1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ሽቱትጋርት ውስጥ ደማቁ ድባብ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት

ዓርብ፣ ሰኔ 28 2016

በጥንታዊቱና ታሪካዊቱ ሽቱትጋርት ከተማ ጀርመን እና ስፔን ከጥቂት ሰአታት በኋላ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመግባት ይፋለማሉ ። የጀርመን እና የስፔን ብሔራዊ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ከወዲሁ የተሟሟቁ ይመስላል ። በተለይ የጀርመን ደጋፊዎች በኮይኒግ ሽትራሰ ተሰባስበው እጅግ በደመቀ ሁኔታ ድጋፋቸውን ከወዲሁ እየገለጡ ነው ።

Deutschland | Fußball Europameisterschaft 2024 | 
ምስል Mantegaftot Sileshi/DW

ደማቁ የሽቱትጋርት የደጋፊዎች ድባብ

This browser does not support the audio element.

ጀርመን ሽቱትጋርት ውስጥ ደማቁ ድባብ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት

ለፍፃሜ የተጠበቁት በሩብ ፍፃሜ ሊፋለሙ ነው

በጥንታዊቱና ታሪካዊቱ ሽቱትጋርት ከተማ ጀርመን እና ስፔን ከጥቂት ሰአታት በኋላ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመግባት ይፋለማሉ ። የጀርመን እና የስፔን ብሔራዊ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ከወዲሁ የተሟሟቁ ይመስላል ። በተለይ የጀርመን ደጋፊዎች በኮይኒግ ሽትራሰ ተሰባስበው እጅግ በደመቀ ሁኔታ ድጋፋቸውን ከወዲሁ እየገለጡ ነው ። «ወደ ቤርሊን እንጓዛለን» ሲሉም በተደጋጋሚ በጀርመንኛ ሲዘምሩ ተደምጠዋል።

በጥንታዊቱና ታሪካዊቱ ሽቱትጋርት ከተማ ጀርመን እና ስፔን ከጥቂት ሰአታት በኋላ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመግባት ይፋለማሉ ምስል Mantegaftot Sileshi/DW

የ2016 ዓ.ም የአውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ እና የጀርመን ድል

ቤርሊን የዋንጫ ጨዋታ የሚደረግባት ከተማ ናት ። ዛሬ ሽቱትጋርት አሬና ውስጥ ከምሽቱ አንድ ሰአት በሚጀምረው የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ለመታደም ደጋፊዎች ወደ ከተማዪቱ እየተመመሙ ነው ።

ብዙዎች በዛሬው ግጥሚያ በምድብ ማጣሪያው አንድም ግብ ያልተቆጠረበት የስፔን ቡድን ያሸንፋል ሲሉ ገምተዋል ። የጀርመን ቡድን የዛሬውን የሩብ ፍፃሜ ካሸነፈ ዋንጫው ቤርሊን ውስጥ ይቀራል ሲሉም አክለዋል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW