1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ ለፖላንድ መሳርያ መከላከያን አቀረበች

ማክሰኞ፣ ኅዳር 13 2015

ፖላንድ ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር አካባቢ በሚሳይል ጥቃት ከደረሰ በኋላ ጀርመን «ሀገር ፍቅር» በተባለ ከባድ መከላከያ ፖላንድን እንደምትደግፍ አስታወቀች። ይህ የተገለፀዉ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ክሪስቲነ ላምብሬሽት ከፖላንድ አቻቸዉ ከማሪዩዝ ብላሽቻክ ጋር በጉዳዮ ላይ ከተስማሙ በኋላ መሆኑ ተነግሯል።

Deutschland Bundeswehr | Flugabwehrraketengruppe 21 mit "Patriot"-System
ምስል Jens Büttner/dpa/picture alliance

ፖላንድ ከዩክሬን ጋር በሚያዋስናት ድንበር አካባቢ በሚሳይል ጥቃት ከደረሰ በኋላ  ጀርመን «ሀገር ፍቅር» በተባለ ከባድ መከላከያ ፖላንድን እንደምትደግፍ አስታወቀች። ይህ የተገለፀዉ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ክሪስቲነ ላምብሬሽት ከፖላንድ አቻቸዉ ከማሪዩዝ ብላሽቻክ ጋር በጉዳዮ ላይ ከተስማሙ በኋላ መሆኑ ተነግሯል።  የጀርመንዋ የመከላከያ ሚኒስትር "ፖላንድ በተለይ የዩክሬን ጎረቤት በመሆንዋ ለአደጋ ተጋልጣለች" ሲሉ ተናግረዋል። ጀርመን ለፖላንድ ያቀረበችዉ «ሀገር ፍቅር» የተሰኘዉ የመሳርያ መከላከያ በተለይ ተዋጊ አውሮፕላኖችን፤ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን እና ተጓዥ አይነት ሚሳይሎችን የሚከላከል እና የሚያመክን መሳርያ ነዉ። ይህ የመከላከያ መሳርያ መረጃ በሚያስተላልፉ በርካታ ራዳሮች በሚያደርጉት ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ነውም ተብሏል።

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW