1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን ኔፈርቲቲን ለግብፅ መመለስ ይኖርባት ይሆን?

ሐሙስ፣ ኅዳር 11 2018

በምዕራቡ ዓለም ኔፈረቲቲ ዘመናዊነትን በሚያሳዬ የማኅበረሰብ ዝግጅቶች ላይ መቃ አንገትዋን፤ የጫነችዉ ዘዉድን ምልክት እያደረጉ ያቀርቧታል። ኔፈረቲቲ የበርሊን ምልክት መሆንዋን የሚናገሩት ኢትዮጵያዊ የታሪክ ምሁር አንድ ቀን ወደ አገርዋ ወደ ግብፅ መግባትዋ እንደማይቀር ተናግረዋል። በጀርመን የሚገኙ ምሁራንም ይሄ ተስፋ እንዳላቸዉ ተናግረዋል።

ኔፈርቲቲ በበርሊን ሙዚየም ዉስጥ - ፎቶ 2022
ኔፈርቲቲ በበርሊን ሙዚየም ዉስጥ - ፎቶ 2022 ምስል፦ Maurizio Gambarini/IMAGO

ጀርመን ኔፈርቲቲን ለግብፅ መመለስ ይኖርባት ይሆን?

This browser does not support the audio element.

ጀርመን ነፈርቲቲን መመለስ ይኖርባት ይሆን?

የአንገተ መሎሎዋ ጥንታዊትዋ የግብፅ ንግሥት የኔፈረቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ በርሊን ሙዚየም ከተቀመጠ ወደ 117 ዓመት ገደማ ሆኖታል። ከሳምንታቶች በፊት ግብጽ ግዙፍ ሙዚየም ካስመረቀች በኋላ የዉቢትዋ የኔፈረቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ ወደ ግብፅ እንዲመለስ ይቀርብ የነበረዉ ጥያቄ እንደገና ተነቃቅቷል። ጀርመናዉያን የታሪክ አጥኚዎችም ጭምር ይህን ጥያቄ ዳግን እያነሱ ነዉ። ንግሥት ኔፈረቲቲ  በጥንታዊትዋ ግብፅ በጣም ታዋቂ ከሆኑት አንዷ ስትሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የውበት እና የሥልጣን ብሎም የስልጣኔ ምልክት ተደርጋ ትታያለች። እንዲያም ሆኖ ስለ ኔፈረቲቲ ህይወት እና ማንነት ከንድፈ ሐሳቦች እና ግምቶች በስተቀር በእርግጠኝነት የሚታወቅ ተጨባጭ የሆነ ነገር አለመኖሩ ይነገራል።

ኔፈርቲቲማለት “ቆንጆዋ (ወይም ፍጹም) ሴት መጥታለች” ማለት እንደሆን እና ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 14ኛዉ ክፍለ ዘመን የኖረች መሆኑ እና አክሄናተን ሚስት እንደነበረች ይነገራል። የኔፈርቲቲ በአሁኑ ዘመን ዝነኛነት ልታገኝ የበቃችዉ በጎርጎረሳዊ 1912 በኖራ ድንጋይ የተሰራዉ እና በቀለም የተሸለመዉ ከአንገት በላይ የኔፈርቲቲ ሃዉልት ከተገኘ በኋላ ነው። የኔፈረቲቲ ከአንገት በላይ ቅርጽ የተገኘዉ በጀርመናዊው የግብፅ ተመራማሪ በሉድቪግ ቦርቻርት (1863-1938) እና ከሱ ጋር ከነበሩ ተመራማሪዎች ቡድን ግብፅ ቴል ኤል-አማርና ዉስጥ በቁፋሮ ነዉ። ንግሥት ነፈርቲቲ መቃ አንገትዋ እና የአይንዋ ቅድ ብሎም የአፍንጫዋ ሰልካካነት ልዩ አድርጓታል። የነፈረቲቲ ቅርስ በቁፋሮ ሲገኝ ከኖራ ድንጋይ የተሰራ እና በቀለማት የተሸለመ እንደነበረ እና ግርማ ሞገስ ያለዉ እንደሆነ በግኝቱ ወቅት ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።

ፈርዖን አክሄናተን እና ንግሥቲቱ ኔፈርቲቲምስል፦ Paul Schemm/AP Photo/picture alliance

ከዓመታቶች በፊት ስለ የኔፈረቲቲ የጠየቅናቸዉ እና በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን ወደ ዓለም አቀፍ የቅርስ ማኅደር የሚገቡ የኢትዮጵያ የቅርስ አስተዳደር ሰነድ ዝግጅት ከፍተኛ ኤክስፐርት ሆነዉ ሲያገለግሎ የነበሩት የዝግጅት ክፍላችን ተባባሪ የነበሩት አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ ኔፈረቲቲ በጀርመናዊ የግብፅ ታሪክ አጥኝ ስለመገኘትዋ ነግረዉን ነበር።

በቁፋሮ የተገኘዉ የኔፈርቲቲ ከደረት በላይ ቅርፅ  ከሌሎች ግኝቶች ጋር ወደ በርሊን ተልኮ በጀርመን ከ 117 ዓመት በላይ አስቆጥሯል። ኔፈረቲቲ ዛሬ በፕሩሲያን የባህል ቅርስ ፋውንዴሽን ባለቤትነት ተይዛ በበርሊን በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየሞች ድረ-ገጽ ላይ እንደተገለጸው "የኒውስ ሙዚየም ኮከብ ቅርስ" ናት። የኒውስ ሙዚየም የበርሊን ሙዚየም አካል እና በተመድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ነው።

ከዘጋቢ ፊልም "ዉቢትዋ ኔፈርቲቲ የማን ናት?"ምስል፦ Medea FILM

 የመልሶ ማቋቋም ጥሪዎች እየጨመሩ ይሄዳሉ

የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ ለባለቤቱ ለግብፅ እንዲመለስ ጥሪ መቅረብ የጀመረዉ ከግኝቱ በኋላ በርሊን እንደደረሰ ብዙም ሳይቆይ ጀምሮ ነዉ። የታላቁ የግብፅ ሙዚየም በጊዛ ከተከፈተ ወዲህ ነፈርቲቲ ትመለስ የሚለዉ ጥያቄ እየጎላ መጥቷል። ግብፃዊትዋ የታሪክ ተመራማሪ ሞኒካ ሃና የነፍሪቲቲ በርሊን ሙዚየም መሆንን አሳፋሪ ሲሉ ገልፀዉታል። « በበርሊን ለሁለት ዓመታት ኖርያለሁ። እና ነገሩ በጣም አስቸጋሪ ነዉ። ይህ የስዋ ቦታ አይደለም። በጣም አሳፋሪ ነዉ። በርሊን በነፈርቲቲ በጣም ብዙ ገንዘብ  እየሰራ ነዉ።»  

የግብፅ ጥንታዊ ቅርሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ እና የቅርፅ ቁፋሮ ባለሞያዉ ዛሂ ሀዋስ ባለፈው ዓመት ነፈርቲቲ እንድትመለሰ ይፋ ባደረጉት አቤቱታ ላይ ፊርማ እንዲሰባሰብ ማድረጋቸዉን ቀጥለዋል።  "የአቤቱታዉ ዓላማ ፣ የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ ወደ በርሊን የመጣበት ጉዳይን በተመለከተ ዉይይት እንዲጀመር እና ቅርሱን ወደ ካይሮ ለመመለስ  ከጀርመን ባለስልጣናት የተከበረ ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ነው" መሆኑ ተመልክቷል።

የጀርመን የባህል ሚንስትር ቃል አቀባይ ለ DW በጽሑፍ በሰጡት የመግለጫ  “ከግብፅ ጋር በተያያዘ የነፈርቲቲን ከአንገት በላይ ቅርጽን ጨምሮ የግብጽ ባህላዊ ንብረቶች ጥበቃ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሥልጣን ሥር ናቸው” ብለዋል። በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ “የኔፈርቲቲ ቅርፅ ወደነበረበት እንዲመለስ ምንም ዓይነት ጥያቄ ከግብፅ ባለሥልጣናት አለመቅረቡን” እና “እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች ለፌዴራል መንግሥት ቀርቦ እንደማያዉቅ” ገልጿል።

ንግሥት ኔፈርቲቲበበርሊን አዲሱ ሙዚየም ዉስጥ ምስል፦ Christophe Gateau/dpa/picture alliance

ኔፈርቲቲ - ወደ በርሊን የመጣችዉ በሕጋዊ መንገድ ነዉ?

የፕሩሺያን የባህል ቅርስ ፋውንዴሽን ቃል አቀባይ ስቴፋን ሙችለር በጎርጎረሳዉያኑ ጥቅምት 2024 ለዶይቸ ቬለ በጽሑፍ በሰጠዉ መግለጫ “የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ የተገኘው በግብፅ ጥንታዊ ቅርስ ባለሥልጣን በተፈቀደው ቁፋሮ ነው። የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ እና ሌሎች ነገሮች ወደ በርሊን የመጡት በግኝቱ ላይ ከግብፅ ጋር በተካሄደ ክፍፍል ነዉ። የፕሩሺያን የባህል ቅርስ ፋውንዴሽን ቃል አቀባይ ስቴፋን ሙችለር፤ በክፍፍሉ ወቅት የኔፈርቲቲ ጥበባዊ ስር በደንብ የታየ አልነበረም፤ በተለመደዉ አሰራር መሰረት - ጉዳዩ መንግሥትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ጉዳዮችን እና ሕጋዊ ጉዳዮችን ያካተተ አልነበረም፤ ሲሉ ተናግረዋል። « በመሰረቱ  በዝያን ጊዜ በሚሰራዉ ሕግ መሰረት ነዉ ቅርሱ ወደዚህ አገር የመጣዉ። ጉዳዩን ዛሬ ቆም ብለን ስናየዉ ግን ሕጋዊ አልነበረም። »

አዶልፍ ሂትለር ቅርስ መመለስን ከልክሏል  

ግብፅ ጉዳይ ታሪክ አጥኝ ግብፃዊትዋ ሞኒካ ሃና የግብፅ መንግስት የመመለስ መብት የለውም የሚለውን የጀርመንን አቋምም ይጠይቃሉ። በጎርጎረሳዉያኑ 1924 በርሊን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ኤግዚቢሽን ከተደረገ በኋላ የግብፅ ባለስልጣናት የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ እንዲመለስ ጠይቀው እንደነበር ጠቁመዋል፣ እንደ ታሪክ ተመራማሪዋ “የግብፅ መንግስት በእርግጥ እንዲመለስለት መጠየቅ መለመን አለበት ወይ  ሲሉም ተናግረዋል። የግብፅ ህዝብ አስተያየት አንድ እና አንድ ነዉ ሲሉ የሚገልፁት ምሁርዋ “የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ጥንታቂ ቅርስ ለግብፅ እንዲመለስ እንፈልጋለን። የእኛ የሆነው የእኛ ነው” ሲሉም አክለዋል። በዝያን ወቅት ምንምም ሕጋዊነት እንዳልነበረም አክለዋል።

«ግብፅ በወቅቱ በበድርርብ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች። የኦቶማን ቅኝ ግዛት፣ የእንግሊዞች ቅኝ ግዛት፣ ብሎም ፈረንሳዮች ዛሬም የጥንታዊ ቅርስ አገልግሎትን ተቆጣጥረዉ ይገኛሉ። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የግብጽ ጥንታዊ ቅርሶች አገልግሎትን የሚቆጣጠር ግብፃውያን አልነበሩም። በጊዜው የነበሩት ህጎች የተፈጠሩት የተደነገጉት አገዛዞች በነበሩበት ጊዜ  ነው። እነዚህ ሕጎች ዛሬ ማንም ሀገር አይቀበላቸዉም።» በጎረሳዉያኑ  በ 1925  የኔፈርቲቲ ከአንገት በላይ ቅርፅ ወደ ግልብፅ  ካልተመለሰ በሀገሪቱ ውስጥ የጀርመን ተመራማሪዎች ተሳትፎን እንደምታግድ ግብፅ ዝታም ነበር። የሉድቪግ ቦርቻርድትን የምርምር ቁፋሮዎች በገንዘብ የደገፈው የበርሊኑ ነጋዴ እና የኪነ-ጥበብ ጠባቂ ጄምስ ሲሞን፣ ኔፈርቲቲ ወደ ግብፅ እንድትመለስ ሲሉ መከራከራቸዉን ሩት ኢ ኢስኪን “ሌላኛው ኔፈርቲቲ፡ ተምሳሌታዊ ማስመለሻዎች” በሚለው መጣጥፏቸዉ ላይ አስቀምጠዋል።   

ቢineሴ እንደ ንግሥት ኔፈርቲቲ - በ 2018 ምስል፦ Larry Busacca/Getty Images

በዚህም ምክንያት ጀርመናዊዉ የኪነ-ጥበብ ጠባቂ ጄምስ ሲሞን ኔፈርቲቲን ለመመለስ የወጠነዉ እቅድ እውን ሊሆን አልቻለም። በጎርጎረሳዉያኑ 1933 ያደረገዉ ሙከራም እንብዛ አጥጋቢ አልነበረም። የናዚ ፖለቲከኛ ሄርማን ጎሪንግ ኔፈርቲቲን በመመለስ የግብፅን ፖለቲካዊ ታማኝነት ለጀርመን ለማስጠበቅ ተስፋ አድርጎም ነበር። የኔፈርቲቲ ታላቅ አድናቂ የሆነዉ ሂትለር በአንጻሩ "የንግሥቲቱን ጭንቅላት ፈጽሞ አሳልፌ አልሰጥም" ሲል የማስመለሱን እቅድ አግዶታል። 

ግብፃዊትዋ ኔፈርቲቲ

ንግሥት ኔፈርቲቲ ከዛሬ 3400 ዓመታት በፊት “አክሄናተን” ከተባለው ፈርዖን ባሏ ጋር ግብፅ ላይ ነግሣ እንደነበር የታሪክ መዝገባት ያሳያሉ። በእነዚህ ዓመታትም ፈርዖን አክሄናተን በአገሪቱ ሊያስፋፋው በሞከረው “አተን” የተሰኘው ሥርዓተ-አምልኮ ላይ የበኩላን ሚና ተጫውታ ነበር። በተለይም አከሄታተን (ወይ አማርና) በተባለው አዲስ ከተማቸው የዚህን አምላክና የቤተሰቧን ምስሎች በሰፊው አስቀርፃ ነበር። የኢትዮጵያ የቅርስ አስተዳደር ሰነድ ዝግጅት ከፍተኛ ኤክስፐርት የነበሩት አቶ ኃይለመለኮት አግዘዉ፤ አንዳንድ የታሪክ ፀሐፍቶች ኔፈርቲቲን ከንግሥት ሳባ ጋር እንደሚያዛምድዋት ተናግረዉ ነበር። በበርሊን ሙዚየም የሚገኘዉና የግብፅዋ ኔፈርቲቲ ቅርፅ ከቻይና እስከ አዉሮጳ የሚመጡ በርሊን የሚገኘዉን ይህን ሙዚየም እንዲጎበኙ ይጋብዛል፤ በዓለማችን ስለ ኔፈርቲቲ የሚናገረዉም ሆነ የሚያዉቀዉ ሰዉ ቁጥር እጅግ ጥቂት መሆኑ ይታወቃል። የኔፈርቲቲ ቅርፅ የተገኘችበትን መቶኛ ዓመት በማስመልከት ከ 17 ዓመት በፊት በርሊን ላይ ትልቅ ዝግጅት ነበር።

አዜብ ታደሰ  / ኢልሳቤት ግሪኒየር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW