ጀርመን፤ 55ኛዉ የዓለም የፀጥታና ደህንነት ጉባዔ
ዓርብ፣ የካቲት 8 2011ማስታወቂያ
55ኛዉ የዓለም የፀጥታና ደህንነት ጉባዔ ዛሬ ምሽት ላይ በደቡብዊ ጀርመን በባቫርያ ግዛት ሙኒክ ከተማ ጀመረ። ከ 40 በላይ የዓለም መንግሥትና የመንግሥታት ተጠሪዎች ታዋቂ ፖለቲከኞች የሚሳተፉበት ይህ ጉባዔ በዓለማችን የሚገኙ ፖለቲከኞች ፤ የፀጥታ እና የመከላከያ ጉዳይ ምሑራን ትልቅ እዉቅና የሚሰጡት ዓለም አቀፍ ጉባዔ በመሆኑ ይታወቃል። እስከ ፊታችን እሁድ ምሽት በሚዘልቀዉ የሙኒኩ የዓለም የፀጥታና ደህንት ጉባዔ ላይ የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ተካፋይ ናቸዉ። በዘንድሮዉ ጉባዔ በርካታ አባላት ያሉት ልዑክ የላከችዉ ቻይና ናት።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ