ግሪንላንድ በዳቮሱ ጉባኤ፣ ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ፍጥጫ
ዓርብ፣ ጥር 15 2018
ስዊትዘርላንድ ዳቮስ ውስጥ የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ የተከናወነበት ይህ ሳምንት አውሮጳውያንን በጥፍራቸው ያስቆመ ነበር ። በተለይ ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በግሪንላንድ ላይ የያዙት አቋም ለአውሮጳውያን ብርቱ ራስ ምታት ሁኖ ዘልቋል ። ዋነኛ የውጥረቱ ሰበብ የዴንማርክ ግዛት የሆነችው እና ከሩስያ ትይዩ በአርክቲክ ንፍቀ ክበብ ውስጥ ውቅያኖሱ ላይ የተንሳፈፈችው ግሪንላንድ ናት ።
ዶናልድ ትራምፕ «መሬትም እኮ አይደለችም አንዳች ግዙፍ ቁራጭ በረዶ» ሲሉ የገለጧት ራስ ገዟ ግሪንላንድ ። የአሜሪካው ፕሬዚደንት፦ በዚህም አለ በዚያ ጠቅልዬ ወደ ግዛቴ አካትታለሁ ሲሉ መዛታቸው ውጥረቱን አጉልቶት ቆይቷል ። አውሮጳውያኑ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲይዙም አስገድዷቸዋል ።
ስለ ሰሞነኛው እሰጥ አገባ እና ስለ አውሮጳውያኑ አስቸኳይ ጉባኤ እንዲነግረን የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
የዳቮስ የዓለም ኤኮኖሚ መድረክ ባለፈው ሰኞ በይፋ ጀምሮ የተጠናቀቀው ዛሬ ነው ። የዴንማርክ ግዛት ስለሆነችው ራስ ገዟ ግሪንላንድ በዳቮስ መድረክ የነበረው አወዛጋቢ ውይይት በምን ተቋጨ? ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕስ «የሰላም ቦርድ» ያነሱት ሐሳብ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ በማብራራት ይጀምራል ።
ሙሉ ቃለ መጠይቁን በድምፅ ከታች በማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ገበያው ንጉሤ
እሸቴ በቀለ