1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

50ኛው ዓመት የጀርመን የተመድ አባልነት

ማክሰኞ፣ መስከረም 8 2016

በ1970 ዎቹ የመሀል ግራው የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲው መራሄ መንግሥት ቢሊ ብራንት ከቀድሞዋ ምሥራቅ ጀርመን ጋር ግንኑነታቸውን አሻሻሉ። ይህም ሁለቱም ጀርመኖች የተመድ አባል የሚሆኑበት መንገድ ጠረገ።በጎርጎሮሳዊው መስከረም 18 1973 ዓ.ም. የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክና የጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተመድ 133ተና እና 134ተኛ አባል ሆኑ።

ሁለቱ መንግሥታት የተመሰረቱት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በ1945 ባበቃ በአራት ዓመቱ በ1949 ነበር።  በወቅቱ የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክ መንግሥት ዲሞክራሲያዊ ሕጋዊነት አለኝ በሚል እምነት ብቸኛው የጀርመንና የህዝቡ ተወካይ ነኝ ማለቱ ጉዳዩ ወደፊት እንዳይራመድ ይዞት ነበር።
ናዚ ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተሸነፈ በኋላ አንድ የነበረችው ጀርመን፣ የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ምዕራብ ጀርመንና የጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮምኒስት ምሥራቅ ጀርመን ተብለው ለሁለት መከፈሏ ዋነኛው ምክንያት ነው። ምስል Seth Wenig/AP Photo/picture alliance

ጀርመን የተመድ አባል ከሆነች 50 ዓመት ደፈነች

This browser does not support the audio element.

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ዓለም አቀፍ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር የተቋቋመው የመንግሥታት ድርጅት ከዓለም ትልቁ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። ዋና ዓላማው ለወደፊቱ ጦርነቶችን መከላከል የሆነው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የተመድ በጄኔቫ በናይሮቢ በቭየናና፣ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በሚገኝበት በሄግ ቢሮዎች አሉት ።በጎርጎሮሳዊው ሚያዚያ 25, 1945ዓም 50 ሀገራት ሳንፍራንሲስኮ ካሊፎርንያ ተሰብስበው የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ጀመሩ። ደንቡ በሰኔ 25 ቀን፣  1945 ፀደቆ በጥቅምት 24 ቀን 1945 ዓም ስራ ላይ ዋለ ። ጀርመን የድርጅቱ አባል ከሆነች ትናንት 50 ዓመት ሞላት።ታዲያ ዓለም አቀፍ ሰላምን ጸጥታን ማስጠበቅ ሰብዓዊ መብቶችን ማስጠበቅ ሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ እና ዘላቂ ልማትን ማራመድ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሕግን ማስከበር ዓላማዎቹ የደረገውን የተመድን  ለመቀላቀል ጀርመን ለምን 28 ዓመት ዘገየች? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። ምክንያቱ ግልጽ ነው ይላል የዶቼቬለው የክሪስቶፍ ሀስልባህ ዘገባ። ናዚ ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተሸነፈ በኋላ አንድ የነበረችው ጀርመን፣ የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ምዕራብ ጀርመንና የጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮምኒስት ምሥራቅ ጀርመን ተብለው ለሁለት መከፈሏ ዋነኛው ምክንያት ነው። ሁለቱ መንግሥታት የተመሰረቱት የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በ1945 ባበቃ በአራት ዓመቱ በ1949 ነበር።  በወቅቱ የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክ መንግሥት ዲሞክራሲያዊ ሕጋዊነት አለኝ በሚል እምነት ብቸኛው የጀርመንና የህዝቡ ተወካይ ነኝ ማለቱ ጉዳዩ ወደፊት እንዳይራመድ ይዞት ነበር። ምንም እንኳን ያኔ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች ምዕራባውያን ተባባሪ ኃይላት ዩናይትድ ስቴትስ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክ በድርጅቱ ብቸኛዋ የጀርመን ተወካይ እንድትሆን መደገፋቸው የማይቀር ቢሆንም የጀርመን ዴሞክራቲክ የኮምኒስት ጀርመን ሪፐብሊክ የበላይ ጠባቂ ሶቭየት ህብረት ግን ይህን ባለመቀበልዋ የጀርመን የተመድ አባልነት ሂደት ተገታ።  
በጎርጎሮሳዊው 1970 ዎቹ  መጀመሪያ ላይ የመሀል ግራው የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲው መራሄ መንግሥት ቢሊ ብራንት አካሄዳቸውን ቀይረው ከቀድሞዋ ምሥራቅ ጀርመን ጋር ግንኑነታቸውን አሻሻሉ። ይህም ሁለቱም ጀርመኖች የተመድ አባል የሚሆኑበት መንገድ ጠረገ።በጎርጎሮሳዊው መስከረም 18 1973 ዓ.ም. የፌደራል ጀርመን ሪፐብሊክና የጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተመድ 133ተና እና 134ተኛ አባል ሆኑ። ሁለቱ ጀርመኖች በጎርጎሮሳዊው ጥቅምት 3 ቀን 1990 ዓም ሲዋሀዱ ደግሞ የተናጠሉ አባልነት አብቅቶ የተዋሀደችው ጀርመን በድርጅቱ አባልነት ቀጠለች።  ከዚያን ወዲህ ጀርመን በተመድ ውስጥ ያላት ሚና እየሰፋ ሄደ። ጀርመን ለድርጅቱ ብዙ መዋጮ ከሚሰጡ አባላት አንዷ ናት። በበርካታ የድርጅቱ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ውስጥ ትሳተፋለች። በርካታ የተመድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ያሉባት ሀገርም ናት። የጸጥታው ምክር ቤት እና ጀርመንዓለም አቀፉ የባህር ሕግ ፍርድ ቤት በሰሜን ጀርመንዋ ከተማ በሐምቡርግ ይገኛል በቀድሞዋ ምዓርብ ጀርመን ዋና ከተማ በቦንም የለተያየዩ የተመድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህ ሁሉ ጠንካራ አስተዋጽኦዎች እና ሚዛን ከሚደፋው የጀርመን ኤኮኖሚና ፖለቲካ ጋር በርሊን ድምጽ በድምጽ መሻር በሚያስችለው የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ለመያዝ ለብዙ ዓመታት እየሞከረች ነው። የድርጅቱ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጭ አካል ምክር ቤቱ የሆነው የምክር ቤቱ ቋሚ አባላት ዩናይትድ ስቴትስ ቻይና ሩስያ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ናቸው። የዚህ ምክር ቤት አባል ለመሆን የምትጥረው ጀርመን ምክር ቤቱ አሁንም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የነበረውን ጆጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ነው፤ አሁን ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም ስትል ትከራከራለች። ይህን ሃሳብ የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ የአንቶንዮ ጉተሬሽም ይጋራሉ።

ዓለም አቀፉ የባህር ሕግ ፍርድ ቤት በሰሜን ጀርመንዋ ከተማ በሐምቡርግ ይገኛል በቀድሞዋ ምዓርብ ጀርመን ዋና ከተማ በቦንም የለተያየዩ የተመድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ይገኛሉ። ምስል Richard Drew/AP/dpa/picture alliance
ምስል Michael Sohn/AP Photo/picture alliance

የጀርመን የውጭ ጉዳዮች ምክር ቤት አባልና በዓመት በሩብ ዓመት አንዴ የሚታተመው ኢንተርናስዮናለ ፖሊቲክ የተባለው መጽሔት ዋና አዘጋጅ ሄኒንግ ሆፍ የጀርመን የፀጥታው ምክር ቤት አባል የመሆን እድሏ እጅግ የመነመ ነው ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት አሁን መቀመጫ የያዙት ሀገራት ብዙ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁበትን ይዞታቸውን ለአዲስ መጤዎች ማጋራት አይፈልጉም።ጀርመን ለአውሮጳ ኅብረት ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጥ ጥሪ ስታቀርብ ነበር። ይሄ ከሆነ ደግሞ ያኔ የኅብረቱ አባል የሆኑት ብሪታንያና ፈረንሳይ የያዙትን መቀመጫማስረከብ ስለሚኖርባቸው ይህም ውጤት አላመጣም ነበር። እናም ሆፍ እንደሚሉት ጀርመን ግልጽ አቋም መያዝ ተስኗታል። « በአንድ በኩል የጀርመን የውጭ ፖሊሲ እንደ ዓለም አስተዳደር የመሳሰሉትን በተመድ በተጠናከረ መልኩ ለማስፈን ቢያንስ በሀሳብ ደረጃ እጅግ ጠቃሚ መሣሪያ ነው።የተመድ 75 ኛ ዓመት መታሰብያ በሌላ በኩል ደግሞ የተመድ አወቃቀር በርግጥ መሻሻያ እንደሚያስፈልገው ማየት ይቻላል። ሆኖም ይህ ወደፊት ለመሆኑ  ምንም ተስፋ የለም ።»የጀርመን ጥምር መንግሥት የራሱ የብዝሀ ምዕራፍ አለው።  የተመድ ግቦችን የሚያጣቅስ ይኽው ምዕራፍ ፣ የተመድን በጣም አስፈላጊ እንደመሆኑ ዓለም አቀፍ የፖለቲካና የፋይናንስ ስርዓት ተቋሙን በሰው ኃይል ለማጠናከር ቁርጠኝነቱ አለን፤ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ አሁን ግባችን ነው የሚል ሀሳብ አካቷል። « በተጨባጭ ጀርመን በአሁኑ ጊዜ ከናሚብያ ጋር በመጪው ዓመት የሚካሄድ «የተመድ የመጪው ትውልድ ጉባኤ» የተሰኘ ስብሰባ በማዘጋጀት ላይ ናት። ሆፍ እንደሚሉት በዚህ ጉባኤ ላይ የሚገኙ ልዑካን «ለወደፊቱ ትውልድ ውል» በሚል በታቀደው አጀንዳ ላይ መስማማት ይጠበቅባቸዋል። 
«በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ያሉ ማሻሻያዎችን የሚፈልጉ ኃይሎችን ለማግኘት በድጋሚ የመጣር ጉዳይ ነው። ያ ብቻ በፍጹም በቂ አይሆንም ። በድጋሚ በጠረጴዛ ዙርያ መሰብሰብ የማሻሻያ ሀሳቦቹን  በአንድ ላይ አድርገው መሰነድና ፤ይህንንም ጀርመንን በመሰለ የአውሮጳ ሀገር እና የጀርመን ቅኝ ግዛት በነበረችው በናሚቢያ የደቡቡን የዓለም ክፍል በመወከል፤እንዚህን ሀሳቦች ሰብስቦ የማሻሻያውን አጀንዳ  ወደፊት በማምጣት እንደገና በግልጽ መተርጎም እና ወደፊት ማራመድ ያስፈልጋል።» ሆፍ ይህን ቢሉም መሳካቱን ግን ይጠራጠራሉ።
የተመድ ሌሎች አማራጮች

 የተመድ ግቦችን የሚያጣቅስ ይኽው ምዕራፍ ፣ የተመድን በጣም አስፈላጊ እንደመሆኑ ዓለም አቀፍ የፖለቲካና የፋይናንስ ስርዓት ተቋሙን በሰው ኃይል ለማጠናከር ቁርጠኝነቱ አለን፤ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ አሁን ግባችን ነው የሚል ሀሳብ አካቷል። ምስል Kay Nietfeld/dpa/picture alliance

በተመድ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የተደረጉት ጥረቶች በሙሉ አልተሳኩም። በዚህ የተነሳም ፍፁም የተለየ ሥራ እየተከናወነ  ነው። ሆፍ በተለይ ቻይና ከድርጅቱ አንጻር የሆኑ መዋቅሮችን እየፈጠረች ነው ይላሉ።ይህንንም የቅርብ ጊዜ ምሳሌ በማጣቀስ አብራርተዋል። «አሁን በተጨማሪ የምናየው ነገር በተለይ ቻይና በምዕራባውያኑ አንጻር መዋቅሮችን እየፈጠረች የራሷን መዋቅሮች ለተመድ እንደ አማራጭ ለማቅረብ እየሞከረች ነው ማለት ይቻላል። በሌላ በኩል የጀርመን የውጭ ፖሊሲም በመጠኑም ቢሆን እየተለወጠ ነው። ለዚህም የቅርብ ጊዜው የቡድን ሀያ ጉባኤ ሰዎች ከተመድ ይልቅ የዓለም አስተዳደርን ገቢራዊ ለማድረግና በዚያ ላይ እንዲተማመኑ መሰል አሰራር ላይ ለማተኮራቸው አንዱ ምሳሌ ነው። »

የማሊ የሰላም ተልዕኮ እና የጀርመን ሚና
በዚህ ረገድ ብሪክስና ቡድን 20 ይጠቀሳሉ። የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስን በተመሳሳይ ባህርይዋ ፎሪን ፖሊ በተባለው መፅሔት ላይ ተችተዋታል።ዩናይትድ ስቴትስ « ዓለም አቀፋዊ እና ሁሉን አካታች የሆነ እርምጃዎችን እያገለለች የተናጠል እና የሁለትዮሽ ስምምነቶች መውሰዷ ዓለም አቀፍ እርምጃዎችን ያሳንሳል፤ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ያዳክማል ካሉ በኋላ አዲስ ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ ካልተመሰረተ በስተቀር የዓለም አቀፍ ስርዓት የሚዛባበት ዘመን መምጣቱ አይቀርም ሲሉ ጎርደን ፎሪን ፖሊሲ በተባለው የአሜሪካ መጽሔት ላይ አስጠንቅቀዋል። ያም ሆኖ በተመድ መርህ የተቃኘው የጀርመን የውጭ ፖሊሲ አሁን በመጠኑም ቢሆን እየተቀየረ ነው ብለዋል ሆፍ።በጀርመን የውጭ ፖሊሲ ዓለም አቀፍ ስርዓት ከቁልፍ ቃላቶች አንዱ ነው። ይህም ለብዙ አሥርት ዓመታት ዘልቋል። ሆኖም የጀርመን መንግሥትም ቢሆን እንደ ቀድሞው ስለ ተመድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እያሰበ አይደለም ይላል የዶቼቬለው ክርስቶፍ ሀስልባህ ።

ክሪስቶፍ ሀስባልህ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW