ጋና ከአሜሪካ ጋር ያደረገችው ስምምነትና ተቃውሞው
ዓርብ፣ መስከረም 30 2018
«የሐገሪቱ ሕገ መንግስት ተጥሷል»
ጋና የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞችን ከዩናይትድ ስቴትስ ለመቀበል መወሰኗ በሐሪቱ ነዋሪዎችና ፖለቲከኞች ውዝግብ ፈጥሯል። የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የሰብአዊ መብት የሚጥስ ሲሉት፤ ፖለቲከኞች ደግሞ »ሕግ የጣሰ» ሲሉ ተቃዎሞአቸውን ገልጸዋል።
በያዝነው ወር መጀመሪያ ጋና ከዩናይትድ ስቴትስ በግዳጅ እንዲመለሱ የተደረጉ 14 የምዕራብ አፍሪቃ ስደተኞችን ተቀብላለች። ይሁንና ስደተኞቹን መልሳ ወደየሐገሮቻቸው መመለሷ በፖለቲከኞች ዘንድ ውዝግብን አስነስቷል። እነዚህ በመጀመሪያ ዙር ጋና የደረሱት ስደተኞች በወታደራዊ የጦር ሰፈሮች እንዲታሰሩ መደሩጉን በሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ዘንድ ውግዘትን አስከትሏል። ከዚያም አልፎ ወደየሐገሮቻቸው በግዳጅ እንዲመለሱ መደረጉን ጠበቆቻቸው ለዶይቼቨለ የእንግሊዝና ክፍል ገልጸዋል። እስከ አሁን በወታደራዊ የጦር ሰፈሮች ቆይተው መልሰው ወደ ቶጎ እንዲመለሱ የተደረጉት 8 ስደተኞች መሆናቸውን የሐገሪቱ የምክርቤት አባል ሳሙኤል ጂናፖር የገለጹ ሲሆን የፕሬዝዳንት ጆን ማሃማ መንግሥት የሕግ የበላይነትን አላከበረም ሲሉ ወቅሰዋል ።
« መንግስት ይህን ስምምነት ከዩናይትድ ስቴትስ ማድረጉ እና ስደተኞች የመቀበል ዘመቻ ጀምሯል። ይህ ድርጊት የተከናወነው የሐገሪቱ ምክርቤት ስምምነቱን ሳያጸድቀው መንግስት የሐገሪቱን ሕገመንግስት አንቀፅ 75 የጣሰ ድርጊት ነው የፈጸመው።»
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1992 የጸደቀው የሐገሪቱ ሕገመንግስት አስፈጻሚው አካል ከውጭ ሐገራት የሚያደርጋቸውን አለምአቀፍ ስምምነቶች በሐገሪቱ ምክርቤት መፅደቅ እንዳለባቸው ይደነግጋል። በመሆኑም የጋና ፖለቲከኞች መንግስት የሕገ መንግስት ጥሰት መፈጸሙን ይተቻሉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ምላሽ
የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩድዜቶ አብላክዋ ለሐገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሐገራቸው ከአሜሪካው ፕረዚደንት ጋር ያደረገችው የስደተኞች ስምምነት ከሐገራቸው ጥቅም ተመዝኖ የተካሄደ ነው ብለዋል።
« ይህን ጉዳይ ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ። ከአሙሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረግነው የስደተኞችጉዳይ ስምምነት ለአሙሪካ በጎ ውለታ ለመዋል አደለም። ይህ ስምምነት ከጋና ጥቅም አንጻር መታየት አለበት። ይህ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን በጎ ጥቅም ያለው ነው። በመሆኑም ሃና በአፍሪካ ዋና ተፈላጊ ሐገር ያደርጋታል።»
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ቢሉም የጋና የፖለቲካ አማራጭና የደህንነት ማዕከል መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዶክተር መሐመድ ሱሌይማን ግን ድርጊቱ በጋና ላይ ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ጫናም እንደሚያሳድር ነው የሚገልጹት።
«ለጋና ምንም ረብ የለውም»
«እርምጃው ለኔ ትርጉም አይሰጠኝም። በሁለተኛ ደረጃ ከመልሶች ይልቅ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ይህን ዜና ስመለከት ለኔ ቀድሞ የተsሰማኝ ስሜት ዩናይትድ ስቴትስ ችግሮቿን እንደጋና ወደመሳሰሉ ሐገራት እያስተላለፈች ነው የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ። ምንም እንኳን የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጥቶ መቀበል መርህ የተፈጸመ ነው ቢሉም በሐገሪቱ ኢኮኖሚም ጫና የሚያሳድር ነው። ጥያቄው ምንድነው እኛ ከዙህ ምን እናገኛለን ነው። ጋናውያን መንግስት ይህን ድርጊቱን እንዲያጤነው እየጠየቁ ነው። መንግስት ግን ከድርጊቱ መታቀብ አልቻለም።»
ዶይቸቨለ ያነጋገራቸው የሐገሪቱ ነዋሪዎችም ድርጊቱን በፅኑ ተቃውመውታል።
ዶሚና ኦድዎ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ፀሐይ ጫኔ