1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ የሙኒኩ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባዔ ዛሬ ጀመረ

ዓርብ፣ የካቲት 10 2015

የሙኒክ የፀጥታ ጉባዔ ተብሎ የሚጠራዉ ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳይ ስብሰባ ደቡባዊ ጀርመን ባባርያ መዲና ሙኒክ ዉስጥ ዛሬ ተጀመረ። የዘንድሮው ጉባዔ ዋንና ትኩረት ሩስያ በዩክሬይን ላይ እያካሄደች ያለቸዉ ጦርነት ላይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባዔዉን በቪዲዮ መልክታቸዉ የከፍቱት የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ቭላዶሚር ዜሌኒስኪ ናቸዉ።

Wladimir Zelensky spricht auf der Münchner Sicherheitskonferenz
ምስል Roman Goncharenko/DW

የሙኒክ የፀጥታ ጉባዔ ተብሎ የሚጠራዉ ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳይ ስብሰባ ደቡባዊ ጀርመን ባባርያ መዲና ሙኒክ ዉስጥ ዛሬ ተጀመረ። የዘንድሮው ጉባዔ ዋንና ትኩረት ሩስያ በዩክሬይን ላይ እያካሄደች ያለቸዉ ጦርነት ላይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።  ጉባዔዉን በቪዲዮ መልክታቸዉ የከፍቱት የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ቭላዶሚር ዜሌኒስኪ ምዕራባዉያን የጦር መሳርያ ከምንግዜዉም በላይ በፍጥነት የጦር መሳርያ እንዲልኩ አሳስበዋል። ዜሌንስኪ ፑቲን እያካሄደዉ ላለዉ የጥጋብ እርምጃ ፋታ መስጠት የለብንም ሲሉ ነዉ የተናገሩት። በመቀጠል የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ በጉባዔዉ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ምዕራባዉያን በቀጣይነት ዩክሬንን ይረዳሉ ሲሉ ቃል ገብተዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮንም ባደረጉት ንግግር ለዩክሬይን በተመሳሳይነት ቃል ገብተዋል። ለሦስት ቀናት የሚዘልቀዉ እና የፊታችን እሑድ ምሽት በሚጠናቀቀዉ በሙኒኩ የፀጥታ ጉባኤ ላይ የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ እና የካናዳዉን ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶውን ጨምሮ የ35 ሐገራት ርዕሳነ  ብሔራትና መራሒያነ መንግሥታት ብሎም  ከ 96 አገሮች የተውጣጡ ፖለቲከኞችና የፀጥታ ጉዳይ ባለሙያዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከ20 ዓመታት በላይ በዚህ ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የሩስያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድሮ በጉባኤዉ ላይ አልተጋበዙም።

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW