገሠ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW