1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋምቤላ ከባድ ዝናብ ያስከተለዉ ጎርፍ አስርሽዎችን አፈናቀለ

ዓርብ፣ ጥቅምት 23 2016

በጋምቤላ ክልል በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም በባሮ፣ጊሎና አኮቦ ወንዝ ሙላት ባስከተው አደጋ ከ36ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ቢሮ አመልክተዋል፡፡ በጋምቤላ ከተማ አራት ከሚደርሱ ቀበሌዎች ውስጥ በወንዝ ሙላት ተፈናቅለው የነበሩ 6ሺ የሚሆኑ ዜጎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተመልክቷል።

የባሮ ወንዝ ሙላት በጋምቤላ በሽዎች የሚቆጠሩትን አፈናቀለ
ፎቶ ማህደር፤ በጋምቤላ ከፍተና ዝናብ ብዙዎችን አፈናቀለምስል privat

በጋምቤላ ከተማ የባሮ ወንዝ ሙላት ዘንድሮ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል፤ በርካቶች ተፈናቅለዋል

This browser does not support the audio element.

በጋምቤላ ክልል በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም በባሮ፣ጊሎና አኮቦ ወንዝ ሙላት ባስከተው አደጋ ከ36ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ቢሮ አመልክተዋል፡፡ በጋምቤላ ከተማ አራት ከሚደርሱ ቀበሌዎች ውስጥ በወንዝ ሙላት ተፈናቅለው የነበሩ 6ሺ የሚሆኑ ዜጎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ቅድሜ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ወልዴ ተናግረዋል፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎች አብዛኞቹ መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ላሬ ከተባለ ወረዳም 6500 ሰዎች በጎርፍ ተፈናቅለው የነበሩ ሲሆን 2500 የሚደርሱ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተነግረዋል፡፡የጎርፍ አደጋ በሊቢያ፤ የአደጋዉን መጠን መቀነስ ይቻል ነበር?

በጋምቤላ ከተማ የባሮ ወንዝ ሙላት ዘንድሮ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም አመልክተዋል፡፡ በመስከረም ወር መጀመሪያ በደረሰው የወንዝ ሙላት 6 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ከከተማው አራት ቀበሌዎች ተፈናቅለው ቆይተዋል፡፡ ያነጋርናቸው በጋምቤላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ በወንዝ ሙላት ተፈናቅለው የነበሩ አንድ ነዋሪ በትምህርት ቤትና ዘመድ ቤት ተጠግቶ የነበሩ በርካታ ሰዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ከባለፈው ማክሰኞ አንስቶ በጣለው ከባድ ዝናብ የወንዙ መጠን አሁንም በመጨመሩ በርካቶችን ማስጋቱን ገልጸዋል፡፡በጋምቤላ ጎርፍ ከ185 ሺህ በላይ ሰዎችን አፈናቀለ

የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ተወካይና በቢሮው የቅድሜ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰይፉ ወልዴ ለዶይቼቨሌ እንደተናገሩት በደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚጥለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የወንዝ ሙላት በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም 36ሺ የሚደርሱ ሰዎችን አፈናቅለዋል፡፡ የባሮ፣አኮቦና ጊሎ ወንዞች ሙላት ያስከተለው ጉዳት ድንገተኛ ስለነበር በወቅቱ ሰዎች ንብረታውን ለማሸሽም እንዳልቻሉ የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ተወካይ አቶ ሰይፉ ወልዴ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሰብል እና ቁም እንስሳት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ሰሞኑን ከባድ ዝናብ እየጣለ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው የወንዝ ሙላት ሰዎችን ዳግም ሊያፈናቅል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውን ጠቁመዋል፡፡ጉዳታቸው የከፋው የአየር ጠባይ ክስተቶች መደጋገም

በጋምቤላ፤ የባሮ ወንዝ ሙላት ዘንድሮ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰምስል privat

በኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላረ እና ጂካዎ ወረዳዎች 10ሺ 345 ሰዎች በውሀ መጥለቅለቅ ተፈናቅለው የነበሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ተገልጸዋል፡፡ የላረ ወረዳው የአደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ታንኮይ ኒድ በወረዳው 6500 ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በላረ ወረዳ ተፈናቅለው በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው ቆይተው ከትናንት በስቲያ ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ የነገሩን አንድ ነዋሪም ንብረታቸው በጎርፍ በመወሰዱ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚሹ ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል የባሮ እና ጊሎ ወንዝ ሙላት በ141ሺ 600 ሄክታር የሚሆን ምርት ላይ ጉዳት ማድረሱን ኦቻ ከ 3 ቀን በፊት ያወጣው መረጃም ያመለክታል፡፡ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማገዝ የመንግስትና የግል ተቋማትን በማስተባበር በመስከረም ወር ውስጥ ድጋፎች መደረጋቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት ገልጸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW