ጀርመን በቡድን ሰባት አባል ሀገራት ፕሬዚደንትነቷ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ታተኩራለች
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 27 2014ማስታወቂያ
በኢንዱስትሪ የበለጸጉ የቡድን 7 አባል ሃገራት ሕብረትን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት በተያዘው የጎርጎርሳውያን አዲስ ዓመት መንበሩን የተረከበችው ጀርመን ፤የአየር ንብረት ጥበቃን ዋነኛ አጀንዳዋ እንደምታደርግ አስታውቃለች። ጀርመን በፕሬዜዳንትነት ቆይታዋ ከአየር ንብረት ጥበቃ በተጨማሪ የኮሮና ወረርሽኝ ማብቂያ እንዲያገኝ እና በወረርሽኙ የተደካመው ኤኮኖሚ እንዲያንሰራራ አበክራ እንደምትሰራ ከወዲሁ አቋሟን ገልጻለች።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ