1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ሰባት ዘመናዊ ታንኮችን ለዩክሬን ለመስጠት ወሰነች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 28 2014

ጀርመን ለዩክሬዪን 2000 የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ዘመናዊ የተባለ ሰባት ታንኮችን ለዩክሬን እንደምትሰጥ ተነገረ። 40 ኪሎሜትር ማስወንጨፍ የሚችለዉ ታንክ በአየር ላይ ያሉ አዉሮፕላኖችንም አነጣሮ አይቶ ማዉደም የሚችል ነዉ ተብሎአል። ይሁንና ይህን ታንክ ለመጠቀም ረዘም ያለ ጊዜ ስልጠና መዉሰድ እንደሚያስፈልግ ነዉ የተነገረዉ።

Panzerhaubitze 2000
ምስል Sebastian Gollnow/dpa/picture alliance

እስከ 40 ኪሎሜትር ማስወንጨፍ የሚችለዉ ታንክ ነዉ

This browser does not support the audio element.

የጀርመን ፌደራል መንግስት ዩክሬንን ከሩሲያ የወረራ ጦርነት ለመከላከል ከባድ የጦር መሳሪያ ለማቅረብ ለረጅም ጊዜ ሲያመነታ ቆይቶ ዛሬ መወሰኑ ተመልክቶአል።  ዛሬ ስሎቫኪያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር ክርስቲን ላምበሬሽት ስሎቫክያ ላይ ባደረጉት ንግግር ሃገራቸዉ ለዩክሬዪን 2000 የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ዘመናዊ የተባለ ሰባት ታንኮችን ለዩክሬን ታቀርባለች። 40 ኪሎሜትር ማስወንጨፍ የሚችለዉ ታንክ በአየር ላይ ያሉ አዉሮፕላኖችንም አነጣሮ አይቶ ማዉደም የሚችል ነዉ ተብሎአል። ይሁንና ይህን ታንክ ለመጠቀም ረዘም ያለ ጊዜ ስልጠና መዉሰድ እንደሚያስፈልግ ነዉ የተነገረዉ። ስልጠናዉንም ቢሆን ጀርመን ለመስጠት ዝግጁ መሆንዋ ተዘግቦአል። ጀርመን ለዩክሬይን መከላከያ ከባድ መሳርያ ሰጠች ማለት እስካሁን ትከተለዉ የቆየችዉን የሰላም መርህ አፈረሰች ማለት ይሆን? ይህን የፊደራል ጀርመን ዉሳኔ ፤ ፖለቲከኞች ሁሉ ይስማሙበታል? ህዝቡስ? እነዚህን ጥያቄዎች ይዘን የበርሊኑን ወኪላችንን በስልክ ጠይቀነዋል ሙሉዉን ቃለ ምልልስ ይከታተሉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ኃደሰ

ነጋሽ መሐመድ  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW