1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ሊዮፓርድ ታንኮችን ለዩክሬን እሰጣለሁ ማለቷን ምዕራባውያን አወደሱ

ሐሙስ፣ ጥር 18 2015

ዩክሬን በቅርቡ ከጥምረቱ አባሎች ከ100 በላይ ታንኮችን ልታገኝ እንደምትችል ነው የሚገመተው። ሩሲያ ግን በተለይ የጀርመንን ውሳኔ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት የጀርመን ጦር በሩሲያኖች ላይ ያደረሰውን ጥቃትና የፈጸመውን በደል የመርሳት ያህል ነው በማለት አውግዛለች። የታንክ መደርደር በጦርነቱ ላይ ምንም ለውጥ አይችልም ስትልም አስታውቃለች ።

Kombobild | Kampfpanzer
ምስል Francois Nascimbeni/Eric Feferberg/Wojtek Radwanski/AFP

ጀርመን ሊዮፓርድ ታንኮችን ለዩክሬን እሰጣለሁ ማለቷን ምዕራባውያን ማወደሳቸው

This browser does not support the audio element.

ጀርመን ከኪይቭና ክኔቶ አባል መንግስታት ለዩኪረን በተለይ ሊዎፓርድ  2 የተሰኙ የጦር ታንኮችን እንድትሰጥ ሲቀርብላት የነበረውን ጥያቄ አዘግይታም ቢሆን ትናንት መልስ ሰጥታበታለች። የጦር ታንኩ እርዳታ ጦርነቱን ይበልጥ ሊያሰፋውና ከሩሲያ ጋርም ያለውን ግጭት ሊያከረው ይችላል በሚል ስጋት፤  እንዲሁም ጀርመን ለዩክሬን ቀዳሚ የታንክ ለጋሽ አገር እንዳትሆን መራሄ መንግሥት ሹልዝ ውሳኔውን እንዳዘገዩት ሲነገር ቆይቷል።አሁን ግን  ከአውሮፓ ህብረትና የኔቶ አባል አገሮች በሚቀርቡት ተደጋጋሚ ጥያቆዎችና የመንግስታቸው አባሎች ከሆኑት  የአረንጓዴዎቹና የሊበራል ፓርቲዎች ግፊት ጭምር ቻንስለሩ ይህን ውሳኔ ያስተላለፉ ሲሆን፤ በውሳኔው መሰረትም  ጀርመን 14 የሎዎፓርድ ሁለት ታንኮችን ለዩኪሬን ለማቅረብና ወታደሮችንም ለማሰልጠን ፈቅዳለች፤ ሌሎች እነዚህኑ ታንኮች ከጀርመን የገዙ አገሮችም ለዩክሬን ማስተላልፍ እንዲችሉ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።  
የጀርመንን ውሳኔ ዩክሬንና ሌሎች ከዩክሬን ጎን የቆሙ ያውሮፓና የኔቶ አገሮች በክፍተኛ ደረጃ ነው ያወደሱት። ፕሪዝዳንት ባይደን “ዩኪሬንን በጋራ ለመርዳት በሚደረገው ጥረት ቻንስለር ሹልስ ለሰጡት አመራርና ላሳዩት ቁርጠኝነት ክልብ አመስግናለሁ” በማለት  በእሳቸው መንግስት በኩልም 31 ታንኮችን ለመስጠት የወሰኑ መሆኑን አስታውቀዋል። ፈረንሳይ፣ ኒዘርላንድስ፤ ስፔን ፊንላንድ፤ በተለይ ፖላንድና ሌሎች የህብረቱና ኔቶ አገሮችም በጀርመን ውሳኔ  የተደሰቱ መሆናቸውን በመገለጽ፤ በበኩላቸው ካሉዋቸው የጀርመን ታንኮች የተወሰኑትን ለዩክሬን እንደሚሰጡ እያሳወቁ ሲሆን፤ በዚህም ዩክሬን በቅርቡ ከሁሉም የጥምረቱ አባሎች ከ100 በላይ ታንኮችን ልታገኝ እንደምትችል ነው የሚገመተው።  
ሩሲያ ግን በተለይ የጀርመንን ውሳኔ ከታሪክ ያለመማርና ከዚህ ቀደም በተለይ በሁለተኛ የዓለም ጦርነት የጀርመን ጦር በሩሲያኖች ላይ ያደረሰውን ጥቃትና የፈጸመን በደል የመርሳት ያህል ነው በማለት አውግዛ፤ የታንክ መደርደር በጦርነቱ ላይ ምንም ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችል አስታውቃለች ።   
በእርግጥ ከጀርመንና ሌሎቹ አገሮች የሚቀርቡት ታንኮች የጦርነቱን ሁኒታ በፍጥነት የሚቀይሩት  ስለመሆኑ በእርግጠኘነት መናገር እንደማይቻል ነው የሚነገረው።፡የኔቶ ዋና ጸሃፊ ሚስተር ስቶልቴንበርግ ግን ዩክሬኖች ከፍተኛ ልምድ ያላቸው በመሆኑ መሳሪያዎቹን ካገኙ ለውጥ ማስመዝገባቸው አይቀርም ነው የሚሉት። “የበለጠ ድጋፍ ማድረግና የጦር መሳሪያ ማቅረብ ያለብን፤  ዩክሬን አሁን ባለው ይዞታዋ እንድትቆይ ሳይሆን፤ ዩክሬን ግዛቶቿን  ነጻ እንድታወጣና ሉዑላዊነቷን እንድትስከብር  ነው” በማለት  የታንኮቹ እርዳታ ዩክሬኖች  ካላቸው ልምድና ከሚያገኙት ስልጠና አንጻር የጦርነቱን ሁኔታ ሊቀይረው እንደሚችል ገልጸዋል። 
ዋና ጸሀፊ ስቶልተንበግ ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍና እርዳታ አስፈላጊነትና ወሳኘት የሚገልጹት፤ ሩሲያ  በዚህ ጦርነት ብታሸነፍ ይደርሳል ብለው ከሚያስቡት አደገኛ ሁኒታ አንጻር ነው፡ “ፕሬዝዳንት ፑቲን ይህን ጦርነት ካሸነፉ፤ ለዩክሬን ትልቅ ትራጀዲይ ነው፤ ለኛ ደግሞ አደገኛ ነው።  አምባገነን  መሪዎች በወታደራዊ ሀይላቸው የፈለጉትን ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ መጥፎ ክስተት ነው የሚሆነው። ለዚህም ነው ለዩክሬን የሚሰጠው ድጋፍ ለራሳችን ደህንነት ጭምር መሆኑን መገንዘብ ያለብን ብለዋል፤ 
ዩዩክሬኑ ፕሬዝድንት ዜለንስኪ፤ ታንኮቹ በፍጥነት እንድዲደርሷቸው እየጠይቁ  ቢሆንም  ከሶስት ወር በፊት ግን ዩክሬን ደርሰው ለግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። ከሁሉም የጦር ታንኮች የጅርመን ስራሾቹ ሊዎፓርድ ሁለቶቹ ተመራጭ የሚሆኑት፤ በተሻለ የነዳጅ ፍጆታቸውና በተገጠሙላቸው አዳዲስ ቴክኖጂ ምክኒያት እንደሆነ ይጠቀሳል።  ክሁሉም በላይ ግን ጠቀሜታቸው  በአውሮፓ በተለይ በኔቶ አባል አገሮች  በብዛት የሚገኙ በመሆኑና ዩክሬን ከነዚህ አገሮች ከምታገኛቸው ታንኮች ዓንድ እራሱን የቻለ የታንክ ብርጌድ ለመገንባት ስለሚያስችላት እንደሆነም ይገለጻል ። በለንደን የኪንግስ ክሮስ ኮሌጅ ፕሮፌሰር  የሆኑት ዶክተር ማይክ ማርቲን ይህንኑ ሀስብ ነው የሚያጠናክሩት። “ ዋናው ነገር  እነዚህ ታንኮች ሁሉም ቦታ መገኘታቸው ነው።  ፖላንዶች፣ ቼኮች ሁሉም እነዚህ ታንኮች አሉሏቸው ። ይህ ማለት ዩክሬኖች አንድ የታንክ ሀይል ለመገንባት ያስችላቸዋል ማለት ነው፤ ሲሉ የሊዎፖልዶቹ ታንኮች በሁሉም ቦታ መገኘት አንዱ የተፈላጊነታቸው ምክኒያት መሆኑን ገልጸዋል።  
ፕሬዝዳንት ዜለንክ ግን አሁንም ተጨማሪ ታንኮች ብቻ ሳይሆን  ተዋጊ ጀቶች ጭምር ባስቸኳይ እንዲላክላቸው እየጠየቁ ነው። የተዋጊ ጀቶቹ ጥያቄ ቢያንስ በአሁኑ ወቅት አዎንታዊ ማላሺ ያገኛል ተብሎ ባይታሰብም፤ የጦርነቱ ግለትና  እየጨምረ የመጣው የአውሮፓውያኑ ተሳፎ ግን በተለይ የኔቶ አገሮችን ወደ ጦርነቱ ስቦ የሚያስገባቸው እንዳይሆን ማስጋቱ አልቀረም።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስለ ለዩክሬን ስለሚሰጥ እርዳታ መግለጫ ሲሰጡምስል Susan Walsh/AP/picture alliance
የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ በጀርመን ምክር ቤት ምስል Fabrizio Bensch/REUTERS

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW