ጄኮብ ዙማ እና የተቀሰቀሰባቸው የሙስና ክስ5 ጥር 2001ማክሰኞ፣ ጥር 5 2001የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዳስረዳው ከዚህ ቀደም በዙማ ላይ የተመሰረተው የሙስና ክስ እንዲሰረዝ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተላለፈው ውሳኔ ስህተትና መሰረታዊ ህጋዊ ደረጃዎችንም ያልጠበቀ ነበር ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግጄኮብ ዙማምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያበደቡብ አፍሪቃ የፊታችን ሚያዚያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የአፍሪቃ ብሄራዊ ምክር ቤቱ መሪ ጄኮብ ዙማ በቀላሉ ድል እንደሚጎናፀፉ እስከትናንት ድረስ አንዳችም አጠራጣሪ ነገር አልነበረም ። ሆኖም ዙማ ያለ መሰናክል ማሸነፍ መቻላቸው እንዲያውም ከነአካቴው ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር መብቃታቸው ከትናንት አንስቶ ማነጋገር ጀምሯል ።