1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጋዛ ርዳታ እንዳይገባ መከልከሉ ያስክተለው ተቃውሞ

ገበያው ንጉሤ
ሐሙስ፣ ሰኔ 5 2017

ሰኞ፤ ሰኔ 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም 12 ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጎቾችና ተከራካሪዎች የሰብአዊ ርዳታ በጀልባ ጭነው ክጣሊያን ሲሲሊ በመነሳት ወደ ጋዛ ለመግባትና ርዳታ ለማድረስ ያደረጉት ጥረት ባህር ላይ እያሉ በእስራኢል ኃይሎች እንደታገደና ሰዎቹም በቁጥጥጥር ስር እንደዋሉ፤ ርዳታውም እንደተወረሰ የጉዞው ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች አሳውቀዋል።

ግሬታ ቱንበርግን ጨምሮ 12 አንቂዎችን ከርዳታ ቁሳቁስ ጋር ጭና የነበረችው ጀልባ
ግሬታ ቱንበርግን ጨምሮ 12 አንቂዎችን ከርዳታ ቁሳቁስ ጋር ጭና የነበረችው ጀልባምስል፦ Salvatore Allegra/Anadolu/picture alliance

ርዳታ ለማድረስ በሞከሩ የሰብአዊ መብት ተክራካሪዎች ላይ የደረሰው እስርና ወከባ

This browser does not support the audio element.

እስራኤል እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር መክሰረም 7 ቀን፣ 2023 ዓ.ም ሽብርተኛ የምትለው ሃማስ በሲቪሎች ላይ ያደረርሰውን ጥቃት ተክትሎ፤ በጋዛ የከፈተችው ጦርነትና ማፈናቀል እንደቀጥለ ሲሆን፤ ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ ደግሞ የሰብአዊ ርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ ማገዷ፤ በብዙዎች ዘንድ ሕዝብን በረሀብ ለመፍጀት ያለመ የጭካኔ ርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። እስራኤል ግን ርምጃው ጋዛን አሸባሪ ነው ከምትለው ሀማስ የማጽዳት አክል መሆኑን ነው የምትገልጸው።

በእስራኤልና ምራባውያን በአሸባሪነት የተፈረጀው ሀማስ መስከረም 7 ቀን፣ 2023 አማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት 1200 ሰዎች የተገደሉና 251 የታገቱ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ እስራኤል በበኩሏ ከዚያ ወዲህ በጋዛ በከፍተችው ጦርነት  54 ሺ 927 ሰላማዊ ፍልስጤሞች እንደተገደሉና በብዙ ሺ የሚቆ\ጠሩ እንደተፍናቀሉ፤ ሰባዊ እርዳታም እንዳይገባ በመከልከሉ ህዝቡ በጅምላ በረሀብ እየተቀጣ መሆኑኑን የዓለማቀፍ ድርጅቶች ጭምር ይገልጻሉ።

ርዳታ ለማድረስ በሞከሩ የሰብአዊ መብት ተክራካሪዎች ላይ የደረሰው እስርና ወከባ

ይህን የእስራኤልን የሰብአዊ ርዳታ ክልከላ በመቃወም ሰኞ፤ ሰኔ 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም 12 ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጎቾችና ተከራካሪዎች የሰብአዊ ርዳታ በጀልባ ጭነው ክጣሊያን ሲሲሊ በመነሳት ወደ ጋዛ ለመግባትና ርዳታ ለማድረስ ያደረጉት ጥረት ባህር ላይ እያሉ በእስራኢል ኃይሎች ታጉሏል ። ሰዎቹም በቁጥጥጥር ስር እንደዋሉ፤ ርዳታውም እንደተወረሰ የጉዞው ተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች አሳውቀዋል።

ርዳታውን ይዘውና አስተባብረው የእስራኤልን ክልከላ ጥሰው ወደ ጋዛ ለመግባት ጥረት ካደረጉት 12 የነዘርላንድስ ፣ ስፔን፤ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ቱርክ ዜጎች ውስጥ ሰስዊድናዊቷ የአየር ለውጥ ተሟጋች ኽሬታ ቱንበርግና ፈረንሳዊቷ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ሪማ ሃሣን ይገኙበታል።

የእስራኤል መንግስት ጀልባዋ በሕገወጥ መንገድ ወደጋዛ ስታመራ መከልከሏንና በውስጧ የነበሩትም መያዛቸውን፤ ርዳታው ግን በሌሎች የርዳታ ድርጅቶች አማካይነት እንዲሰጥ የሚተላለፍ መሆኑን አስታውቀዋል።

ማክሰኖች እለት ግሬታ ቱንበርግን ጨምሮ ሦስት የጉዞው አባላት ወደ አገራቸው የተላኩ ሲሆን ሌሎቹ አሁንም በእስራኤል ቁጥጥር ስር እንደሆኑ ነው የሚታውቀውምስል፦ Hugo Mathy/AFP

የእስራኤል መንግሥት በበጎ አድራጊዎቹ ላይ የፈጸመው እንግልት

ማክሰኖች እለት ህሬታ ቱንበርግን ጨምሮ ሦስት የጉዞው አባላት ወደ አገራቸው የተላኩ ሲሆን ሌሎቹ አሁንም በእስራኤል ቁጥጥር ስር እንደሆኑ ነው የሚታውቀው። ህሬታ የነበረውን ሁኔታ ስትገልጽ "በእስራኤል ሀይሎች ከህግ ውጭ ተይዘንና ታግተን ነው ያለፍላጎታችን ወደ እስራኤል የተወስድነው። በዓላምቀፉ ባህር ሳለን ነበር የታገትነው። በጀልባው ስር አስቀምጠው ያለፍላጎታችን ወደ እስራኤል ወሰዱን” በማለት ዋናው ነገር ግን ይህ በኛ የደረሰው ሳይሆን በጋዛ የዘር ማጥፋት እየተፈጻመ መሆኑ ነው በማለት መንግስታትና የዓለም ህዝቦች በሙሉ እስራኤል ከዚህ ድርጊቷ እንድትቆጠብና የታሰሩት የጉዞው አባላትም እንዲፈቱ የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርባለች። 

መንግሥታት በእስራኤል ላይ እያቀረቧቸው ያሉ ጥያቄዎችና ያስተላለፏቸው ማዕቀቦች

መንግሥታት በተለይ ዜጎቻቸው የታሰሩባቸው የቱርክ፤ ጀርመን፤ ፈረንሳይና ስዊድን መንግስታት የእስራኤልን ድርጊት በማውገዝ የታሰሩትን እንድትፈታ የሰባዊ እርዳታም እንዲገባ እንድታደርግ ጠይቀዋል። ከዚሁ ጋር በተያይዘና በምራባዊው የፍልስጤም ግዛት የሜጸመውን ጥቃት በምቃወምም ባለፈው ማክሰኞ የብርታኒያ፤ ካናዳ፤ አውስትራሊያ፣ ኒውዝላድና ኖርዌይ መንግስታት በጋራ በተለይ በጠቅላይ ሚኒስተር ናታኒያሁ መንግስት የደህንነትና የገንዝብ ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ የጣሉ መሆቸውን የብርታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዴቪድ ላሚይ አስታውቀዋል ።

ባለፈው ሰኞ 12 ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጎቾችና ተከራካሪዎች የሰብአዊ ርዳታ በጀልባ ጭነው ክጣሊያን ሲሲሊ በመነሳት ወደ ጋዛ ለመግባትና ርዳታ ለማድረስ ያደረጉት ጥረት ባህር ላይ እያሉ በእስራኢል ኃይሎች ታጉሏልምስል፦ Salvatore Allegra/Anadolu/picture alliance

"ዛሬ በእነዚህ ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ ጥለናል፤ ምክንያቱም በምዕራብ ዳርቻ በፍልስጤሞች ላይ የሚፈጸመው ሺብርና የሚካሂዱ የሰፈራ ፕሮግራሞች መቆም ያለባቸው በመሆኑና በሁለት መንግስታት የመፍሄ ሀሳብ በጽኑ ስለምናምን ነው” በማለት የማእቀባቸውን አላማና ግብ አስታውቀዋል።

ሆኖም ግን እስራኤል ይህን እርምጃ አጥብቃ ነው የተቃወመችው። አሜሪካም ርዳታ ይዘው ወደ ጋዛ ለማለፍ የሞከሩትንም ሆነ በሁለቱ ሚኒስትሮች ላይ የተጣለውን ማቀብ ተቃውማለች። ያውሮፓ ህብረትም በአባል መንግስታቱ መካክል ስምምነት የሌለ በመሆኑ ምክኒያት እስራኤል በፍልስጤም ህዝብ ላይ እየወሰድችው ካለው ርምጃና  በጋዛ ካለው ሰብአዊ ቀውስ አንጻር  ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ እይተነገረ ሲሆን፤ በያገሮቹ ያሉ ህዝቦች ግን የእስራኤልን መንግስት ብቻ ሳይሆን መንግስቶቻቸውን በእስራኤል ላይ የያዙትን የተለሳለሰ አቋም በመቃወምና ሰብአዊ ርዳታ ወደጋዛ እንዲገባ በመጠየቅ በየክተሞቻቸው አደባብዮች በብዛት በመውጣት ድምጻቸውን ማሰማት ቀጥለዋል ።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW