1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ በሳክሶኒያ እና በቱሪንግ ክፍላተ አገሮች የሚካሄደዉ ምርጫ አንድምታ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 21 2016

በምስራቃዊ ጀርመን ሳክሶኒ እና ቱሪንግ ግዛቶች የፊታችን እሁድ የአካባቢ ምርጫ ያካሂዳሉ። በአካባቢ መንግሥት የፓርላማ ምርጫ ፓርቲዎቹ በፌዴራሉ ግዛቶች ውስጥ ነገሮች እንዴት መቀጠል እንዳለባቸው የተለያየ እቅድ ይዘዋል። መጤ ጠሉ 'አማራጭ ለጀርመን'-በጀርመንኛ ምሕጻሩ ኤኤፍዲ፤ አረንጓዴዎቹ፤ የክርስትያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ፤ በምርጫዉ ይሳተፋሉል።

ጀርመን በቱሪንጂያ ግዛት የምረጡኝ ዘመቻ
ጀርመን በቱሪንጂያ ግዛት የምረጡኝ ዘመቻ ምስል Ben Knight/DW

ጀርመን፤ ሳክሶኒ እና ቱሪንጂያ ግዛቶች ምርጫ እና አንድምታዉ

This browser does not support the audio element.

 በሳክሶኒያ  እና በቱሪንግ ክፍላተ አገሮች የሚካሄደዉ ምርጫ እና አንድምታዉ  

በምስራቃዊ ጀርመን በሳክሶኒያ  እና በቱሪንግ ክፍላተ አገሮች የፊታችን እሁድ  የአካባቢ ሸንጎ ምርጫ ይካሄዳል። ሰባት የፓለቲካ ድርጅቶች ተገቢ ቦታቸውን ለመያዝ እዚያ ሕዝብ ፊት ቀርበው ይወዳደራሉ።
የምርጫው ውጤት ለጀርመን መንግሥት የሦስትዮሹ ጣምራ   መንግሥት ወሳኝ ነው ተብሎ በተመልካቾች ዘንድ ይገመታል።
'አማራጭ ለጀርመን' ወይም በጀርመንኛ ምሕጻሩ ኤኤፍዲ፤ የሣራ ቫገን ክኔሽት ጥምር ፓርቲ እና የክርስትያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጥሩ ውጤት ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል፣ የግራ ዘመም ፓርቲ እና የሶሻል ዱሞክራቶቹ፣ የሊበራል ዴሞክራቶቹ እና የአረንጓዴው ፓርቲ ከአለፈው ምርጫ  ዝቅ ያለ ውጤት ያመጣሉ ተብሎም ይገመታል።

በጀርመን ዞሊንገን ከተማ ሦስት ሰዎች ስለ ተገደሉበት ጥቃት መረጃ ነበረው የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ
 
ሰሞኑን በምዕራብ ጀርመን በሶሊንገን ከተማ አንድ የሶሪያ ስደተኛ በስለት  የሦስት ሰዎችን ሕይወት ከአጠፋ ወዲህ በአገሪቱ በጀርመን ኃይለኛ ክርክርን በፓለቲካ ድርጅቶች መካከል አስነስቶአል። በሃገሪቱ ነዋሪዎች መካከል ጥርጣሬ ስጋት እና ቁጭትንም ቀስቅሷል። ተደጋግሞ  በጀርመን ከተማ የተፈፀመዉ የሽብር ጥቃት በተለይ መጤ ጠል ዜጎችን ይበልጥ ወደፊት እንዳያመጣቸዉም አስግቷል።

ጀርመን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ያካሄደችው የመጀመሪያው ብሔራዊ ምርጫ ሲታውስ
የፊታችን እሁድ በምስራቃዊ ጀርመን ሁለት ከተሞች የሚካሄደዉ ምርጫ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?
የበርሊኑን የሦስት ፓርቲዎች ጥምር መንግሥትንም የምርጫው ውጤት ያናጋ ይሆን? የሚለውን ጥያቄ አንስተን የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግረነዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል 

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW