1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግሪክ፤ በተነሳ የጫካ ቃጠሎ የ 18 ስደተኞች አስክሪን ተገኘ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 16 2015

ግሪክ ዉስጥ በተነሳ የደን ቃጠሎ የ 20 ሰዎች አስክሪን መገኘቱ ተነገረ። ሟቾች ምናልባትም ስደተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። እሳት ቃጠሎ የተነሳበት የግሪክ ደናማ አካባቢ በአብዛኛዉ ከቱርክ የሚመጡ ህገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት አካባቢዎች የሚሻገሩበት ቦታ እንደሆነም ተመልክቷል።

ግሪክ ዉስጥ በተነሳ የደን ቃጠሎ  ከ 20 ሰዎች በላይ ሞቱ
ግሪክ ዉስጥ በተነሳ የደን ቃጠሎ ከ 20 ሰዎች በላይ ሞቱምስል ALEXANDROS AVRAMIDIS/REUTERS

ግሪክ ዉስጥ በተነሳ የደን ቃጠሎ የ 20 ሰዎች አስክሪን መገኘቱ ተነገረ። ሟቾች ምናልባትም ስደተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። እሳት ቃጠሎ የተነሳበት የግሪክ ደናማ አካባቢ በአብዛኛዉ ከቱርክ የሚመጡ ህገ-ወጥ ስደተኞች ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት አካባቢዎች የሚሻገሩበት ቦታ እንደሆነም ተመልክቷል። አስክሪኖቹ የተገኙት አንዲት አነስተኛ ጎጆ ብጤ ቤት ዉስጥ እንደሆነ እና አንድ ሌላ በጢስ ታፍኖ ሳይሞት እንዳልቀረ የተነገረ ስደተኛ አስክሪን በጫካ ዉስጥ መገኘቱ ተመልቷል። ከቱርክ ወደ ግሪክ በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞች በግሪክ ድንበር ላይ በሚገኘዉ ጫካ ውስጥ በላስቲክ ጎጆ ቀልሰዉ ለጥቂት ቀናት ተደብቀዉ ከቆዩ በኋላ በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ወደ ምዕራብ ግሪክ እና ወደ ሌሎች የአውሮጳ አገሮች ጫካዉ አቅራቢያ ካለ አውራ ጎዳና በተሽከርካሪ እንደሚወሰዱ ተመልክቷል።


አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW