1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ገራድነት በስልጤ

ሐሙስ፣ መስከረም 24 2011

ገራድ የስልጤ ማህበረሰብ የአስተዳደር ስርዓት ነው።  በሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች መሀል የስልጤ ብሄረሰብ አንዱ ነው። የስልጤ ዞን ከአዲስ አበባ ደቡብ ክልል ሆሳእና መንገድ 172 ኪ,ሜ ርቀት ከመንገድ 60 ኪ,ሜ ገባ ብሎ ይገኛል። 3 ሺ ኪ,ሜ ስፋትን ሲያካልል ከጉራጌ፣ ከሀዲያ፣ አላባና ከኦሮሚያ ብሄረሰቦች ተጎራብቷል።

Meskel Urlaubsort Äthiopien
ምስል DW/R.Kifle

የስልጤ ማህበረሰብ የገራድ ባህላዊ አስተዳደር

This browser does not support the audio element.

 

1.5 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት እንዳለው ይገመታል። በስልጤ ማህበረሰብ የገራድነት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ቅጫ ይባላል። ስርዓቱን ለማስፈጸም ባህላዊ አስተዳደሩ ከሚሰጠው የስልጣን ወሰኖች ከፍተኛውና የመጨረሻው ደረጃ ነው። ታማኝ፣ በሀብት ደረጃ የተሻሉ፣ ስራ ወዳድ፣ ውሸትን አጥብቆ የሚያወግዝ፣ ችግሮች ሲከሰቱ የመፍትሄው አፈላላጊ የሆነ፣ አዛኝ፣ ጥሩ ባህሪይ ያለው፣ የገራድነት ስልጣንና ክብር ይሰጠዋል።

በስልጤ ባህላዊ አስተዳደር ውስጥ የአስተዳደሩ ስርዓት መጠሪያ ሴራ አንዳንድ ቦታዎች ኖብር ይባላል። አስተዳደራዊ መዋቅሩ ከታች ጀምሮ ሰርጌነክ ፣ ቦርዴ፣ መውጣ፣ አድአ ይባላሉ።

በነዚህ የአስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ የሚመሩት የአከባቢ ሰዎች የጌኔት መሪዎች ይባላሉ። በአስተዳደር ስርዓት ውስጥ የገራድነት ስርዓትን የሚመሩት ሰዎች ወይም ገራድ በአከባቢው የሰፈሩትን ህብረተሰብ ነው። በአሉበት አከባቢም የአስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶ ይገኛል።

ምስል DW/R.Kifle

ገራድ አለት ገራድ፣ ሳር ገራድ እና ሙለ ገራድ ተብሎ በሦስት ይከፈላል። የሳር ገራድ ሙለ ገራድን እየተከተለ የሱን ልምድ የሚቀስም ከስር ሆኖ የአከባቢ ስራዎችን የሚሰራ ግጭቶች ሲኖሩ የሚፈታ ነው። ሙለ ገራድ የሚባለው በሁለት የሳር ገራዶች ሀላፊ ሆኖ ይሰራል። ሙለ ገራድ በሶስኛው መዋቅር ደረጃ ላይ ሆኖ በአከባቢው ላይ የሰፈሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚመራ ነው።

ሙለ ገረድ ከስር በማድረግ በበላይነት ከአናት የሚመሩት ገራድ አቦ ይባላሉ። የአከባቢው ህብረተሰቦችን አሰባስበው በአንድ ጥላ ስር (ሜቾ) የሚመሩት ታላቅ መሪ ገራድ አቦ ተብለው ይጠራሉ።

ዶር ከይረዲን ተዘራ በአዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ ሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህርና የማህበራዊ ዘርፍ ተመራማሪ ናቸው። ስለገራድ፣ ገራድነት በስልጤ ማህበረሰብ ዘንድ ያለውን ሚናና ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት ያለው ጠቀሜታ ማብራርያ ሰጥተዉናል።   

ገራድነት በዘር የተወረሰ የሚወራረስ ብዙዎች ነው ቢሉም እንደ ዶር ከይረዲን እንዳጠናሁትና አሁን ላይ እንዳለው ለገራድነት ስልጣንና ክብር የሚበቁት በአከባቢው ማህበረሰብ ዘንድ የተከበሩ፣ አስታራቂ፣ ተደማጭነት ያላቸው፣ በኃብት ደረጃቸውም የተሻለ ፣ የቤተሰብ ሀላፊ፣ መልካም ስነ ምግባር ና መሰል ለህብረተሰቡ መልካም አገልግሎትን የሰጠ የስልጣን እርከኑን ይጨብጣል።

ምስል DW/R.Kifle

የገራዶቹ እንቅስቃሴ የበለጠ አየጠነከረ የሚመጣው በመውጣና በአድአ የአስተዳድር መዋቅር ነው። ከታች ጀምሮ ያሉትን የአስተዳድሩ የእርከን ደረጃ ሁሉንም ባሰባሰበ መዋቅር ነው የሚመሩት።

ቀደም ሲል ግዛት በማስፋፋት፣ ከአካባቢ ጋር ባለ ግንኙነት፣ በሚፈጠሩ ግጭቶች የተሻለ የጦር አመራርና ብቃት ያለው ገራድነት ይሰጠው ነበር። ግዛቱን አስፋፍቶ አንድነቱን በመጠበቅ ደረጃ ብቃቱን ያሳየ ስልጣኑ ይሰጠዋል። አሁን ባለው ግን ከዚህ ይለያል ይላሉ ዶር ከይረዲን

የገራድ የአስተዳደር ስርዓት በሶማሌ፣ ሀዲያ፣ ማረቆ አሁንም ድረስ ያለ ሲሆን ሆኖም በስልጤ ማህበረሰብ ጎልቶ ይታያል። ገራድነት የኢትዮጵያ ህዝቦች የእርስ በርስ ትስስር ማሳያ ነው። በተለያዩ ቦታዎች ማህበረሰቡን የሚመሩ ገራዶች አሉ። ሁሉም ገራዶች ባሉበት ህብረተሰብ ተቀባይነታቸው የጎላ ነው።       

ግራዝማች ኢማም ሀጂ ሁሴን ...... ገራድ ናቸው። ዓመቱን ባያስታውሱም ገራድ የሆኑት በቀድሞው ቀዳማዊ ሀይለስላሴ መንግስት ነው ብለዋል።

ገራድነት የስልጣን ገደብ አለውን? እስካሁን ባየሁት የተቀመጠ ነገር የለም ብለውኛል። ህብረተሰቡ ወደ ስልጣኑ ሲያመጣው ቀድሞ በሰጠው መስፈርት ሲሆን በስልጣኑ የሚቆየው ህብረተሰቡ እንደሚሰጠው አመለካከት ይሆናል። ገደብ ግን እንደሌለው ነግረውናል።

ምስል DW/R.Kifle

የገራድ የሰላም አባት ይባላል። በህብረተሰቡ ውስጥም ሆነ አጎራባች በሚኖሩ ህብረተሰቦች ዘንድ የሚኖረውን ግንኙነት ማስተሳሰር። ከሀይማኖት አባቶች፣ ከመንግስትና አጎራባች ክልሎች ጋር ፤ በጋራ ለሚኖሩ ችግሮች መፍትሄ ማፈላለግ፣ ሰላምን ማስፈንና ግጭቶችን መፍታት ፣ በአካባቢ ጥበቃና ልማት ላይ ማስተባበር ተግባራቸው ይሆናል።

በህብረተሰቡ ዘንድ መሰል ባህላዊ አስተዳደራዊ ስርዓት መኖሩ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። ግጭቶችን ለመፍታትና የልማት እንቅስቃሴም ለማድረግ ተሰሚነት ስለሚኖራቸው ከመንግስት ጋር ቀርቦ መስራት ቢቻል መልካም ይሆናል እንደዶር ከይረዲን እምነት። ባህል የህብረተሰብ ማንነት መገለጫ እንደመሆኑ የጋራ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

የ «DW» ተከታታዮች ስለስልጤ ማህበረሰብ የአስተዳደር ስርዓት ያየንበት የእለቱን መሰናዶ ሙሉ ጥንቅር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

 

ነጃት ኢብራሂም  

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW