1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጋና ዉስጥ ማርበርግ ተኅዋሲ ሰዎችን ገደለ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 12 2014

ጋና ማርበርግ ተኅዋሲ የተባለ እና ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰል ተላላፊ በሽታ የተያዙ ሁለት ሰዎችን ማግኘትዋን ገለፀች። ሰዎቹ ተኅዋሲዉ እንዳለባቸዉ የተረጋገጠዉ በያዝነዉ ወር መጀመርያ ላይ ሁለት ጊዜ ምርመራ ከተደረገላቸዉ በኋላ መሆኑ ተመልክቶዋል።

Marburg-Virus
ምስል፦ Bernhard-Nocht-Institut/Bni/dpa/picture alliance

ጋና ማርበርግ ተኅዋሲ የተባለ እና ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰል ተላላፊ በሽታ የተያዙ ሁለት ሰዎችን ማግኘትዋን ገለፀች። ሰዎቹ ተኅዋሲዉ እንዳለባቸዉ የተረጋገጠዉ በያዝነዉ ወር መጀመርያ ላይ ሁለት ጊዜ ምርመራ ከተደረገላቸዉ በኋላ መሆኑ ተመልክቶዋል። በጋና የተካሄዱት ሁለት ምርመራዎች ሐምሌ 3 ቀን የተረጋገጡ ቢሆንም ጉዳዩ የመጨረሻ ማረጋገጫ እንዲያገኝ ውጤቱ በሴኔጋል በሚገኝ ቤተ ሙከራ በዳጋሚ ማረጋገጥ ይገባል ሲል የዓለም የጤና ድርጅት ገልጿል። የማርበርግ ተኅዋሲ በሽታ እስካሁን ሕክምናም ሆነ ክትባት ያልተገኘለት የደም መፍሰስ እና ትኩሳትን የሚያስከትል ገዳይ እና ተላላፊ በሽታ መሆኑ ተገልፆዋል። ጋና በያዝነዉ ወር መጀመሪ በአሻንቲ ክልል ይኖሩ የነበሩ ሁለት ህመምተኞች ሕይወታቸዉ ካለፈ በኋላ ወረርሽኑን ማግኘትዋን ይፋ ማድረግዋ ታዉቋል። የበሽታዉን ስርጭት ለመግታት ዝግጁነትዋን የገለፀችዉ ጋና ከህመምተኞቹ ጋር ሳይገናኙ አልቀሩም የተባሉ  ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችን እንዲገለሉ አድርጋ ክትትል እያደረገች መሆኑንም አስታዉቃለች። 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW