1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«ገዳይ» የተባሉ ተገደሉ፣ ተጠርጣሪዎች ታሠሩ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 15 2013

በበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ትናንት በከፈቱት ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል፣ቤት፣ ሐብት ንብረት አቃጥለዋል የተባሉ 42 ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት ተገደሉ።የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ «ተደመሰሱ» ካሏቸዉ ሰዎች ጋር በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩ 7 የክልልና የፌደራል መንግሥታት ባለ ሥልጣናት ታስረዋል

Benishangul-Gumuz Regional Communication Affairs Office
ምስል፦ DW/N. Dessalegn

«ገዳይ» የተባሉ ተገደሉ፣ ተጠርጣሪዎች ታሠሩ

This browser does not support the audio element.

በበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ትናንት በከፈቱት ጥቃት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል፣ ቤት፣ ሐብት ንብረት አቃጥለዋል የተባሉ 42 ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት ተገደሉ። የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ «ተደመሰሱ» ካሏቸዉ ሰዎች ጋር በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩ 7 የክልልና የፌደራል መንግሥታት ባለ ሥልጣናት ታስረዋል። ከታሠሩት አንዱ የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ደ ኤታ ናቸው። የመተከል ዞን ቡለን ወረዳ፣ የበኩጂ ቀበሌን  ትናንት ጧት የወረሩ ታጣቂዎች ከ100 እስከ 135 የሚደርሱ ሰላማዊ ሰዎችን ባሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸዉን ትናንት ዘግበናል። የመተከል ዞን «ኮማንድ ፖስት» የተባለዉ የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር በጥቃቱ በትንሽ ግምት 100 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉን ዛሬ አረጋግጧል። ጥቃቱ ትናንት ማታ እዚያዉ ቡለን ወረዳ ዉስጥ ግን በሌሎች ቀበሌዎች ቀጥሎ እንደነበር ነዋሪዎች አስታዉቀዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW