1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ የጃዋር መሐመድ የምስጋና ጉዞ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 27 2014

አቶ ጃዋር መሐመድ በእስር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ለሳቸውና አብረዋቸው ለታሰሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ደጋፊዎቻቸው አድርገዋል ላሉት ጥረት ዛሬ ምስጋና አቀረቡ። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጃዋር ምስጋናውን ያቀረቡት ዛሬ በጀርመን ኑርንበርግ ከተማ አቅራቢያ በተዘጋጀ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ በአካል ተገኝተው ነው።

[No title]

የአቶ ጃዋር መሐመድ በጀርመን ከደጋፊዎቻቸውጋ ያደረጉት ውይይት

This browser does not support the audio element.

ይህ የጉዟቸው አንደኛው አላማ ሲሆን ሌላኛዋ አላማ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚደረግ ጥረት ውስጥ ደጋፊዎቻቸው የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማሳሰብ  ነው ተብሏል። ጉብኝታቸው አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካን የሚያካልል ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ እና ቤልጄም ከመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት ከደጋፊዎቻቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀኑ ስብሰባውን እየተከታተለ የሚገኘው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ታምራት ዲንሳ ዘግቧል። አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ለሁለት ዓመት ገደማ ያህል በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል። 

ታምራት  ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW